ወደ ዕብራውያን 8
8
የአዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት
1 #
መዝ. 109፥1። እንግዲህ ከተናገርነው ነገር ዋናው ይህ ነው፦ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤ 2እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት። 3ሊቀ ካህናት ሁሉ መባንና መሥዋዕትን ሊያቀርብ ይሾማልና፤ ስለዚህ ይህም ካህን የሚያቀርበው አንድ ነገር ሊኖረው ግድ ነው። 4እንግዲህ በምድር ቢኖርስ፥ እንደ ሕግ መባን የሚያቀርቡት ስላሉ፥ ካህን እንኳ ባልሆነም፤ 5#ዘፀ. 25፥40።ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ በነበረ ጊዜ፥ “በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ፤” ብሎት ነበርና፤ እነርሱ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ። 6አሁን ግን በተሻለ ተስፋ ቃል ስለ ተመሠረተ፥ መካከለኛ የሆነበት ኪዳን የተሻለ እንደሆነ ሁሉ፥ የተቀበለውም አገልግሎት ከእነርሱ አገልግሎት ይበልጣል፥፥ 7ፊተኛው ኪዳን ጉድለት ባይኖረው፥ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር።
8 #
ኤር. 31፥31-34። ጉድለት አግኝቶባቸዋልና እንዲህ ይላቸዋል፦
“እነሆ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ኪዳን
የምመሠርትበት ወራት ይመጣል፥ ይላል ጌታ፤
9ከግብጽ ምድር ለማውጣት እጃቸውን በያዝሁበት ቀን
ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤
እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና እኔም ቸል አልኳቸው፤ ይላል ጌታ።
10ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፥ ይላል ጌታ፤
ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤
በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤
እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ፤
እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል።
11እያንዳንዱም ‘ጌታን እወቅ፥’ ብሎ ጐረቤቱን
ወይም ወንድሙን አያስተምርም፤
ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና።
12በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤
ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስብም።”
13“አዲስ” በሚል ጊዜ ፊተኛውን አሮጌ አድርጎታል፤ ስለዚህ ጊዜው ያለፈበትና አሮጌው ነገር ሁሉ የሚጠፋበት ጊዜ ተቃርቧል።
Currently Selected:
ወደ ዕብራውያን 8: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in