ኦሪት ዘዳግም 6
6
ታላቁ ትእዛዝ
1 #
ዘዳ. 4፥1፤45፤ 5፥1፤ 31፤ 6፥17፤ 20፤ 11፥32፤ 12፥1፤ 26፥16። “ጌታ አምላክህ በርስትነት በሚሰጥህ ምድር እንድትጠብቃት እንዳስተምርህ ያዘዘኝ ትእዛዝ፥ ሕግና ሥርዓት ይህች ናት። 2#ዘዳ. 4፥10፤40፤ 5፥29፤ 6፥24፤ 10፥12-13።አንተ ልጅህም የልጅ ልጅህም፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ፤ ጌታ አምላክህን ፈርተህ እኔ ለአንተ ያዘዝሁትን፥ ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ በመጠበቅ፥ ዕድሜህም ይረዝም ዘንድ፤ 3#ዘፀ. 3፥8።እንግዲህ፥ እስራኤል ሆይ፥ ስማ! መልካም እንዲሆንልህ፥ የአባቶችህም አምላክ ጌታ እንደ ተናገረ፥ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር፥ እጅግ እንድትበዛ በጥንቃቄ ጠብቅ።
4 #
ዘዳ. 4፥35፤39፤ 5፥6-10፤ 6፥13-14፤ 10፥17፤ 1ነገ. 8፥60፤ 18፥39፤ 2ነገ. 5፥15፤ 19፥15፤ 19፤ ኢሳ. 44፥6፤ 45፥5-6፤ ማቴ. 22፥37-38፤ ማር. 12፥29-30፤ ሉቃ. 10፥27። “እስራኤል ሆይ፥ ስማ! ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥ 5#ዘዳ. 4፥29፤ 10፥12፤ 11፥13፤ 13፥4፤ 26፥16፤ 30፥2፤ 10፤ 1ሳሙ. 7፥3፤ 2ነገ. 23፥3፤ 25።አንተም ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ኃይልህ ውደድ። 6#ዘዳ. 11፥18-21።ዛሬ እኔ የማዝህ እነዚህን ቃላትም በልብህ አኑር።#ዘዳ. 11፥18፤ 30፥14፤ 32፥46፤ መዝ. 37፥31፤ ምሳ. 3፥3፤ ኢሳ. 51፥7፤ ኤር. 31፥33። 7#ዘዳ. 4፥9-10፤ 6፥20-25፤ 11፥1-7፤ 19፤ 31፥13፤ 32፥46፤ ምሳ. 6፥22።ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም ሆነ፥ ስትነሣም ንገራቸው። 8#ዘዳ. 11፥18፤ ዘፀ. 13፥9፤ 16፤ ምሳ. 3፥3፤ 6፥21።በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፥ በዐይኖችህም መካከል#6፥8 በግንባርህም እንደክታብ ይሁንህ። 9#ዘዳ. 11፥20።በቤትህም መቃኖች፥ በቅጽርህም በሮች ላይ ጻፈው።
ስላለመታዘዝ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ
10 #
ዘዳ. 5፥6-10። “ጌታ አምላክህ ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ፥ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ባስገባህ ጊዜ፥ ያልሠራሃቸውንም ታላቅና መልካም ከተሞች፥#ዘዳ. 1፥8።#ዘዳ. 8፥7-14፤ 32፥11-14፤ ኢያ. 24፥13፤ ነህ. 9፥25። 11ያልሞላሃቸውንም ሀብትን የሞሉ ቤቶች፥ ያልቆፈርካቸውም የተቆፈሩ ጉድጓዶች፥ ያልተከልሃቸውንም የወይን ተክልና የወይራ ዛፎች፥ ስትበላና ስትጠግብ፥ 12#ዘዳ. 5፥6።በዚያን ጊዜ ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ጌታ እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። 13#ዘዳ. 10፥20፤ ኢሳ. 48፥1፤ ኤር. 4፥2፤ 12፥16፤ ማቴ. 4፥10፤ ሉቃ. 4፥8።ጌታ እግዚአብሔርን ፍራ፤ እርሱንም አምልክ፥ በስሙም ማል። 14#ዘዳ. 4፥23-26፤ 8፥19-20፤ 11፥16-17፤ 28፤ 29፥18-28፤ 30፥17-18፤ 2ነገ. 17፥7-18።በዙሪያህ ያሉት አሕዛብ የሚያመልኩአቸውን ሌሎችን አማልክት አትከተል። 15በመካከልህ ያለው ጌታ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነውና፥ የአምላክህ የጌታ ቁጣው እንዳይነድብህ፥ ከምድርም ፊት እንዳያጠፋህ።
16 #
ዘፀ. 17፥1-7፤ መዝ. 95፥8-9፤ ማቴ. 4፥7፤ ሉቃ. 4፥12። “ ‘በማሳህ’ እንደ ፈተናችሁት ጌታ አምላካችሁን አትፈታተኑት። 17ለእናንተ ያዘዘውን የጌታ የአምላካችሁን ምስክሩን፥ ሥርዓቱንም፥ ትእዛዛቱንም አጥብቃችሁ ያዙ። 18መልካም እንዲሆንልህ፥ ጌታም ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብተህ እርሷን እንድትወርስ በጌታ ፊት ትክክልና መልካሙን አድርግ። 19#ዘፀ. 23፥27፤ 34፥11፤ ኢያ. 1—12።ይህም፥ ጌታ እንደሰጠህ ተስፋ፥ ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ በማሳድድ ነው።
20 #
ዘዳ. 6፥6-9። “በሚመጡት ዘመናት ልጅህ፥ ‘አምላካችን ጌታ ያዘዛችሁ ምስክርነቶች፥ ሥርዓት፥ ፍርድስ ምንድነው?’ ብሎ በጠየቀህ ጊዜ፥#ዘፀ. 12፥26፤ 13፥14፤ ኢያ. 4፥6፤ 21። 21#ዘዳ. 26፥5-10።አንተም ልጅህን እንዲህ ትለዋለህ፥ ‘በግብጽ የፈርዖን ባርያዎች ነበርን፤ ጌታም በጽኑ እጅ ከግብጽ አወጣን፥#ዘዳ. 5፥3፤ 6። 22ጌታም በግብጽና በፈርዖን በቤቱም ሁሉ ላይ፥ በዓይናችን እያየን፥ ታላቅና አሰቃቂ፥ ምልክት ተአምራትም አደረገ። 23#ዘዳ. 1፥8።ከዚያም ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር አምጥቶን ሊያስገባንና ሊሰጠን ከዚያ አወጣን። 24#ዘዳ. 4፥1-4፤ 30፥15-20።ዛሬም በሕይወት እንዳኖረን፥ ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን፥ አምላካችንን ጌታን እንድንፈራ፥ እነዚህንም ሥርዓቶች ሁሉ እንድንፈጽም ጌታ አዘዘን። 25እርሱም እንዳዘዘን በጌታ አምላካችን ፊት እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ለመፈጸም ብንጠነቀቅ ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።’
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 6: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: