ወደ ሮሜ ሰዎች 10
10
1ወንድሞች ሆይ! የልቤ መልካም ምኞትና እግዚአብሔርንም የምለምነው እስራኤላውያን እንዲድኑ ነው። 2ለእግዚአብሔር ቅንዓት እንዳላቸው እመሰክርላቸዋለሁ ነገር ግን ቅንአታቸው በእውቀት ላይ የተመሠረተ አይደለም። 3የእግዚአብሔርን ጽድቅ ባለማወቅ፥ የራሳቸውንም ጽድቅ ለመመሥረት በመፈለግ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም። 4የሚያምን ሁሉ እንዲጸድቅ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።
መዳን ለሁሉም
5 #
ዘሌ. 18፥5። ሙሴ በሕግ ስለ ሆነው ጽድቅ ሲጽፍ “እነዚህን የሚፈጽም ሰው በእነርሱ ይኖራል” ይላል። 6#ዘዳ. 30፥12-14።ከእምነት የሆነው ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፥ “በልብህ ‘ወደ ሰማይ ማን ይወጣል?’ አትበል፤” ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ 7ወይም “በልብህ ‘ወደ ጥልቁስ ማን ይወርዳል?’ አትበል፤” ይህም ክርስቶስን ከሙታን ለማስነሣት ነው። 8ነገር ግን ምን ይላል? ቃሉ በአጠገብህ ነው፤ በአፍህና በልብህም ነው፤ የምንሰብከው የእምነት ቃል ይህ ነው። 9ምክንያቱም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር፥ እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ፤ 10ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል፥ በአፉም መስክሮ ይድናልና። 11#ኢሳ. 28፥16።መጽሐፍ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም” ይላልና። 12በአይሁዳዊና በግሪካዊ መካከል ልዩነት የለምና፤ ያው ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ 13#ኢዩ. 2፥32።“የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።”
14ታዲያ ያላመኑበትን እንዴት ይጠሩታል? ያልሰሙትንስ እንዴት ያምኑታል? ያለ ሰባኪስ እንዴት ሊሰሙ ይችላሉ? 15#ኢሳ. 52፥7።ካልተላኩስ እንዴት ይሰብካሉ? “መልካሙን ዜና የሚያበሥሩ እግሮቻቸው እንዴት ውብ ናቸው!” ተብሎ እንደተጻፈው ነው። 16#ኢሳ. 53፥1።ነገር ግን ሁሉም ለምሥራቹ ቃል አልታዘዙም። ኢሳይያስ “ጌታ ሆይ! የተናገርነውን ማን አመነ?” ብሏልና። 17ስለዚህ እምነት የሚመጣው ከመስማት ነው፤ መስማትም በክርስቶስ ቃል በኩል ነው።
18 #
መዝ. 19፥4። ነገር ግን አልሰሙም ወይ? እላለሁ፥ በእርግጥም ሰምተዋል፤
“ድምፃቸው በምድር ሁሉ ላይ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።”
19 #
ዘዳ. 32፥21። ነገር ግን እስራኤል አላወቀምን? እላለሁ። ሙሴ አስቀድሞ
“ሕዝብ ባልሆነው አስቀናችኋለሁ፤ በማያስተውል ሕዝብም
አስቆጣችኋለሁ”
ብሏል። 20#ኢሳ. 65፥1።ስለዚህ ኢሳይያስም በድፍረት
“ላልፈለጉኝ ተገኘሁ፤ ላልጠየቁኝም ተገለጥሁ”
አለ። 21#ኢሳ. 65፥2።ስለ እስራኤል ግን “ወደማይታዘዝና ወደሚቃወም ሕዝብ ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ” ይላል።
Currently Selected:
ወደ ሮሜ ሰዎች 10: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in