መዝሙረ ዳዊት 27
27
1ሳይቀባ፥ የዳዊት መዝሙር።
#
መዝ. 18፥29፤ 36፥10፤ 43፥3፤ ኢሳ. 10፥17፤ ሚክ. 7፥8። ጌታ ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፥
የሚያስፈራኝ ማን ነው?
ጌታ የሕይወቴ ከለላዋ ነው፥
የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?
2 #
መዝ. 14፥4። ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥
ሥጋዬን ለመብላት በቀረቡ ጊዜ፥
እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ።
3ሠራዊትም ቢከብበኝ ልቤ አይፈራም፥
ጦርነትም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ።
4 #
መዝ. 23፥6፤ 61፥5። ጌታን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ፥
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት እኖር ዘንድ፥
ጌታን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥
መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
5 #
መዝ. 31፥21። በመከራ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥
በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥
በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።
6እነሆ፥ አሁን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፥
በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን ሠዋሁ፥
ለጌታ እቀኛለሁ እዘምርለትማለሁ።
7አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ፥
ማረኝና አድምጠኝ።
8 #
መዝ. 24፥6፤ ሆሴዕ 5፥15። “ፊቴን እሹት” የሚለውን ቃልህን በልቤ አሰብኩኝ፦
አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ።
9ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥
ተቈጥተህ ከባርያህ ፈቀቅ አትበል፥
ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥
የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተወኝ።
10 #
ኢሳ. 49፥15። አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥
ጌታ ግን ተቀበለኝ።
11 #
መዝ. 25፥4፤ 86፥11። አቤቱ፥ መንገድህን አስተምረኝ፥
በጠላቶቼም ምክንያት በቀና መንገድ ምራኝ።
12የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና
ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ።
13 #
መዝ. 116፥9፤ ኢሳ. 38፥11። የጌታን ቸርነት በሕያዋን ምድር
እንደማይ አምናለሁ።
14በጌታ ተስፋ አድርግ፥
በርታ፥ ልብህም ይጽና፥
በጌታ ተስፋ አድርግ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 27: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መዝሙረ ዳዊት 27
27
1ሳይቀባ፥ የዳዊት መዝሙር።
#
መዝ. 18፥29፤ 36፥10፤ 43፥3፤ ኢሳ. 10፥17፤ ሚክ. 7፥8። ጌታ ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፥
የሚያስፈራኝ ማን ነው?
ጌታ የሕይወቴ ከለላዋ ነው፥
የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?
2 #
መዝ. 14፥4። ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥
ሥጋዬን ለመብላት በቀረቡ ጊዜ፥
እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ።
3ሠራዊትም ቢከብበኝ ልቤ አይፈራም፥
ጦርነትም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ።
4 #
መዝ. 23፥6፤ 61፥5። ጌታን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ፥
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት እኖር ዘንድ፥
ጌታን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥
መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
5 #
መዝ. 31፥21። በመከራ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥
በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥
በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።
6እነሆ፥ አሁን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፥
በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን ሠዋሁ፥
ለጌታ እቀኛለሁ እዘምርለትማለሁ።
7አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ፥
ማረኝና አድምጠኝ።
8 #
መዝ. 24፥6፤ ሆሴዕ 5፥15። “ፊቴን እሹት” የሚለውን ቃልህን በልቤ አሰብኩኝ፦
አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ።
9ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥
ተቈጥተህ ከባርያህ ፈቀቅ አትበል፥
ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥
የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተወኝ።
10 #
ኢሳ. 49፥15። አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥
ጌታ ግን ተቀበለኝ።
11 #
መዝ. 25፥4፤ 86፥11። አቤቱ፥ መንገድህን አስተምረኝ፥
በጠላቶቼም ምክንያት በቀና መንገድ ምራኝ።
12የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና
ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ።
13 #
መዝ. 116፥9፤ ኢሳ. 38፥11። የጌታን ቸርነት በሕያዋን ምድር
እንደማይ አምናለሁ።
14በጌታ ተስፋ አድርግ፥
በርታ፥ ልብህም ይጽና፥
በጌታ ተስፋ አድርግ።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in