YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 47

47
1ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
2 # መዝ. 89፥16፤ ሶፎ. 3፥14። አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥
በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።
3 # መዝ. 95፥3፤ ዘፀ. 15፥18፤ ኢሳ. 24፥23፤ 52፥7። ጌታ ልዑል ግሩምም ነውና፥
በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና።
4 # መዝ. 2፥8። አሕዛብን ከእኛ በታች፥
ወገኖችንም ከእግራችን በታች አስገዛልን።
5 # ኢሳ. 58፥14። ለሚወደው ለያዕቆብ ኩራት
የሆነችውን ርስታችንን እርሱ ይመርጥልናል።
6 # መዝ. 24፥8፤ 10፤ 68፥18-19፤ 98፥6። አምላክ በእልልታ፥
ጌታ በመለከት ድምፅ ዐረገ።
7ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፥
ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ።
8 # መዝ. 72፥11፤ 93፥1፤ 96፥10፤ 97፥1፤ 99፥1፤ ኤር. 10፥7። እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፥
በጥበብ ዘምሩ።
9እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ፥
እግዚአብሔር በተቀደሰው ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።
10 # መዝ. 89፥19፤ ዘፀ. 3፥6፤ ኢሳ. 2፥2-4። የአሕዛብ አለቆች፥
እንደ አብርሃም አምላክ ሕዝብ ተሰበሰቡ፥
የምድር ጋሻዎች የእግዚአብሔር ናቸውና፤ እርሱም እጅጉን ከፍ ብሏል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in