መዝሙረ ዳዊት 50
50
1የአሳፍ መዝሙር።
#
ዘዳ. 10፥17፤ ኢያ. 22፥22። የአማልክት አምላክ#50፥1 እጅግ ኃያል አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፥
ከፀሓይም መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራት።
2 #
መዝ. 48፥2። ከጽዮን፥ ከውበት ሙላቱ
እግዚአብሔር ያበራል።
3 #
መዝ. 97፥3፤ ዳን. 7፥10። አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፥
እሳት በፊቱ ይቃጠላል፥
በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ ነፋስ አለ።
4በላይ ያለውን ሰማይን
ምድርንም እንዲሁ በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል፥
5“ከእኔ ጋር በመሥዋዕት ኪዳን ያቆሙትን
ቅዱሳኑን ሰብስቡልኝ” ይላል።
6 #
መዝ. 19፥2፤ 97፥6። ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥
እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።
7ሕዝቤ፥ ስማኝ፥ ልንገርህ፥
እስራኤልም፥ ስማኝ፥ ልመስክርብህ፥
አምላክስ እኔ አምላክህ ነኝ።
8ስለ ቁርባንህ አልወቅስህም፥
የሚቃጠል መሥዋዕትህ ሁልጊዜ በፊቴ ነው።
9 #
መዝ. 69፥32፤ አሞጽ 5፥21-22። ከቤትህ ፍሪዳን
ከመንጋህም አውራ ፍየልን አልወስድም፥
10የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ
በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና።
11የሰማይን አዕዋፍ ሁሉ አውቃለሁ፥
የምድረ በዳ አራዊትም በእኔ ዘንድ ናቸው።
12 #
መዝ. 24፥1፤ 89፥12፤ ዘዳ. 10፥14፤ 1ቆሮ. 10፥26። ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥
ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና።
13የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን?
የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን?
14 #
ዕብ. 13፥15። ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥
ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፥
15 #
መዝ. 77፥3። በመከራ ቀን ጥራኝ፥
አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።
16ክፉውን ግን እግዚአብሔር አለው፦
ለምን አንተ ሕጌን ትናገራለህ?
ኪዳኔንም በአፍህ ለምን ትይዛለህ?
17አንተስ ተግሣጼን ጠላህ፥
ቃሎቼንም ወደ ኋላህ ጣልህ።
18ሌባውን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ጋር ትሮጥ ነበር
እድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ።
19አፍህ ክፋትን አበዛ፥
አንደበትህም ሽንገላን ተበተበ።
20ተቀምጠህ በወንድምህን ላይ ክፉን ተናገርህ፥
የእናትህንም ልጅ አማህ።
21ይህን አድርገህ ዝም አልሁህ፥
እኔ እንደ አንተ የምሆን መሰለህ፥
እዘልፍሃለሁ በፊትህም እቆማለሁ።
22እግዚአብሔርን የምትረሱ እናንተ፥ ይህን አስተውሉ፥
አለዚያ ግን ስበታትናችሁ የሚያድንም የለም።
23 #
መዝ. 91፥16። ምስጋናን የሚሠዋ ያከብረኛል፥
የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 50: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መዝሙረ ዳዊት 50
50
1የአሳፍ መዝሙር።
#
ዘዳ. 10፥17፤ ኢያ. 22፥22። የአማልክት አምላክ#50፥1 እጅግ ኃያል አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፥
ከፀሓይም መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራት።
2 #
መዝ. 48፥2። ከጽዮን፥ ከውበት ሙላቱ
እግዚአብሔር ያበራል።
3 #
መዝ. 97፥3፤ ዳን. 7፥10። አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፥
እሳት በፊቱ ይቃጠላል፥
በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ ነፋስ አለ።
4በላይ ያለውን ሰማይን
ምድርንም እንዲሁ በሕዝቡ ለመፍረድ ይጠራል፥
5“ከእኔ ጋር በመሥዋዕት ኪዳን ያቆሙትን
ቅዱሳኑን ሰብስቡልኝ” ይላል።
6 #
መዝ. 19፥2፤ 97፥6። ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥
እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።
7ሕዝቤ፥ ስማኝ፥ ልንገርህ፥
እስራኤልም፥ ስማኝ፥ ልመስክርብህ፥
አምላክስ እኔ አምላክህ ነኝ።
8ስለ ቁርባንህ አልወቅስህም፥
የሚቃጠል መሥዋዕትህ ሁልጊዜ በፊቴ ነው።
9 #
መዝ. 69፥32፤ አሞጽ 5፥21-22። ከቤትህ ፍሪዳን
ከመንጋህም አውራ ፍየልን አልወስድም፥
10የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ
በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና።
11የሰማይን አዕዋፍ ሁሉ አውቃለሁ፥
የምድረ በዳ አራዊትም በእኔ ዘንድ ናቸው።
12 #
መዝ. 24፥1፤ 89፥12፤ ዘዳ. 10፥14፤ 1ቆሮ. 10፥26። ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥
ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና።
13የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን?
የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን?
14 #
ዕብ. 13፥15። ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥
ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፥
15 #
መዝ. 77፥3። በመከራ ቀን ጥራኝ፥
አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።
16ክፉውን ግን እግዚአብሔር አለው፦
ለምን አንተ ሕጌን ትናገራለህ?
ኪዳኔንም በአፍህ ለምን ትይዛለህ?
17አንተስ ተግሣጼን ጠላህ፥
ቃሎቼንም ወደ ኋላህ ጣልህ።
18ሌባውን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ጋር ትሮጥ ነበር
እድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ።
19አፍህ ክፋትን አበዛ፥
አንደበትህም ሽንገላን ተበተበ።
20ተቀምጠህ በወንድምህን ላይ ክፉን ተናገርህ፥
የእናትህንም ልጅ አማህ።
21ይህን አድርገህ ዝም አልሁህ፥
እኔ እንደ አንተ የምሆን መሰለህ፥
እዘልፍሃለሁ በፊትህም እቆማለሁ።
22እግዚአብሔርን የምትረሱ እናንተ፥ ይህን አስተውሉ፥
አለዚያ ግን ስበታትናችሁ የሚያድንም የለም።
23 #
መዝ. 91፥16። ምስጋናን የሚሠዋ ያከብረኛል፥
የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።
Currently Selected:
:
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in