YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 1

1
1በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሐዋ​ርያ ሊሆን ከተ​ጠራ ከጳ​ው​ሎ​ስና ከወ​ን​ድ​ማ​ችን ከሶ​ስ​ቴ​ንስ፥ 2በቆ​ሮ​ን​ቶስ ሀገር ላለች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ለከ​በ​ሩና ቅዱ​ሳን ለተ​ባሉ የእ​ነ​ር​ሱና የእኛ ጌታ የሆ​ነ​ውን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ስም በየ​ስ​ፍ​ራው ለሚ​ጠሩ ሁሉ፥ 3ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን።
4ስለ እና​ንተ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ለእ​ና​ንተ ስለ​ተ​ሰ​ጣ​ችሁ ጸጋ ዘወ​ትር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ። 5በአ​ነ​ጋ​ገር ሁሉ፥ በዕ​ው​ቀ​ትም ሁሉ ከብ​ራ​ች​ሁ​በ​ታ​ልና። 6ለክ​ር​ስ​ቶስ መመ​ስ​ከሬ በእ​ና​ንተ እንደ ጸና መጠን። 7ፍጹ​ማ​ንም እን​ድ​ት​ሆኑ#“ፍጹ​ማ​ንም እን​ድ​ት​ሆኑ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም መም​ጣት ተስፋ አድ​ር​ጋ​ችሁ ፍጹም ጸጋን እን​ዳ​ታጡ፥ 8እር​ሱም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቀን ያለ ነውር ትገኙ ዘንድ እስከ ፍጻሜ ያጸ​ና​ች​ኋል። 9ከልጁ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የጠ​ራ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው።
መለ​ያ​የት እን​ደ​ማ​ይ​ገባ
10ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን! አንድ ቃል እን​ድ​ት​ና​ገሩ፥ እን​ዳ​ታ​ዝኑ፥ ፍጹ​ማ​ንም እን​ድ​ት​ሆኑ፥ ሁላ​ች​ሁ​ንም፦ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ት​ለ​ያ​ዩም አንድ ልብና አንድ አሳብ ሆና​ችሁ ኑሩ። 11ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ! እን​ደ​ም​ት​ጣ​ሉና እን​ደ​ም​ት​ከ​ራ​ከሩ ከቀ​ሎ​ኤስ ወገ​ኖች ስለ እና​ንተ ነገ​ሩኝ። 12#የሐዋ. 18፥24። እነሆ፥ እርስ በር​ሳ​ችሁ፥ “እኔ የጳ​ው​ሎስ ነኝ፤ እኔ የአ​ጵ​ሎስ ነኝ፤ እኔ የኬፋ ነኝ፤ እኔ የክ​ር​ስ​ቶስ ነኝ” የም​ት​ሉ​ትን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ። 13ክር​ስ​ቶስ ተከ​ፍ​ሎ​አ​ልን? ወይስ በውኑ ጳው​ሎስ ስለ እና​ንተ ተሰ​ቅ​ሎ​አ​ልን? ወይስ በጳ​ው​ሎስ ስም ተጠ​ም​ቃ​ች​ኋ​ልን? 14#የሐዋ. 18፥8፤ 19፥29፤ ሮሜ 16፥23። ከቀ​ር​ስ​ጶ​ስና ከጋ​ይ​ዮስ በቀር ከእ​ና​ንተ ወገን ሌላ ስላ​ላ​ጠ​መ​ቅሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለሁ። 15በእ​ርሱ ስም ተጠ​መ​ቅን የሚል እን​ዳ​ይ​ኖር። 16#1ቆሮ. 16፥15። ነገር ግን የእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስን ቤተ ሰብእ አጥ​ም​ቄ​አ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ ሌላም ያጠ​መ​ቅ​ሁት እን​ዳለ አላ​ው​ቅም።
ስለ መስ​ቀል
17ክር​ስ​ቶስ ወን​ጌ​ልን ለመ​ስ​በክ እንጂ ለማ​ጥ​መቅ አል​ላ​ከ​ኝ​ምና፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስን መስ​ቀ​ሉን ከንቱ እን​ዳ​ና​ደ​ርግ ነገ​ርን በማ​ራ​ቀቅ አይ​ደ​ለም። 18የመ​ስ​ቀሉ ነገር በሚ​ጠፉ ሰዎች ዘንድ ስን​ፍና ነውና፥ ለም​ን​ድ​ነው ለእኛ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው። 19#ኢሳ. 29፥14። መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “እኔ የጥ​በ​በ​ኞ​ችን ጥበብ አጠ​ፋ​ለሁ፤ የመ​ካ​ሪ​ዎ​ች​ንም ምክር እን​ቃ​ለሁ።” 20#ኢዮብ 12፥17፤ ኢሳ. 19፥12፤ 33፥18፤ 44፥25። እን​ግ​ዲህ ጥበ​በኛ ማን ነው? ጸሓ​ፊስ ማን ነው? ይህን ዓለ​ምስ የሚ​መ​ረ​ም​ረው ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ዓለም ጥበብ ስን​ፍና አላ​ደ​ረ​ገ​ው​ምን? 21ሰዎች በጥ​በ​ባ​ቸው በማ​ያ​ው​ቁት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ ስን​ፍና በሚ​መ​ስ​ላ​ቸው ትም​ህ​ርት ያመ​ኑ​ትን ሊያ​ድ​ና​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወድ​ዶ​አ​ልና። 22አይ​ሁድ ምል​ክ​ትን ይጠ​ይ​ቃሉ፤ የጽ​ርዕ ሰዎ​ችም ጥበ​ብን ይሻሉ። 23እኛ ግን የተ​ሰ​ቀ​ለ​ውን ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ሰ​ብ​ካ​ለን፤ ይህም ለአ​ይ​ሁድ ማሰ​ና​ከያ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ስን​ፍና ነው። 24ለእኛ ለዳ​ን​ነው#ግሪኩ “ለተ​ጠ​ሩት ግን ...” ይላል። ግን ከአ​ይ​ሁድ፥ ከአ​ረ​ሚም ብን​ሆን ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጥበብ ነው። 25የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስን​ፍና ከሰው ይልቅ ይጠ​በ​ባ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበ​ረ​ታ​ልና።
26ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን! እን​ግ​ዲህ እን​ዴት እንደ ተጠ​ራ​ችሁ እዩ፤ በሥጋ እጅግ ብዙ​ዎች ዐዋ​ቂ​ዎች አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና፥ ብዙ​ዎች ኀያ​ላ​ንም አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና፥ በዘ​መ​ድም ብዙ​ዎች ደጋ​ጎች አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና። 27ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​በ​ኞ​ችን ሊያ​ሳ​ፍር የዚ​ህን ዓለም ሰነ​ፎች መረጠ፤ ኀይ​ለ​ኞ​ች​ንም ያሳ​ፍር ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ዓለም ደካ​ሞች መረጠ። 28አለን የሚ​ሉ​ት​ንም ያሳ​ፍር ዘንድ ዘመድ የሌ​ላ​ቸ​ው​ንና የተ​ና​ቁ​ትን፥ ከቍ​ጥ​ርም ያል​ገ​ቡ​ትን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መረጠ። 29ሰው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዳ​ይ​መካ። 30እና​ን​ተም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ርሱ ናችሁ፤ በእ​ር​ሱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ጽድ​ቅን፥ ቅድ​ስ​ና​ንና ቤዛ​ነ​ትን አገ​ኘን። 31#ኤር. 9፥24። መጽ​ሐፍ እንደ አለው ይሆን ዘንድ “የሚ​መ​ካስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመካ።”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in