YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 87

87
1የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር።
# መዝ. 76፥2-3፤ 78፥68-69። መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፥
2ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥
ጌታ የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል።
3የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ ስለ አንቺ የተከበረ ነገር ይባላል።
4ከሚያውቁኝ መሃል ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ፥
እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን፥ ጢሮስና የኢትዮጵያም ሕዝብ፥
እነዚህ በዚያ ተወለዱ።
5 # መዝ. 48፥9፤ ገላ. 4፥26። ስለ ጽዮን ሰው እንዲህ ይላል፥
“ሰው ሁሉ በውስጥዋ ተወለደ#87፥5 የሰባ ሊቃናት (ግሪኩ) “እናት ጽዮን” ሲል ግዕዙ ደግሞ “እናታችን ጽዮን” ይላል።”፥
እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።
6 # ኢሳ. 4፥3። ጌታ እያለ ሕዝቦችን ይመዘግባል።
“እገሌ በውስጥዋ ተወለደ” እያለ፥
7 # መዝ. 68፥26፤ 149፥3። በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል።#87፥7 መኳንንት፥ እንደ ሕጻናት፥ ሁሉም መኖርያቸውን በአንቺ ላይ ያደርጋሉ፥ የሚል ትርጒም የሚሰጡ አሉ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in