መጽሐፈ ሩት መግቢያ
መግቢያ
መጽሐፈ ሩት የተሰየመው ለምራቷ ለኑኃሚን መሐላ በማድረግ ለእስራኤላውያን ራሷን በሰጠችው እና የሞዓብ አገር ተወላጅ በሆነችው በሩት ነው። ሩት ባልዋ በሞተ ጊዜ እስራኤላዊት ለሆነችው ምራቷ እጅግ አስደናቂ የሆነ ታማኝነት ታሳያታለች፤ እንዲሁም ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር ያድርባታል፤ በመጨረሻም ከድሮ ባልዋ ዘመዶች መካከል እስራኤላዊ የነበረውን የቤተልሔሙን ቦዔዝን ታገባለች። በዚህም ጋብቻ አማካይነት የእስራኤል ታላቅ ንጉሥ ለነበረው ዳዊት ቅድመ አያት የመሆንን ዕድል ትጐናጸፋለች፤ ወደ ክርስቶስ በሚመራን መሢሓዊ መስመር ላይም እናገኛታለን (ማቴ 1፥5)።
መጽሐፈ ሩት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በማለፍ ለእግዚአብሔር ታማኝ በሆነ ማኅበረሰብ ውስጥ ተሳታፊ የሚሆኑ የሰው ልጆችን ፍቅርና ታማኝነትን የሚያሳይ ነው። የታሪኩም መሪ ሐሳብ በኃላፊነትና በፍቅር የሚደረግ ውሳኔ ላይ ያውጠነጠነ ነው፤ የሩት ታማኝነትና (2፥11)፥ ልግስናዋ (1፥15-17፤ 2፥2-7) የሚደነቅ ነው፤ መጽሐፈ ሩት እንደ ሰንሰለት በተያያዙ ጠቃሚ ክንዋኔዎች ውስጥ እያንዳንዱን እርምጃ እግዚአብሔር ሲባርክ፥ ሩትም ለትክክለኛ ፍርድ ስትል ኃላፊነትን ስትወስድና ቁርጥ ፈቃደኝነት ስታሳይ ይተርካል። በመጽሐፈ መሳፍንት ያሉት ታሪኮች የእግዚአብሔር ሕዝብ ከእግዚአብሔር በመራቃቸው የደረሰባቸውን ጥፋት ያሳያሉ፤ ሩትን “ሞዓባዊት” በሚል ስያሜ የሚጠራው ይህ መጽሐፍ ደግሞ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ፊቷን የመለሰች አንዲት ባዕድ ሴት በረከት ማግኘቷን፥ ታማኞች ከሆኑት ሕዝቡ መካከል አንዷ ልትሆን መብቃቷን እና የመዳን ታሪክ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ያለው መሆኑን ያለማቋረጥ የሚያስታውስ ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የናዖሚ ከሩት ጋር ወደ ቤተልሔም መመለስ (1፥1-22)
የሩትና የቦዔዝ መገናኘት (2፥1—3፥18)
የቦዔዝ ሩትን ማግባት (4፥1-22)
ምዕራፍ
Currently Selected:
መጽሐፈ ሩት መግቢያ: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: