ወደ ዕብራውያን 1
1
እግዚአብሔር በልጁ አማካይነት እንደ ተናገረ
1እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በብዙ እና በልዩ ልዩ መንገዶች ለአባቶቻችን በነቢያት ተናገረ፤ 2#ጥበ. 7፥22።በእነዚህ በኋለኞቹ ዘመናት ግን፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን፥፥ 3#ጥበ. 7፥25፤26፤ 8፥1።እርሱም የክብሩ ጸዳልና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኀጢአታችንን ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤
ስለ እግዚአብሔር ልጅ ታላቅነት
4ከመላእክት ይልቅ እጅግ የላቀ ስምን በተቀበለ መጠን፥ እንደዚሁ ከእነርሱ እጅግ ልቆ ይበልጣል።
5 #
መዝ. 2፥7፤ 2ሳሙ. 7፥14፤ 1ዜ.መ. 17፥13። ከመላእክትስ፥
“አንተ ልጄ ነህ፥
እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤”
ደግሞም
“እኔ አባት እሆነዋለሁ፥
እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤”
6 #
ዘዳ. 32፥43። ያለው ከቶ ለማን ነው? ደግሞም የበኲር ልጁን ወደ ዓለም በላከ ጊዜ
“የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ፤”
ይላል። 7#መዝ. 103፥4።ስለ መላእክትም
“መላእክቱን ነፋሳት፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ”
ይላል፤ 8#መዝ. 44፥7፤8።ስለ ልጁ ግን፥
“አምላክ ሆይ! ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤
የጽድቅ በትር የመንግሥትህ በትር ነው።
9ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፅንም ጠላህ፤
ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ፤”
ይላል። 10#መዝ. 102፥26-28።እናም፥
“ጌታ ሆይ! አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥
ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤
11እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ፤
ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤
12እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ፤
ይለወጣሉም፤
አንተ ግን አንተ ነህ፤
ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም፤”
13 #
መዝ. 109፥1። ነገር ግን ከመላእክት፥
“ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፤”
ከቶ ለማን ብሎአል? 14#ጦቢ. 12፥14፤15።ታዲያ፥ መላእክት ሁሉ መዳንን ስለሚቀበሉ ሰዎች፥ ለአገልግሎት የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን?
Currently Selected:
ወደ ዕብራውያን 1: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in