ወደ ቲቶ መግቢያ
መግቢያ
ቲቶ ከአረማዊነት ወደ ክርስትና የተመለሰ ሲሆን ጳውሎስን በወንጌል ተልእኮው በቅርብ የሚረዳ የሥራ ጓደኛው ነበር፤ ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው በዕድሜ አነስተኛ ለሆነው ለዚሁ ለሥራ ጓደኛው ለቲቶ ሲሆን ቲቶ በዚያን ጊዜ የቤተ ክርስቲያንን ሥራ በመቈጣጠር በቀርጤስ ይገኝ ነበር። መልእክቱ የሚያተኲረው በሦስት ዋና ዋና ነገሮች ላይ ነው፦
አንደኛ፥ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በተለይ በቀርጤስ ሰዎች መጥፎ ሥነ ምግባር አንጻር ምን ዐይነት ሥነ ምግባር ሊኖራቸው እንደሚገባ ለቲቶ ማሳሰቢያ ይሰጠዋል፤ ሁለተኛ፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ቡድኖች ማለትም በዕድሜ የገፉ ወንዶችንና ሴቶችን፥ እንዲሁም ወጣቶች ወንዶችንና አገልጋዮችን እንዴት ማስተማር እንደሚገባው ቲቶን ይመክረዋል፤ በመጨረሻም ስለ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በተለይም በሰላምና በወዳጅነት ስለ መኖር፥ እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጥላቻን፥ ክርክርንና መለያየትን ስለ ማስወገድ፥ ለቲቶ ምክርና መመሪያ ይሰጠዋል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1-4
የቤተ ክርስቲያን መሪዎች 1፥5-16
በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ቡድኖች የሥራ ድርሻ 2፥1-15
ምክርና ማስጠንቀቂያ 3፥1-11
ማጠቃለያ 3፥12-15
Currently Selected:
ወደ ቲቶ መግቢያ: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

: