YouVersion Logo
Search Icon

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች መግቢያ

መግቢያ
ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች የጻፈላቸው ሁለተኛው መልእክት የተጻፈው በቆሮንቶስ ከነበረችው ቤተ ክርስቲያን ጋር የነበረው ግንኙነት እጅግ አስቸጋሪ በሆነበት ጊዜ ነው። አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባሎች ከበድ ያሉ ነቀፋዎችን የሰነዘሩበት ቢሆንም ጳውሎስ ዕርቅ ለመፍጠር ታላቅ ፍላጎት እንዳለው ያሳያል፤ ይህም በሚሆንበት ጊዜ ታላቅ ደስታ ሊሰማው እንደሚችል ይገልጣል።
በመልእክቱ መጀመሪያ ክፍል ላይ ጳውሎስ በቆሮንቶስ ከነበረችው ቤተ ክርስቲያን ጋር ስላለው ግንኙነት በመግለጥ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ለተነሣው ነቀፋና ተቃውሞ ለምን ከረር ያለ መልስ እንደሰጣቸው ያስረዳል። ከዚህም ጋራ በማያያዝ ይህ የእርሱ ተግሣጽ ወደ ንስሓና ወደ ዕርቅ የመራቸው በመሆኑ የተሰማውን ደስታ ይገልጥላቸዋል። ቀጥሎም በይሁዳ ያሉትን ክርስቲያኖች ለመርዳት በለጋስነት እንዲሰጡ ያሳስባቸዋል። በመጨረሻዎቹ ምዕራፎች ጳውሎስ በሐዋርያነቱ ላይ ስለ ቀረበበት ክስ መከላከያ ይሰጣል። በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን እውነተኞች ሐዋርያት በማድረግ ጳውሎስ ሐሰተኛ ሐዋርያ ነው እያሉ ይከሱት ነበር።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መቅድም (1፥1-11)
ጳውሎስና የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን (1፥12—7፥16)
በይሁዳ ለሚገኙ ክርስቲያኖች ርዳታ (8፥1—9፥15)
ጳውሎስ ለሐዋርያዊ ሥልጣኑ ያቀረበው መከላከል (10፥1—13፥10)
ማጠቃለያ (13፥11-13)
ምዕራፍ

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy