YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘዳግም 5

5
ዐሥርቱ ትእዛዛት
1 # ዘዳ. 4፥1፤45፤ 5፥31፤ 6፥1፤ 17፤ 20፤ 11፥32፤ 12፥1፤ 26፥16። ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአት በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሕግና ሥርዓት ስሙ። 2ጌታ አምላካችን በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። 3ጌታ ይህችን ቃል ኪዳን ከአባቶቻችን ጋር ብቻ ሳይሆን ያደረገው ዛሬ በዚህ በሕይወት ካለነው ከእኛ ከሁላችንም ጋር ነው። 4#ዘፀ. 19፥3-25፤ 20፥18-19፤ 24፥2።በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ጌታ ፊት ለፊት አናገራችሁ።#ዘዳ. 34፥10፤ ዘኍ. 12፥8። 5እናንተ በእሳቱ ምክንያት ፈርታችሁ፥ ወደ ተራራውም አልወጣችሁምና፤ በዚያን ጊዜ፥ እኔ የጌታን ቃል ልነግራችሁ፥ በጌታና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር። እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦
6 # ዘፀ. 20፥2-17። “ ‘ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ።#ዘፀ. 20፥2፤ መዝ. 81፥11።
7 # ዘዳ. 4፥23-24፤ 31፤ 6፥4-5፤ 7፥9-10፤ 12፥2—13፥18፤ 17፥3፤ 18፥20፤ 24፥16፤ 27፥15፤ ዘፀ. 20፥3-6፤ 34፥6-7፤ 14፤ ዘሌ. 26፥1፤ ዘኍ. 14፥18፤ መዝ. 81፥10፤ 97፥7፤ ኤር. 7፥9፤ 31፥29-30፤ 32፥18-19፤ ሕዝ. 18፥1-24። “ ‘ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።
8“ ‘በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፥ 9በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም። 10ለሚወድዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን አደርጋለሁ።
11 # ዘዳ. 6፥13፤ 10፥20፤ 18፥20፤ 23፥21-23፤ ዘፀ. 20፥7፤ ዘሌ. 19፥12፤ 24፥10-23፤ መዝ. 24፥4፤ ኤር. 29፥23፤ ማቴ. 5፥33-37። “ ‘የጌታን የአምላክህ ስም በከንቱ አትጥራ፥ ጌታ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ሳይቀጣው አይቀርምና።
12 # ዘዳ. 14፥22—16፥17፤ 24፥18፤ 22፤ ዘፀ. 20፥8-11፤ 23፥12፤ 31፥12-17፤ 34፥21፤ ኢሳ. 58፥13-14፤ ኤር. 17፥21-27፤ ማቴ. 12፥1-14፤ ማር. 2፥23—3፥6፤ ሉቃ. 6፥1-11፤ 13፥10-17፤ 14፥1-6፤ ዮሐ. 5፥2-18፤ 7፥22-23። “ ‘ጌታ አምላክህ እንዳዘዘህ፥ እንድትቀድሰው፥ የሰንበትን ቀን ጠብቅ። 13ስድስት ቀን ሥራ፥ ሥራህንም ሁሉ አከናውን፥ 14ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ አምላካችሁ ሰንበት ነው፥ አንተ ወንድ ልጅህም ሴት ልጅህም አገልጋይህም፥ አገልጋይትህም፥ በሬህም፥ አህያህም፥ ከብትህም ሁሉ፥ ወይም በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ፥ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፥ አንተ እንደምታርፍ ሁሉ አገልጋይህና አገልጋይትህ እንዲያርፉ። 15አንተም በግብጽ ባርያ እንደ ነበርህ አስታውስ፥ ጌታ እግዚአብሔር በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ አወጣህ፥ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ትጠብቅ ዘንድ አዘዘህ።
16 # ዘዳ. 21፥18-21፤ 27፥16፤ ዘፀ. 20፥12፤ 21፥15፤ 17፤ ሲራ. 3፥1-16፤ ማቴ. 10፥34-39፤ 12፥46-50፤ 15፥4፤ 19፥19፤ ማር. 3፥31-35፤ 7፥10፤ 10፥19፤ ሉቃ. 8፥19-21፤ 14፥26፤ 18፥20፤28-30፤ ኤፌ. 6፥1-4። “ ‘ጌታ አምላክህ እንዳዘዘህ፥ ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ፥ አባትህንና እናትህን አክብር።
17 # ዘዳ. 4፥41-43፤ 19፥1-13፤ 20፥1—21፥9፤ 21፥18-23፤ ዘፍ. 4፥8-16፤ ዘፀ. 20፥13፤ 21፥12-14፤ ዘኍ. 35፥16-34፤ ኤር. 7፥9፤ ሆሴዕ 4፥2፤ ማቴ. 5፥21-26፤ 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20፤ ያዕ. 2፥11። “ ‘አትግደል።
18 # ዘዳ. 22፥13—23፥1፤ ዘፍ. 20፥1-18፤ 39፥7-20፤ ዘፀ. 20፥14፤ ዘሌ. 18፥20፤ 20፥10፤ 2ሳሙ. 11፥1—12፥25፤ ኤር. 7፥9፤ ሆሴዕ 4፥2፤ ማቴ. 5፥27-30፤ 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20፤ ያዕ. 2፥11። “ ‘አታመንዝር።
19 # ዘዳ. 23፥24፤ 24፥7፤ ዘፍ. 40፥15፤ ዘፀ. 20፥15፤ 21፥16፤ 37፤ 22፥1-3፤ 12፤ ዘሌ. 19፥11፤ 13፤ 1ነገ. 21፥1-19፤ ኤር. 7፥9፤ ሆሴዕ 4፥2፤ ማቴ. 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20። “ ‘አትስረቅ።
20 # ዘዳ. 19፥15-19፤ ዘፀ. 20፥16፤ 23፥1-3፤ ዘሌ. 19፥11፤15-16፤ 1ነገ. 21፥1-19፤ መዝ. 5፥6-10፤ 10፥7-9፤ 27፥12፤ ምሳ. 25፥18፤ 30፥8-10፤ ኤር. 7፥9፤ ሆሴዕ 4፥2፤ ማቴ. 19፥18፤ 26፥59-60፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20። “ ‘በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
21 # ዘዳ. 7፥25፤ ዘፀ. 20፥17፤ ኢያ. 7፥21፤ 2ሳሙ. 11፥1—12፥25፤ 1ነገ. 21፥1-19፤ ኢሳ. 5፥8፤ ሚክ. 2፥2፤ ማቴ. 5፥27-30፤ ሉቃ. 12፥13-21፤ ኤፌ. 5፥5፤ ቈላ. 3፥5። “ ‘የባልጀራህን ሚስት አትመኝ፥ የባልንጀራህንም ቤት እርሻውንም አገልጋዩንና አገልጋይቱን፥ በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከባልንጀራህ ንብረት ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።’
22 # ዘዳ. 4፥13፤ 9፥9-11፤ 17፤ 10፥1-5፤ ዘፀ. 24፥12፤ 31፥18፤ 32፥15-20፤ 34፥1-5። “እነዚህን ቃሎች ጌታ በተራራው ላይ ለጉባኤአችሁ ሁሉ በእሳትና በደመና፥ በድቅድቅ ጨለማው ውስጥ ሆኖ፥ በታላቅ ድምፅ ተናገረ፥ ምንም ምን አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው፥ ለእኔም ሰጠኝ።
የሕዝቡ ፍርሀት
23“ተራራው በእሳት ይነድ በነበረበት ወቅት ከጨለማው ውስጥ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ፥ እናንተ፥ የነገዶቻችሁ አለቆች ሽማግሌዎቻችሁም ሁሉ፥ ወደ እኔ ቀረባችሁ፥ 24#ዘዳ. 4፥33፤36፤ ዘፀ. 20፥19።እንዲህም አላችሁ፦ ‘እነሆ፥ አምላካችን ጌታ ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔር ከሰው ተነጋግሮ ሰውም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል። 25#ዘዳ. 18፥16።ይህች ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና፥ እንግዲያውስ አሁን ለምን እንሞታለን? እኛ የአምላካችንን የጌታን ድምፅ ደግመን ከሰማን እንሞታለን። 26ከሥጋ ለባሽ ሁሉ፥ እኛ እንደ ሰማን፥ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሕያው አምላክን ድምፅ ሰምቶ በሕይወቱ የኖረ ማን ነው? 27#ዘፀ. 20፥19።አንተ ቅረብ፤ አምላካችን ጌታ የሚለውን ሁሉ ስማ፤ አምላካችን ጌታም ለአንተ የሚናገረውን ሁሉ ለእኛ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እናደርገዋለን።’
28 # ዘዳ. 18፥17። “በተናገራችሁኝም ጊዜ ጌታ የእናንተን ቃል ጽምፅ ሰማ፤ ጌታም አለኝ፦ ‘የዚህን ሕዝብ ነገር፥ የተናገሩህን ቃል ድምፅ ሰምቼአለሁ፤ የተናገሩህ ሁሉ መልካም ነው። 29እኔንም ለመፍራት ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ ለመጠበቅ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው ሁልግዜ በኖራቸው! ለእነርሱ ለልጆቻቸውም ለዘለዓለም መልካም በሆነላቸው ነበር! 30አሁንም ሂድና፦ “ወደ ድንኳናችሁ ተመለሱ” ብለህ ንገራቸው። 31#ዘዳ. 4፥1፤45፤ 5፥1፤ 6፥1፤ 17፤ 20፤ 11፥32፤ 12፥1፤ 26፥16።አንተ ግን እዚህ እኔ አጠገብ ቁም፤ እኔ በምሰጣቸው ምድር እነዚህን በመጠበቅ እንዲኖሩ፥ ሕግጋቴን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቶቼን ሁሉ እነግርሃለሁ።’
32“ጌታ አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ለማድረግ ጠንቃቃ ሁኑ፤ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ። 33#ዘዳ. 4፥40።በሕይወት እንድትኖሩ፥ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ ጌታ አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in