1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 4
4
የቃል ኪዳኑ ታቦት መማረክ
1የሳሙኤልም ቃል ወደ እስራኤል ሁሉ ደረሰ። በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ሊወጉ ወጡ፤ እነርሱ በአቤንኤዘር ሲሰፍሩ፥ ፍልስጥኤማውያን ደግሞ በአፌቅ ሰፈሩ። 2ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመግጠም ሠራዊታቸውን አሰለፉ፤ ጦርነቱ እንደ ተፋፋመም፥ እስራኤላውያን በፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ፤ በጦርነቱም ላይ አራት ሺህ ያህል እስራኤላውያን ተገደሉ። 3#ዘኍ. 10፥35፤ 14፥42-44።ሠራዊቱ ወደ ሰፈር በተመለሰ ጊዜ የእስራኤል አለቆች፥ “ዛሬ ጌታ በፍልስጥኤማውያን እንድንሸነፍ ያደረገን ለምንድን ነው? አብሮን እንዲወጣ፥ ከጠላቶቻችንም እጅ እንዲያድነን የጌታን የኪዳኑን ታቦት ከሴሎ እናምጣ” አሉ። 4#ዘፀ. 25፥21-22።ስለዚህ ሕዝቡ ሰዎችን ወደ ሴሎ ልከው፥ በኪሩቤል መካከል በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን የሠራዊት ጌታን የኪዳን ታቦት አስመጡ፤ ሁለቱ የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስ ከኪዳኑ ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።
5የጌታ የኪዳኑ ታቦት ወደ ሰፈር በገባ ጊዜ፥ ምድር እስክትናወጥ ድረስ እስራኤላውያን ሁሉ ታላቅ የሆታ ድምፅ አሰሙ። 6ፍልስጥኤማውያንም ይህን ታላቅ የሆታ ድምፅ ሲሰሙ፥ “በዕብራውያን ሰፈር የምንሰማው ይህ ሁሉ የሆታ ድምፅ ምንድነው?” ሲሉ ጠየቁ። የጌታም ታቦት ወደ ሰፈር መምጣቱን በተረዱ ጊዜ፤ 7ፍልስጥኤማውያንም ፈርተው እንዲህ አሉ፤ “አምላክ ወደ ሰፈሩ መጥቷል፤ ወዮልን! ከዚህ አስቀድሞ እንዲህ ዓይነት ነገር አጋጥሞን አያውቅም። 8ወዮልን! ከእነዚህ ኀያላን አማልክት እጅ ማን ያድነናል? ግብፃውያንን በምድረ በዳ በልዩ ልዩ መቅሠፍት የመቱ እነዚሁ አማልክት ናቸው፤ 9ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ በርቱ! ወንድነታችሁም ይታይ፤ ያለዚያ ባርያ እንዳደረጋችኋቸው ሁሉ፥ ዕብራውያን እናንተን መልሰው ባርያ ያደርጓችኋል። ስለዚህ በወንድነት ጠንክራችሁ ተዋጉ!” 10ፍልስጥኤማውያንም ተዋጉ፤ እስራኤላውያንም ስለ ተሸነፉ እያንዳንዱ ወደየድንኳኑ ሸሸ። ታላቅ እልቂትም ሆነ፤ ከእስራኤልም ሠላሳ ሺህ እግረኛ ወታድሮች ወደቁ። 11#1ሳሙ. 2፥34።የእግዚአብሔር ታቦት ተማረከ፤ ሁለቱም የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስ ተገደሉ።
የዔሊ መሞት
12 #
ኢያ. 7፥6፤ 2ሳሙ. 1፥2፤ ኤር. 7፥12። አንድ የብንያም ወገን የሆነ ሰው ልብሱን ቀዶ፥ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ፥ ከጦሩ ሜዳ እየበረረ ወደ ሴሎ መጣ። 13እዚያ እንደደረሰም፥ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ስለ ተጨነቀ፥ በመንገድ ዳር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር። ሰውየውም ወደ ከተማው ገብቶ የሆነውን ሁሉ ባወራ ጊዜ፥ ከተማው ሁሉ በጩኸት ተናወጠ። 14ዔሊም ጩኸቱን በሰማ ጊዜ፥ “የምን ጩኸት ነው?” ሲል ጠየቀ። ሰውየውም ፈጥኖ መጣና ለዔሊ ነገረው፤ 15ዔሊ የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ስለ ነበር ዐይኖቹ ደክመው ማየት ተስኗቸው ነበር። 16ሰውየውም ዔሊን፥ “ከጦሩ ሜዳ ገና አሁን መምጣቴ ነው፤ ከጦርነቱ አምልጬ የወጣሁትም ዛሬውኑ ነው” ብሎ ነገረው። ዔሊም፥ “ልጄ ሆይ፤ ታዲያ እንዴት ሆነ?” ሲል ጠየቀ። 17ወሬውን ያመጣውም ሰው፥ “እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ሠራዊቱም ከፍተኛ እልቂት ደርሶበታል፤ እንዲሁም ሁለቱ ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ሞተዋል፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት ተማርኳል” ብሎ መለሰለት። 18ሰውየው ስለ እግዚአብሔር ታቦት በተናገረ ጊዜ፥ ዔሊ በቅጥሩ በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ በጀርባው ወደቀ፤ እርሱም ያረጀና ሰውነቱም የሚከብድ ስለ ነበር፥ ዐንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱ ለአርባ ዓመት በእስራኤል ላይ ፈራጅ ነበር።
የፊንሐስ ሚስት አሟሟት
19በዚያን ጊዜ ምራቱ የፊንሐስ ሚስት፥ ነፍሰ ጡር ነበረች፤ የምትወልድበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር፥ የእግዚአብሔርን ታቦት መማረክ፥ የዐማቷንና የባሏንም መሞት በሰማች ጊዜ ምጡ ስለ ጠናባት ተንበርክካ ወለደች። 20#1ሳሙ. 14፥3፤ ዘፍ. 35፥16-20።ለመሞትም በምታጣጥርበት ጊዜ፥ በአጠገቧ የነበሩት ሴቶች፥ “አይዞሽ፤ ወንድ ልጅ ወልደሻልና በርቺ” አሏት። እርሷ ግን መልስ አልሰጠችም፤ ልብ ብላም አላዳመጠችም። 21የእግዚአብሔር ታቦት ስለ ተማረከ፥ ዐማቷና ባሏም ስለ ሞቱ፥ “ክብር ከእስራኤል ተለይቷአል” ስትል የሕፃኑን ስም ኢካቦድ#4፥21 በዕብራይስጥ “ክብር አልባ” ማለት ነው አለችው። 22#መዝ. 78፥61።ከዚያም፥ “የእግዚአብሔር ታቦት ተማርኳልና ክብር ከእስራኤል ተለይቶአል” አለች።
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 4: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: