2ኛ የጴጥሮስ መልእክት መግቢያ
መግቢያ
ሁለተኛው የሐዋርያው የጴጥሮስ መልእክት የተጻፈው በልዩ ልዩ ስፍራ ለሚገኙ የጥንት ክርስቲያኖች ነው። የመልእክቱ ዋና ዓላማ የሐሰተኞች መምህራንን ክፉ ሥራና የእነርሱንም ትምህርት አስመልክቶ የተከሠተውን የሥነ ምግባር ብልሹነት መቃወም ነው። ለተፈጠሩት ችግሮች መፍትሔ የሚሆነው ኢየሱስ ሲያስተምር በዐይናቸው ያዩና በጆሮአቸው የሰሙ ሰዎች ያስተላለፉትን ምስክርነት በአንክሮ መያዝና መከተል ነው። ጸሐፊው በተለይ ያተኮረው “ክርስቶስ ተመልሶ አይመጣም” የሚለውን የሐሰት ትምህርት በመንቀፍ ላይ ነው፤ ይህንኑ አስመልክቶ “ክርስቶስ ተመልሶ ከመምጣት የሚዘገየው ሰው ሁሉ ከኃጢአቱ እንዲመለስ፥ ማንም ሰው እንዲጠፋ እግዚአብሔር ስለማይፈልግ ነው” ይላል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1-2)
የክርስቲያን ጥሪ (1፥3-21)
ሐሰተኞች መምህራን (2፥1-22)
የክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት (3፥1-18)
ምዕራፍ
Currently Selected:
2ኛ የጴጥሮስ መልእክት መግቢያ: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: