YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 24

24
1የዳዊት መዝሙር#24፥1 የግሪኩ ንባብ “በመጀመሪያ ሰንበት” የሚል ቃል ይጭምራል።
# መዝ. 50፥12፤ 89፥12፤ ዘዳ. 10፥14፤ 1ቆሮ. 10፥26። ምድርና ሞላዋ የጌታ ናቸው፥
ዓለምና በእርሷም የሚኖሩ ሁሉ።
2 # መዝ. 136፥6፤ ኢሳ. 42፥5። እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቶአታልና፥
በፈሳሾችም ላይ አጽንቶአታልና።
3 # መዝ. 15፥1። ወደ ጌታ ተራራ ማን ይወጣል?
በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል?
4 # ማቴ. 5፥8። እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥
ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥
በሽንገላ ያልማለ።
5እርሱ ከጌታ ዘንድ በረከትን
ከመድኃኒቱ አምላክም ጽድቅን ይቀበላል።
6ይህች ትውልድ እርሱን የምትፈልግ ናት፥
የያዕቆብን አምላክ ፊት የምትፈልግ።
7 # መዝ. 118፥19-20። እናንት በሮች#24፥7 የግሪኩ ትርጒም “እናንት መኳንንቶች በሮችን ክፈቱ” ይላል። የዕብራይስጡ ንባብ ግን በሮች ቀና እንዲሉ ወይም ራሳቸውን ከፍ እንዲያደርጉ ትእዛዝ እንደተሰጣቸው ይገልጻል። አባባሉ ምሳሌአዊ ነው። ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፥
የዘለዓለም ደጆችም ተከፈቱ፥
የክብርም ንጉሥ ይግባ።
8ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?
ጌታ ነው፥ ብርቱና ኃያል፥
ጌታ ነው፥ በሰልፍ ኃያል።
9እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፥
የዘለዓለም ደጆችም ይከፈቱ፥
የክብርም ንጉሥ ይግባ።
10ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?
የሠራዊት ጌታ
እርሱ የክብር ንጉሥ ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in