መዝሙረ ዳዊት 92
92
1በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር።
2 #
መዝ. 33፥1፤ 147፥1። ጌታን ማመስገን መልካም ነው፥
ልዑል ሆይ፥ ለስምህም ዝማሬ ማቅረብ፥
3በማለዳ ምሕረትን፥
በሌሊትም እውነትህን ማውራት
4 #
መዝ. 33፥2፤ 144፥9። ዐሥር አውታር ባለው በበገና፥
ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ።
5አቤቱ፥ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና፥
በእጅህም ሥራ ደስ ይለኛልና።
6 #
መዝ. 131፥1፤ 139፥6፤17፤ ጥበ. 13፥1፤ 17፥1። አቤቱ፥ ሥራህ እንዴት ትልቅ ነው!
ሐሳብህም እንዴት ጥልቅ ነው!
7የማያስተውል ሰው አያውቅም።
አላዋቂ አይረዳውም።
8 #
መዝ. 37፥35። ኃጢአተኞች እንደ ሣር ቢበቅሉ
ዓመፃ የሚያደርጉ ሁሉ ቢለመልሙ፥
ለዘለዓለም ዓለም እንደሚጠፉ ነው።
9አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘለዓለም ልዑል ነህ፥
10 #
መዝ. 68፥1-2፤ 125፥5። አቤቱ፥ እነሆ፥ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፥
ዓመፃንም የሚሠሩ ሁሉ ይበተናሉና።
11 #
መዝ. 23፥5፤ መዝ. 75፥11፤ ዘዳ. 33፥17። እንደ ጐሽ አጠነከርከኝ#92፥11 ዕብራይስጡ “እንደ ጐሽ ቀንድ ቀንዴን ከፍ ከፍ አደረግህ ይላል።”፥
በአዲስ ዘይትም ቀባኸኝ።
12 #
መዝ. 91፥8። ዓይኔም ጠላቶቼን ቃኘች፥
ጆሮዬም በእኔ ላይ የተነሡትን ክፉዎች ሰማች።
13 #
መዝ. 1፥3፤ 52፥10፤ ኤር. 17፥8። ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል፥
እንደ ሊባኖስ ዝግባም ያድጋል።
14በጌታ ቤት ውስጥ ተተክለዋል፥
በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ።
15ያንጊዜ ገና በሽምግልናም ያፈራሉ
ገና ወተታማና አርንጓዴ ሆነው ይኖራሉ።
16 #
ዘዳ. 32፥4። ጌታ ትክክለኛ እንደሆነ ይነግራሉ፥
ዓለቴ ነው፤ በእርሱም ዘንድ ዓመፃ የለም።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 92: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in