መዝሙረ ዳዊት 10
10
መዝሙር 10 በዕብራይስጥ
1አቤቱ፥ ለምን ርቀህ ቆምህ?
በመከራም ጊዜ ለምን ትሰወራለህ?
2 #
ኢሳ. 32፥7። በክፉዎች ትዕቢት ምስኪኖች ይሰደዳሉ፥
ባሰቡት ተንኰላቸው ተጠመዱ።
3 #
መዝ. 36፥2። ክፉ በነፍሱ ፈቃድ ይኮራልና፥
ስግብግብም ይረግማል፥ ጌታንም ይንቃል።
4 #
መዝ. 14፥1፤ ኢዮብ 22፥13፤ ኢሳ. 29፥15፤ ኤር. 5፥12፤ ሶፎ. 1፥12። ክፉ በትዕቢቱ ጌታን አይፈልገውም፥
በሐሳቡ በሙሉ እግዚአብሔር የለም።
5መንገዱ ሁልጊዜ የጸና#10፥5 የግሪኩ ትርጒም “የረከሰ ነው” ይላል። ነው፥
ፍርድህ ከእርሱ በላይ እጅግ ከፍ ያለ ነው፥
በጠላቶቹ ላይ ግን ይቀልዳል።
6በልቡ፦ “ለልጅ ልጅ አልታወክም ክፉም አያገኘኝም” ይላል።
7 #
ኢሳ. 32፥7፤ ሮሜ 3፥14። አፉ በመርገም፥ በሽንገላና በዐመፃ የተመላ ነው፥
ከምላሱ በታች ተንኰልና ክፋት አሉ።
8 #
መዝ. 11፥2፤ ኢዮብ 24፥14። በመንደሮች#10፥8 በሸምበቆዎች መካከል ሸምቆ ይቀመጣል የሚል ትርጉምም አለ። ሸምቆ ይቀመጣል
ንጹሓንን በስውር ይገድል ዘንድ፥
ዐይኖቹም ወደ ምስኪኑ ይመለከታሉ።
9 #
መዝ. 17፥12፤ ምሳ. 1፥11፤ ኤር. 5፥26። እንደ አንበሳ በዱር በስውር ይሸምቃል፥
ድሀውን ለመንጠቅ ያደባል፥
ድሀውን ይነጥቀዋል በአሽክላውም ይስበዋል።
10ምስኪኑ ይዋረዳል፥ ይጐብጣል፥
በኃያላኑም እጅ ይወድቃል።
11 #
መዝ. 44፥25፤ 64፥6፤ 73፥11፤ 94፥7፤ ሕዝ. 9፥9። በልቡም እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር ረስቶኛል፥
ፈጽሞም እንዳያይ ፊቱን ሰወረ”።
12አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ተነሥ እጅህንም ከፍ ከፍ አድርግ፥
ድሆችን አትርሳ።
13ክፉ ስለምን እግዚአብሔርን ናቀ?
በልቡም፦ “ፈልጎ አያገኘኝም” ይላልና።
14 #
ዘፀ. 22፥21-22፤ መዝ. 31፥8፤ 56፥9፤ 2ነገ. 20፥5፤ ኢሳ. 25፥8፤ ራእ. 7፥17። አየኸው፥ አንተ ክፋትንና ቁጣን ትመለከታለህና
በእጅህ ፍዳውን ለመስጠት፥
ምስኪን እራሱን ለአንተ አሳልፎ ይሰጣል፥
ለድሀ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።
15የክፉዉንና የግፈኛውን ክንድ ሰባብር፥
ምንም እስከማይገኝ ድረስ ክፋቱን ፈልገህ አግኝ።
16 #
መዝ. 145፥13፤ ኤር. 10፥10። ጌታ ለዘለዓለም ንጉሥ ነው፥
አሕዛብ ከምድሩ ይጠፋሉ።
17ጌታ ሆይ የምስኪኖችን ምኞት ሰማህ፥
ልባቸውንም ታጸናለህ፥ ጆሮህንም ታዘነብላለህ፤
18 #
ዘዳ. 10፥18። ፍርዱ ለወላጅ አልባና ለተጨቆነ ይደረግ ዘንድ፥
ሰዎች በምድር ላይ ማሸበራቸውን እንዳይቀጥሉ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 10: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in