1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12
12
የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች
1ስለ መንፈሳዊ ነገርም፥ ወንድሞች ሆይ! አላዋቂ እንድትሆኑ አልፈልግም። 2አሕዛብ በነበራችሁበት ጊዜ በማታውቁት ነገር ተመርታችሁ መናገር ወደማይችሉ ጣዖቶች ትወሰዱ እንደ ነበር ታውቃላችሁ። 3ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር “ኢየሱስ የተረገመ ነው፤” የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው፤” ሊል ማንም እንደማይችል አስታውቃችኋለሁ።
4 #
ሮሜ 12፥6-8። ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉ፤ መንፈስ ግን አንድ ነው፤ 5ጌታም አንድ ሲሆን፤ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችም አሉ፤ 6አሠራሮችም ልዩ ልዩ አሉ፤ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ ግን አንዱ እግዚአብሔር ነው። 7ለእያንዳንዱ የመንፈስን መገለጥ የሚሰጠው ለጥቅም ነው። 8ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋል፤ ለሌላውም ያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፤ 9በዚያው መንፈስ ለአንዱ እምነት ይሰጠዋል፤ ለሌላው የመፈወስ ስጦታን በዚያው አንድ መንፈስ ይሰጠዋል፤ 10ለሌላው ተአምራትን የማድረግ ኃይል ይሰጠዋል፤ ለሌላው ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱ መናፍስትን መለየት፥ ለሌላው በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለሌላውም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤ 11ይህን ሁሉ ግን አንዱና ያው መንፈስ ያደርጋል፤ እንደፈቃዱም ለእያንዳንዱ ሰው ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።
በአንድ አካል የተለያዩ የአካል ክፍሎች እንዳሉ
12 #
ሮሜ 12፥4፤5። አካልም አንድ እንደሆነ ብዙም የአካል ክፍሎች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ክፍሎች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤ 13አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባርያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።
14አካል ብዙ የአካል ክፍሎች እንጂ አንድ የአካል ክፍል አይደለምና። 15እግር “እኔ እጅ አይደለሁምና የአካል ክፍል አይደለሁም፤” ብትል፥ ይህን በማለትዋ የአካል ክፍል መሆንዋ ይቀራልን? 16ጆሮም “እኔ ዐይን አይደለሁምና የአካል ክፍል አይደለሁም፤” ቢል፥ ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን? 17አካል ሁሉ ዐይን ቢሆን መስማት ወዴት በተገኘ? ሁሉም መስማት ቢሆን ማሽተት ወዴት በተገኘ? 18አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ የአካል ክፍሎችን እያንዳንዳቸው በአካል አድርጎአል። 19ሁሉም አንድ የአካል ክፍል ቢሆንስ አካል ወዴት በሆነ? 20ዳሩ ግን አሁን የአካል ክፍሎች ብዙዎች ናቸው፤ አካል ግን አንድ ነው። 21ዐይን እጅን “አታስፈልገኝም፤” ልትለው አትችልም፤ ወይም ራስ ደግሞ እግሮችን “አታስፈልጉኝም፤” ሊላቸው አይችልም። 22ነገር ግን ደካሞች የሚመስሉ የአካል ክፍሎች ይልቁን የሚያስፈልጉ ናቸው፤ 23ከአካልም ክፍሎች ያልከበሩ ሆነው የሚመስሉንን በሚበዛ ክብር እናለብሳቸዋለን፤ በምናፍርባቸውም የአካላችን ክፍሎች ክብር ይጨመርላቸዋል፤ 24ፊት ለፊት ለሚታዩት የአካላችን ክፍሎች ግን ይህ አያስፈልጋቸውም። እግዚአብሔር ግን ለማየት የሚያሳፍሩ መስለው የሚታዩንን የአካል ክፍሎች በበለጠ ክብር እንዲያዙ አድርጎ የአካል ክፍሎችን አስማምቷል። 25ይህም በአካል ክፍሎች መካከል መለያየት ሳይኖር እርስ በርሳቸው እንዲተሳሰቡ ነው። 26አንድም አካል ቢሠቃይ የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሠቃያሉ፤ አንድ አካልም ቢከበር የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።
27እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የአካሉ ክፍሎች ናችሁ። 28#ኤፌ. 4፥11።እግዚአብሔርም አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት የሚያደርጉትን፥ ቀጥሎም የመፈወስ ስጦታ ያላቸውን፥ ሰዎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፥ አስተዳዳሪዎችንና በተለያዩ ልሳኖች የሚናገሩትን ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ሰይሟል። 29ሁሉም ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸውን? ሁሉስ ተአምራትን ይሠራሉን? 30ሁሉስ የመፈወስ ስጦታ አላቸውን? ሁሉስ በልሳኖች ይናገራሉን? ሁሉስ ይተረጉማሉን? 31ነገር ግን የላቀውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ። ደግሞም ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ አሳያችኋለሁ።
Currently Selected:
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: