ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 14
14
በቋንቋ ስለ መናገርና ስለ መተርጐም ሀብት
1ፍቅርን ተከተሏት፤ ለመንፈሳዊ ስጦታ፥ ይልቁንም ትንቢት ለመናገር ተፎካከሩ። 2በቋንቋ የሚናገር ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው የሚናገር አይደለም። የሚናገረውን የሚሰማው የለምና፥ ነገር ግን በመንፈስ ምሥጢርን ይናገራል። 3ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽና ለመምከር፥ ለማረጋጋትም ለሰው ይናገራል። 4በቋንቋ የሚናገር ራሱን ያንጻል፤ የሚተረጕም ግን የክርስቲያን ማኅበርን ያንጻል። 5ሁላችሁም በቋንቋ ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ይልቁንም ትንቢት ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ሳይተረጕም በቋንቋ ከሚናገር ይልቅ ትንቢት የሚናገር እጅግ ይበልጣልና፤ ቢተረጕም ግን ማኅበሩን ያንጻል።
6አሁንም ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ መጥቼ በማታውቁት ቋንቋ ባነጋግራችሁ፥ የጥበብ ነገርንም ቢሆን፥ የትንቢትንም ነገር ቢሆን፥ የማስተማር ሥራንም ቢሆን ገልጬ ካልነገርኋችሁ የምጠቅማችሁ ጥቅም ምንድን ነው? 7ነፍስ የሌለው ድምፅ የሚሰጥ እንደ መሰንቆ፥#ግሪኩ “እንደ ዋሽንት” ይላል። ወይም እንደ ክራር ያለ መሣሪያ በስልት ካልተመታ መሰንቆው ወይም ክራሩ የሚለውን ማን ያውቃል? 8መለከት የሚነፋም በታወቀው ስልት ካልነፋ ለጦርነት ማን ይዘጋጃል? 9እንዲሁም እናንተ በማይታወቅ ቋንቋ ብትናገሩ፥ ይህንኑም ገልጣችሁ ባትተረጕሙ የምትሉትንና የምትናገሩትን ማን ያውቃል? ከነፋስ ጋር እንደምትነጋገሩ ትሆናላችሁ። 10በዓለም ልዩ ልዩ ቋንቋዎች አሉ፤ ከእነርሱም ትርጕም የሌለው አንድም የለም። 11የቋንቋውን ትርጓሜ ካላወቅሁ እኔ ለሚያነጋግረኝ እንደ እንግዳ እሆንበታለሁ፤ የሚያነጋግረኝ እርሱም ለእኔ እንደ እንግዳ ይሆናል። 12እንዲሁ እናንተም ለመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ተፎካከሩ፤ ትበዙም ዘንድ ማኅበሩ የሚታነጽበትን ፈልጉ። 13በማያውቀው ቋንቋ የሚናገር ሰውም መተርጐም እንዲችል ይጸልይ። 14በማላውቀው ቋንቋ የምጸልይ ከሆንሁ ቃሌ ብቻ ይጸልያል፤ ልቤ ግን ባዶ ነው። 15እንግዲህ ምን አደርጋለሁ በመንፈስ እጸልያለሁ፤ በማስተዋልም እማልዳለሁ፤ በመንፈሴ እዘምራለሁ፤ በማስተዋልም እዘምራለሁ። 16አንተ በመንፈስ ብታመሰግን፥ ያ የቆመው ያልተማረው በአንተ ምስጋና ላይ እንዴት አሜን ይላል? የምትናገረውንና የምትጸልየውን አያውቅምና። 17እነሆ፥ አንተስ መልካም ታመሰግናለህ፤ ነገር ግን ሌላው እንዴት ይታነጻል? 18እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፤ ከሁላችሁ ይልቅ እኔ በቋንቋዎች እናገራለሁና። 19ነገር ግን ሌሎችን አስተምር ዘንድ፥ በቋንቋ ከሚነገር ብዙ ቃል ይልቅ በቤተ ክርስቲያን በአእምሮዬ አምስት ቃላትን ልናገር እሻለሁ።
20ወንድሞቻችን ሆይ፥ በአእምሮ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃናት ሁኑ፤ በዕውቀትም ፍጹማን ሁኑ። 21#ኢሳ. 28፥11-12። በኦሪትም፥ “ይህን ሕዝብ በሌሎች ቋንቋዎችና በሌላ አንደበት እናገራቸዋለሁ፤ እንዲሁም ሆኖ አይሰሙኝም ይላል እግዚአብሔር” ብሎአል። 22አሁንም ቋንቋ መናገር ለማያምኑ ሰዎች ለምልክት ነው፤ ለሚያምኑ ግን አይደለም፤ ትንቢትም ለሚያምኑ ነው እንጂ ለማያምኑ አይደለም። 23ሕዝቡ ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰቡ፥ ሁሉም በልዩ ልዩ ቋንቋ ቢናገሩ፥ አላዋቂዎች፥ ወይም የማያምኑ ቢመጡ አብደዋል ይሉአቸው የለምን? 24ሁሉም ትንቢት ቢናገሩ ግን የማያምኑ ወይም አላዋቂዎች ቢመጡ ሁሉ ይከራከሩአቸው የለምን? ሁሉስ ያሳፍሩአቸው የለምን? 25በልባቸው የደበቁትም ይገለጣል፤ ከዚህ በኋላ ያ የማያምነው ተመልሶ ይጸጸታል፤ በግንባሩም ወድቆ ለእግዚአብሔር ይሰግዳል፥ በእውነት እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለም ይናገራል።
ስለ ጸሎተ ማኅበር ሥርዐት
26አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ ሁላችሁ በምትሰበሰቡበት ጊዜ መዝሙር አላችሁ፤ ትምህርት አላችሁ፤ መግለጥ አላችሁ፤ በቋንቋ መናገር አላችሁ፤ መተርጐምም አላችሁ፤ ሁሉም ለሚታነጽበት ጥቅም አድርጉት። 27በቋንቋ የሚናገር ቢኖር ሁለት ሁለት፥ ወይም ቢበዛ ሦስት ሦስት እየሆኑ በተራ ይናገሩ፤ ሌላውም ይተርጕምለት። 28የሚተረጕም ከሌለ ግን በቤተ ክርስቲያን በቋንቋ የሚናገረው ዝም ይበል፤ በእግዚአብሔር መካከልና በእርሱ መካከል ይናገር። 29ነቢያትም ቃላቸው ለቤተ ክርስቲያን ይታወቅ ዘንድ ሁለት ሁለት፥ ወይም ሦስት ሦስት ሆነው ይናገሩ። 30ተቀምጦ ሳለ ምሥጢር የተገለጠለት ቢኖር ፊተኛው ዝም ይበል። 31ሁሉ እንዲማር፥ ሁሉም ደስ እንዲለው፥ እንዲጸናም ሁላችሁ እያንዳንዳችሁ ትንቢት ልትናገሩ ትችላላችሁና። 32የነቢያት ሀብት ለነቢያት ይሰጣልና። 33በቅዱሳን ጉባኤ ሁሉ እንደሚደረግ፥ እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና። 34ሴቶችም በቤተ ክርስቲያን ዝም ይበሉ፤ ሊታዘዙ እንጂ ሊናገሩ አልተፈቀደምና፤ ኦሪትም እንዲህ ብሎአልና። 35ለሴት በቤተ ክርስቲያን መናገር ክልክል ነው፤ ሊማሩ ከወደዱ ደግሞ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ። 36የእግዚአብሔር ቃል ከእናንተ ብቻ ወጥቶአልን? ወይስ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እናንተ ብቻ ደርሶአልን?
37ራሱን እንደ ነቢይ አድርጎ ወይም መንፈስ ቅዱስ እንዳደረበት አድርጎ የሚቈጥር ቢኖር፥ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነውና ይህን የጻፍሁላችሁን ይወቅ። 38ነገር ግን ይህን የማያውቅ ቢኖር እግዚአብሔርን አያውቀውም። 39አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ ትንቢትን ለመናገር ቅኑ፤ በቋንቋ የሚናገረውንም አትከልክሉት። 40ነገር ግን ሁሉን በአገባብና በሥርዐት አድርጉ፤
Currently Selected:
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 14: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: