2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች መግቢያ
መግቢያ
ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንቶስ ሳለ የመጀመርያውን የተሰሎንቄ መልእክት ከጻፈ ከጥቂት ጊዜ በኋላ 51 ዓ.ም. ገደማ ሁለተኛውን የተሰሎንቄ መልእክት ጽፎአል። የተሰሎንቄ ክርስትያኖች መከራና ስደት በርትቶባቸው ተስፋ በመቁረጥ ላይ ይገኙ ነበር፤ እነርሱም መከራቸው ከመብዛቱ የተነሣ ከጳውሎስ የተላከ በሚመስል ደብዳቤና ሐሰተኛ አስተምህሮ የዓለም ፍጻሜ በዘመናቸው እንደሚመጣ አምነው ነበር። ከዚህም አልፈው በክርስትያናዊው ሕይወት መፈጸም የሚገባቸውን ኃላፊነት ስለተዉ ጳውሎስ ይህን መልእክት ሊጽፍ ችሎአል። ስለዚህ እርሱ በዋነኝነት የተሰሎንቄ ክርስትያኖች በጌታ የፍርድ ቀን ሽልማትና ቅጣት እንዳለ አውቀው በእምነታቸው እንዲጸኑ ያሳስባቸዋል፤ የጌታም ቀን ቀርቧል የሚለውን አስተምህሮ በመከተል መረበሽና ሥራ ማቆም እንደማይገባቸው አስተምሯል። ስለሆነም ምእምናን የክርስትያናዊውን ሕይወት መኖር እንደሚገባቸውና ሥራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ መመርያ ለመስጠት አቅዶ የጻፈው መልእክት ነው።
ሁለተኛው የተሰሎንቄ መልእክት በሦስት ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል። አንደኛው ክፍል ምዕራፍ አንድን የሚያጠቃልል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ቤተ ክርስትያን ያቀረበውን ሰላምታና ምስጋና የያዘ ነው። ሁለተኛው ክፍል ምዕራፍ ሁለትን የሚያጠቃልል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ክርስትያኖች በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ላይ ስለ ተነሣው ሐሰተኛ አስተምህሮ ማስጠንቀቅያ የሚሰጥበት ነው። ሦስተኛው ክፍል ምዕራፍ ሦስትን የሚያጠቃልል ሲሆን በመጨረሻ የተሰጠን ምክርንና የስንብት ሰላምታን የያዘ ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1-2)
ምስጋናና አደራ (1፥3-12)
ስለ ክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት የተሰጠ ትምህርት (2፥1-17)
ስለ ክርስቲያናዊ አኗኗር ምክር (3፥1-15)
ማጠቃለያ (3፥16-18)
ምዕራፍ
Currently Selected:
2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች መግቢያ: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: