1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 6
6
የቃል ኪዳኑ ታቦት መመለስ
1የጌታም ታቦት በፍልስጥኤማውያን ሀገር ሰባት ወር ተቀመጠ። 2ፍልስጥኤማውያን ካህናትንና ጠንቋዮችን ጠርተው፥ “የጌታን ታቦት ምን እናድርገው? ወደ ስፍራው እንዴት መመለስ እንደሚገባን ንገሩን” አሏቸው። 3እነርሱም፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት የምትመልሱ ከሆነ ከበደል መሥዋዕት ጋር ስደዱት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፤ በዚያን ጊዜ ትፈወሳላችሁ፤ እጁም ከእናንተ ላይ ለምን እንዳልተነሣ ታውቃላችሁ” አሏቸው። 4እነርሱም፥ “የምንልከው የበደል መሥዋዕት ምን መሆን አለበት?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተንም ሆነ አለቆቻችሁን የመታው መቅሠፍት አንድ ዓይነት በመሆኑ፥ በፍልስጥኤማውያን ገዥዎች ቍጥር አምስት የወርቅ ዕባጮችና አምስት የወርቅ ዐይጦች ላኩ። 5አገሩን በማጥፋት ላይ ባሉት ዕባጮችና ዐይጦች ዓይነት ምስሎችን ሠርታችሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ክብር ስጡ። ይህን ካደረጋችሁ እጁን ከእናንተ፥ ከአማልክቶቻችሁና ከምድራችሁ ላይ ያነሣ ይሆናል። 6#ዘፀ. 7፥14፤ 8፥15፤ 9፥34።ግብፃውያንና ፈርዖን እንዳደረጉት ልባችሁን የምታደነድኑት ለምንድን ነው? እነርሱ እስራኤላውያንን የለቀቋቸው እርሱ በጽኑ ከቀጣቸው በኋላ አይደለምን? 7#ዘኍ. 19፥2፤ ዘዳ. 21፥3፤ 2ሳሙ. 6፥3።ስለዚህ አዲስ ሠረገላና ቀንበር ያልተጫነባቸው ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውን ግን ወደ ቤት መልሷቸው። 8የጌታን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩ፤ ስለ በደልም መሥዋዕት ያቀረባችሁትን ልዩ ልዩ የወርቅ ዕቃ በሣጥን ውስጥ አድርጋችሁ በታቦቱ አጠገብ አኑሩት፤ መንገዱንም እንዲሄድ ልቀቁት። 9ከዚያም ወዴት እንደሚሄድ ተመልከቱ፤ ወደ ገዛ አገሩ ወደ ቤትሼሜሽ አቅጣጫ የሚሄድ ከሆነ፥ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እርሱ ነው። ወደዚያ ካልሄደ ግን፥ መከራው በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የእርሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን።”
10እነርሱም እንደዚሁ አደረጉ። ሁለቱን ላሞች ወስደው በሠረገላው ጠመዷቸው፤ እንቦሶቻቸውንም በቤት ውስጥ ዘጉባቸው። 11የጌታን ታቦት በአይጦችና በእባጮች ምስል ከተሠራ ወርቅ ከተሞላበት ሣጥን ጋር በሠረገላው ላይ አስቀመጡ፤ 12ከዚያም ላሞቹ መንገዳቸውን በመያዝ፥ እምቧ እያሉ፥ ቀጥ ብለው ወደ ቤትሼሜሽ አመሩ። የፍልስጥኤም ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ተከተሏቸው።
የቃል ኪዳኑ ታቦት በቤትሼሜሽ
13በዚህ ጊዜ የቤትሼሜሽ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴአቸውን ያጭዱ ነበር፤ ቀና ብለው ሲመለከቱም ታቦቱን በማየታቸው በጣም ደስ አላቸው። 14#2ሳሙ. 24፥21-25።ሠረገላውም ወደ ቤትሼሜሽ ወደ ኢያሱ እርሻ መጥቶ ቆመ። በዚያ ስፍራ አንድ ትልቅ ቋጥኝ ነበር። ሕዝቡም የሠረገላውን ዕንጨት ፈለጡት፤ ላሞቹንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ለጌታ አቀረቡ። 15#ዘዳ. 31፥25፤ 1ዜ.መ. 15፥2።ሌዋውያኑም የጌታን ታቦትና የወርቅ ዕቃዎቹን የያዘውን ሣጥን አውርደው በትልቁ ቋጥኝ ላይ አኖሩ። በዚያችም ዕለት የቤትሼሜሽ ሕዝብ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ መሥዋዕቶችንም ሠዉ። 16አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎችም ይህን ተመልክተው፥ በዚያው ዕለት ወደ ዔቅሮን ተመለሱ።
17ፍልስጥኤማውያን ስለ በደል መሥዋዕት ለጌታ የላኳቸው የወርቅ ዕባጮች እነዚህ ናቸው፤ አንዱ ስለ አሽዶድ፥ አንዱ ስለ ጋዛ፥ አንዱ ስለ አስቀሎና፥ አንዱ ስለ ጌት፥ አንዱ ስለ ዔቅሮን የቀረቡ ነበሩ። 18#1ሳሙ. 7፥12፤ ዘፍ. 31፥52፤ ኢያ. 24፥27።የወርቅ ዐይጦቹም ቍጥር፥ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች በሚያስተዳድሯቸው የተመሸጉ ከተሞችና ከእነዚህ ውጭ ባሉት መንደሮቻቸው ቍጥር ልክ ነው። በቤትሼሜሻዊው በኢያሱ እርሻ ውስጥ የጌታን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ትልቅ ቋጥኝ እስከ ዛሬ ምስክር ነው።
19ጌታም ከቤትሼሜሽ ሰዎች ጥቂቱን መታ፤ ምክንያቱም ወደ ጌታ ታቦት ውስጥ በመመልከታቸው ነበር። ከመካከላቸው ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ ጌታ እጅግ ስለ መታቸውም ሕዝቡ አለቀሱ።
የቃል ኪዳኑ ታቦት በቂርያትይዓሪም
20የቤትሼሜሽም ሰዎች፥ “ታዲያ በዚህ ቅዱስ አምላክ በጌታ ፊት ማን መቆም ይችላል? ታቦቱስ ከዚህ ወጥቶ ወደ ማን ይሂድ?” አሉ። 21ከዚያም ወደ ቂርያትይዓሪም ሰዎች መልእክተኞች ልከው፥ “ፍልስጥኤማውያን የጌታን ታቦት መልሰውልናል፤ መጥታችሁ ወደ እናንተ ውሰዱት” አሏቸው።
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 6: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: