YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 112

112
1 # መዝ. 1፥1-2፤ 119፥1-2፤ 128፥1። ሃሌ ሉያ።
ጌታን የሚፈራ፥
ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ብፁዕ ነው።
2ዘሩ በምድር ላይ ኃያል ይሆናል፥
የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።
3ክብርና ሀብት በቤቱ ነው፥
ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።
4 # መዝ. 37፥6፤ 97፥11፤ ምሳ. 13፥9፤ ኢሳ. 58፥10። ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፥
መሓሪ፥ ርኅሩኅና ጻድቅ ነው።
5ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም፥
ነገሩንም በቀና መንገድ ይፈጽማል።
6 # ምሳ. 10፥7፤ ጥበ. 8፥13። ለዘለዓለም አይናወጥም፥
የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል።
7ክፉ ዜናን አይፈራም፥
ልቡ የጸና፥ በጌታም የታመነ ነው።
8በጠላቶቹ ላይ እስኪኮራ ድረስ
ልቡ ጽኑ ነው፥ አይፈራምም።
9 # ምሳ. 22፥9፤ 2ቆሮ. 9፥9። በተነ፥ ለችግረኞችም ሰጠ፥
ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል፥
ቀንዱም#112፥9 ኃይልም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
10ክፉ ሰውም አይቶት ይቈጣል፥
ጥርሱንም ያፋጫል፥ ይቀልጣልም፥
የክፉዎች ምኞት ትጠፋለች።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in