ወደ ሮሜ ሰዎች መግቢያ
መግቢያ
የሐዋርያው የጳውሎስ መልእክት ወደ ሮም ሰዎች የተጻፈው ጳውሎስ በሮም የምትገኘውን ቤተ ክርስቲያን ለመጐብኘት ዕቅድ ስለ ነበረው፥ ተዘጋጅተው እንዲጠብቁት ለማድረግ ነው። የጳውሎስ ዕቅድ በሮም ከሚገኙት ምእመናን ጋር ለጥቂት ጊዜ ከሠራ በኋላ በእነርሱ ረዳትነት ወደ ስፔን ለመሄድ ነበር፤ ስለ ክርስትና እምነት የተረዳውንና ክርስቲያኖች በሕይወታቸው ተግባራዊ ስለሚያደርጉበትም የክርስትና ትምህርት ሁኔታ በመዘርዘር ጽፎአል።
ጳውሎስ በሮም ለሚገኙት ምእመናን ሰላምታውን ካስተላለፈና እንደሚጸልይላቸውም ተስፋ ከሰጣቸው በኋላ የመልእክቱን ማእከላዊ ሐሳብ ይገልጻል፤ እርሱም “‘ጻድቅ በእምነት ይኖራል’ ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና” የሚለው ቃል መሆኑን ያመለክታል።
ከዚህ በኋላ ጳውሎስ ይህንኑ ሐሳብ በማስፋፋት ይጽፋል፤ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ፥ ሰዎች ሁሉ የኃጢአት ተገዢዎች ስለ ሆኑ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ይኖርባቸዋል፤ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ሊታረቁ የሚችሉትም በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ነው፤ ከእግዚአብሔር ጋር የሚመሠርቱት አዲስ ኅብረት አዲስ ሕይወት ስለ መሆኑ ጳውሎስ በሰፊው ያስረዳል። አማኝ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ይኖረዋል፤ በእግዚአብሔርም መንፈስ አማካይነት ከኃጢአትና ከሞት ኃይል ነጻ ይወጣል፤ ከምዕራፍ 5 እስከ 8 ጳውሎስ የእግዚአብሔር ሕግና በአማኞች ሕይወት የሚሠራው የመንፈስ ኃይል ምን እንደሆነ ይገልጣል፤ ከዚህም በመቀጠል ጳውሎስ “እግዚአብሔር ለሰው ዘር ባለው ዕቅድ ውስጥ አይሁድና አሕዛብ እንዴት ሊጣመሩ ይችላሉ?” ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል።
አይሁድ ኢየሱስን ሳይቀበሉ መቅረታቸው ለጳውሎስ ትልቅ የሐዘን ምክንያት ነበር። ይሁን እንጂ አይሁድ ኢየሱስን የሚቀበሉበት ጊዜ እንደሚመጣ ጳውሎስ ያምናል፤ በመጨረሻ ጳውሎስ የክርስትናን ሕይወት እንዴት መኖር እንደሚገባ፥ በተለይም ምእመናን እርስ በርስ ባላቸው ግንኙነት የፍቅርን መንገድ እንዴት መከተል እንደሚገባቸው ያስረዳል፤ እግዚአብሔርን ስለ ማገልገል፥ ክርስቲያኖች ስለ አገራቸውና እርስ በእርስ ስለሚኖራቸው ኃላፊነትና በኅሊና ምክንያት ስለሚነሡ ጥያቄዎችም በመዘርዘር ይገልጻል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የመጽሐፉ ፍሬ ሐሳብ መግቢያ (1፥1-17)
መዳን ለሰው ልጅ አስፈላጊ መሆኑ (1፥18—3፥20)
የእግዚአብሔር የማዳኑ መንገድ (3፥21—4፥25)
በክርስቶስ የሚገኝ አዲስ ሕይወት (5፥1—8፥39)
እስራኤል በእግዚአብሔር ዕቅድ (9፥1—11፥36)
ክርስቲያናዊ ምግባር (12፥1—15፥13)
ማጠቃለያና ሰላምታ (15፥14—16፥27)
ምዕራፍ
Currently Selected:
ወደ ሮሜ ሰዎች መግቢያ: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: