መጽሐፈ ምሳሌ 4
4
1ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥
ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፥
2መልካም ትምህርትን እሰጣችኋለሁና፥
ሕጌን አትተዉ።
3እኔም አባቴን የምሰማ ትንሽ ልጅ ነበርሁና፥
በእናቴም ዘንድ እወደድ ነበር።
4ያስተምረኝም ነበር እንዲህም ይለኝ ነበር፦
“ልብህ ቃሌን በጥብቅ ይያዘው፥
ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ።
5ጥበብን አግኝ፥ ማስተዋልን አግኝ፥ አትርሳም፥
ከአፌም ቃል ፈቀቅ አትበል።
6አትተዋት፥ ትጠብቅሃለች፥
ውደዳት፥ ትንከባከብህማለች።
7የጥበብ መጀመሪያ እነሆ፥ ጥበብን አግኝ፥
ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።
8ከፍ ከፍ አድርጋት፥ እርሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፥
ብታቅፋትም ታከብርሃለች።
9በራስህ የጸጋ አክሊልን ታኖራለች፥
የተዋበ ዘውድንም ታበረክትልሃለች።”
10ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ንግግሬንም ተቀበል፥
የሕይወትህም ዓመታት ይበዙልሃል።
11የጥበብን መንገድ አስተማርሁህ፥
በቀናች ጎዳና መራሁህ።
12በሄድህ ጊዜ እርምጃህ አይታገድም፥
ብትሮጥም አትሰናከልም።
13ተግሣጽን ያዝ፥ አትተውም፥
ጠብቀው፥ እርሱ ሕይወትህ ነውና።
14በክፉዎች መንገድ አትግባ፥
በመጥፎ ሰዎችም ጎዳና አትሂድ።
15ከእርሷ ራቅ፥ አትሂድባትም፥
ራቅ በል ተዋትም።
16ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥
ካላሰናከሉም እንቅልፋቸው ይወገዳልና።
17የክፋትን እንጀራ ይበላሉና፥
የግፍንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና።
18የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥
ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል።
19የክፋት መንገድ እንደ ጨለማ ነው፥
እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም።
20ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ
ወደ ቃሎቼም ጆሮህን አዘንብል።
21ከዓይንህ አታርቃቸው፥
በልብህም ውስጥ ጠብቃቸው።
22ለሚያገኙአቸው ሕይወት፥
ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና።
23ከሁሉ አስበልጠህ ልብህን ጠብቅ፥
የሕይወት ምንጭ እርሱ ነውና።
24ጠማማ ንግግርን ከአንተ አስወግድ፥
አሳሳች ቃሎችን ከአንተ አርቅ።
25ዐይኖችህ አቅንተው ይዩ፥
አተኩረው ፊት ለፊት ይመልከቱ።
26 #
ዕብ. 12፥13። የእግርህን መንገድ አቅና፥
አካሄድህም ሁሉ ይጽና።
27ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፥
እግርህንም ከክፉ መልስ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 4: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፈ ምሳሌ 4
4
1ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥
ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፥
2መልካም ትምህርትን እሰጣችኋለሁና፥
ሕጌን አትተዉ።
3እኔም አባቴን የምሰማ ትንሽ ልጅ ነበርሁና፥
በእናቴም ዘንድ እወደድ ነበር።
4ያስተምረኝም ነበር እንዲህም ይለኝ ነበር፦
“ልብህ ቃሌን በጥብቅ ይያዘው፥
ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ።
5ጥበብን አግኝ፥ ማስተዋልን አግኝ፥ አትርሳም፥
ከአፌም ቃል ፈቀቅ አትበል።
6አትተዋት፥ ትጠብቅሃለች፥
ውደዳት፥ ትንከባከብህማለች።
7የጥበብ መጀመሪያ እነሆ፥ ጥበብን አግኝ፥
ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።
8ከፍ ከፍ አድርጋት፥ እርሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፥
ብታቅፋትም ታከብርሃለች።
9በራስህ የጸጋ አክሊልን ታኖራለች፥
የተዋበ ዘውድንም ታበረክትልሃለች።”
10ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ንግግሬንም ተቀበል፥
የሕይወትህም ዓመታት ይበዙልሃል።
11የጥበብን መንገድ አስተማርሁህ፥
በቀናች ጎዳና መራሁህ።
12በሄድህ ጊዜ እርምጃህ አይታገድም፥
ብትሮጥም አትሰናከልም።
13ተግሣጽን ያዝ፥ አትተውም፥
ጠብቀው፥ እርሱ ሕይወትህ ነውና።
14በክፉዎች መንገድ አትግባ፥
በመጥፎ ሰዎችም ጎዳና አትሂድ።
15ከእርሷ ራቅ፥ አትሂድባትም፥
ራቅ በል ተዋትም።
16ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥
ካላሰናከሉም እንቅልፋቸው ይወገዳልና።
17የክፋትን እንጀራ ይበላሉና፥
የግፍንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና።
18የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥
ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል።
19የክፋት መንገድ እንደ ጨለማ ነው፥
እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም።
20ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ
ወደ ቃሎቼም ጆሮህን አዘንብል።
21ከዓይንህ አታርቃቸው፥
በልብህም ውስጥ ጠብቃቸው።
22ለሚያገኙአቸው ሕይወት፥
ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና።
23ከሁሉ አስበልጠህ ልብህን ጠብቅ፥
የሕይወት ምንጭ እርሱ ነውና።
24ጠማማ ንግግርን ከአንተ አስወግድ፥
አሳሳች ቃሎችን ከአንተ አርቅ።
25ዐይኖችህ አቅንተው ይዩ፥
አተኩረው ፊት ለፊት ይመልከቱ።
26 #
ዕብ. 12፥13። የእግርህን መንገድ አቅና፥
አካሄድህም ሁሉ ይጽና።
27ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፥
እግርህንም ከክፉ መልስ።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in