YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 15

15
የተ​ማ​ሩ​ትን ስለ ማስ​ታ​ወስ
1ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ች​ሁ​ንና የተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ትን ያላ​ች​ሁ​በ​ትን፥ በእ​ር​ሱም የም​ት​ድ​ኑ​በ​ትን ወን​ጌል አሳ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ። 2ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ች​ሁን ታስቡ እንደ ሆነ በቃሌ አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ያለ​ዚያ ግን ማመ​ና​ችሁ ከንቱ ነው።
ስለ ጌታ​ችን ትን​ሣ​ኤና መገ​ለጥ
3 # መዝ. 54፥5-12። እኔ የተ​ማ​ር​ሁ​ትን አስ​ቀ​ድሜ መጽ​ሐፍ እን​ደ​ሚል እን​ዲህ ብዬ አስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ችሁ፥ “ክር​ስ​ቶስ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ሞተ። 4#መዝ. 15፥8-10፤ ማቴ. 12፥40፤ የሐዋ. 2፥24-32። ተቀ​በረ፤ እንደ ተጻ​ፈም በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተነሣ።” 5#ማቴ. 28፥16-17፤ ማር. 16፥14፤ ሉቃ. 24፥36፤ ዮሐ. 20፥19። ለጴ​ጥ​ሮስ ታየው፤ ከዚ​ህም በኋላ ለዐ​ሥራ አንዱ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ታያ​ቸው። 6ከዚ​ህም በኋላ ከአ​ም​ስት መቶ ለሚ​በዙ ወን​ድ​ሞች በአ​ንድ ጊዜ ታያ​ቸው፤ ከእ​ነ​ርሱ ብዙ​ዎቹ እስከ ዛሬ አሉ፤ አን​ዳ​ን​ዶቹ ግን አን​ቀ​ላ​ፍ​ተ​ዋል። 7ከዚ​ህም በኋላ ለያ​ዕ​ቆብ ታየው፤ ኋላም ለሐ​ዋ​ር​ያት ሁሉ፤ 8#የሐዋ. 9፥3-6። ከሁ​ሉም በኋላ ጭን​ጋፍ ለም​መ​ስል ለእኔ ታየኝ። 9#የሐዋ. 8፥3። ከሐ​ዋ​ር​ያት ሁሉ እኔ አን​ሣ​ለ​ሁና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ስለ አሳ​ደ​ድሁ ሐዋ​ርያ ተብዬ ልጠራ የማ​ይ​ገ​ባኝ፥ 10ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለ​ሁ​በት አለሁ፤ ለእ​ኔም የሰ​ጠኝ ጸጋው ለከ​ንቱ የሆ​ነ​ብኝ አይ​ደ​ለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከ​ምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አጸ​ናኝ እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም። 11አሁ​ንም እኔም ብሆን፥ እነ​ር​ሱም ቢሆኑ እን​ዲህ እና​ስ​ተ​ም​ራ​ለን፤ እና​ን​ተም እን​ዲሁ አም​ና​ች​ኋል።
ስለ ሙታን መነ​ሣት
12ክር​ስ​ቶስ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ተነ​ሥ​ቶ​አል ብለን ለሌ​ላው የም​ና​ስ​ተ​ምር ከሆነ፥ እን​ግ​ዲህ ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ሙታን አይ​ነ​ሡም የሚሉ እን​ዴት ይኖ​ራሉ? 13ሙታን የማ​ይ​ነሡ ከሆነ ክር​ስ​ቶ​ስም ከሙ​ታን ተለ​ይቶ አል​ተ​ነ​ሣማ፤ 14ክር​ስ​ቶ​ስም ከሙ​ታን ካል​ተ​ነሣ እን​ግ​ዲ​ያስ ትም​ህ​ር​ታ​ችን ከንቱ ነው፤ የእ​ና​ን​ተም እም​ነ​ታ​ችሁ ከንቱ ነው። 15እኛም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮች ሆነ​ናል፤ ክር​ስ​ቶ​ስን አስ​ነ​ሣው ብለ​ና​ልና፥ እን​ግ​ዲያ ሳያ​ስ​ነ​ሣው ነውን?። 16ሙታን የማ​ይ​ነሡ ከሆነ ክር​ስ​ቶ​ስም ከሙ​ታን አል​ተ​ነ​ሣማ። 17ክር​ስ​ቶ​ስም ከሙ​ታን ካል​ተ​ነሣ ማመ​ና​ችሁ ከንቱ ነው፤ ገናም በኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ አላ​ችሁ። 18እን​ግ​ዲ​ያስ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ነው የሞቱ ጠፍ​ተ​ዋላ። 19በዚህ ዓለም ሕይ​ወት ብቻ ክር​ስ​ቶ​ስን ተስፋ ከአ​ደ​ረ​ግ​ነው ከሰው ሁሉ ይልቅ ጉዳ​ተ​ኞች ነን።
20አሁ​ንም ክር​ስ​ቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ተነ​ሥ​ቶ​አል። 21በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰው ሞት መጥ​ቶ​አ​ልና፤ በሁ​ለ​ተ​ኛው ሰው ትን​ሣኤ ሙታን ሆነ። 22ሁሉ በአ​ዳም እን​ደ​ሚ​ሞት እን​ዲሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ሁሉ ሕያ​ዋን ይሆ​ናሉ። 23ነገር ግን ሰው ሁሉ በየ​ሥ​ር​ዐቱ ይነ​ሣል፤ በመ​ጀ​መ​ሪያ ከሙ​ታን የተ​ነሣ ክር​ስ​ቶስ ነው፤ ከዚያ በኋላ በክ​ር​ስ​ቶስ ያመኑ እርሱ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ ይነ​ሣሉ። 24እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ መን​ግ​ሥ​ቱን እጅ ባደ​ረገ ጊዜ፥ ገዥም ሁሉ፥ ንጉ​ሥም ሁሉ፥ ኀይ​ልም ሁሉ በተ​ሻረ ጊዜ፥ ያን​ጊዜ ፍጻሜ ይሆ​ናል። 25#መዝ. 109፥1። ጠላ​ቶቹ ሁሉ ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ወ​ድቁ#ግሪኩ “ጠላ​ቶ​ቹን ሁሉ ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ጥ​ል​ለት ድረስ” ይላል። ድረስ ይነ​ግሥ ዘንድ አለ​ውና። 26ከዚያ በኋላ የመ​ጨ​ረ​ሻው ጠላት ይሻ​ራል፤ ይኸ​ውም ሞት ነው። 27#መዝ. 8፥6። ሁሉን ከእ​ግሩ በታች አስ​ገ​ዝ​ቶ​ለ​ታ​ልና፥ “ሁሉ ይገ​ዛ​ለት” ባለ ጊዜ ግን ሁሉን ከሚ​ያ​ስ​ገ​ዛ​ለት በቀር እንደ ሆነ የታ​ወቀ ነው። 28ሁሉም በተ​ገ​ዛ​ለት ጊዜ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሁሉ ቦታ በሁሉ ይሆን ዘንድ፥ ያን ዕለት ወል​ድም ሁሉን ላስ​ገ​ዛ​ለት ይገ​ዛል።
29ያለ​ዚ​ያማ ለምን ያጠ​ም​ቃሉ? ሙታን እን​ዲ​ነሡ አይ​ደ​ለ​ምን? ሙታን የማ​ይ​ነሡ ከሆ​ነስ ለምን ያጠ​ም​ቃሉ?#ግሪኩ “እን​ግ​ዲ​ያማ ካል​ሆነ ስለ ሙታን የሚ​ጠ​መቁ ምን ያደ​ር​ጋሉ ሙታ​ንስ ከቶ የማ​ይ​ነሡ ከሆነ ስለ እነ​ርሱ የሚ​ጠ​መቁ ስለ ምን​ድን ነው?” ይላል። 30እን​ግ​ዲህ እኛስ ሁል​ጊዜ መከ​ራን ስለ​ምን እን​ቀ​በ​ላ​ለን? 31ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሆ​ነ​ውና በእ​ና​ንተ ላይ ባለኝ ትም​ክ​ህት ሁል​ጊዜ እገ​ደ​ላ​ለሁ። 32#ኢሳ. 22፥13። በውኑ በኤ​ፌ​ሶን ከአ​ውሬ ጋር የታ​ገ​ልሁ ለሰው ብዬ ነውን? ምንስ ይጠ​ቅ​መ​ኛል? ሙታን የማ​ይ​ነሡ ከሆነ እን​ግ​ዲህ እን​ብላ እን​ጠጣ፥ ነገም እን​ሞ​ታ​ለን። 33ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን#“ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። አያ​ስ​ቱ​አ​ችሁ፤ ክፉ ነገር መል​ካም ጠባ​ይን ያበ​ላ​ሻ​ልና።
ስለ ትን​ሣኤ በም​ሳሌ ትም​ህ​ርት
34ለጽ​ድቅ ትጉ፤ አት​ሳቱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የማ​ያ​ው​ቁት ሰዎች አሉና፤ ነገር ግን እን​ድ​ታ​ፍሩ ይህን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ 35ሙታን እን​ዴት ይነ​ሣሉ? የሚ​ነ​ሡስ በምን አካ​ላ​ቸው ነው? የሚል አለ። 36አንተ ሰነፍ! አንተ የም​ት​ዘ​ራው እን​ኳን ካል​ፈ​ረሰ አይ​በ​ቅ​ልም። 37የም​ት​ዘ​ራ​ውም የስ​ንዴ ቢሆን፥ የሌ​ላም ቢሆን የም​ት​ዘ​ራት ቅን​ጣት ብቻ ናት እንጂ ይህ ኋላ የሚ​ገ​ኘው አገ​ዳው አይ​ደ​ለም። 38እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እንደ ወደደ አገ​ዳን ይሰ​ጠ​ዋል፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ዘርም አገ​ዳው እየ​ራሱ ነው።
39የፍ​ጥ​ረቱ ሁሉ አካል አንድ አይ​ደ​ለ​ምና፤ የሰው አካል ሌላ ነው፤ የእ​ን​ስ​ሳም አካል ሌላ ነው፤ የወፍ አካ​ልም ሌላ ነው፤ የዓሣ አካ​ልም ሌላ ነው። 40ሰማ​ያዊ አካል አለ፤ ምድ​ራዊ አካ​ልም አለ፤ ነገር ግን በሰ​ማይ ያለው አካል ክብሩ ልዩ ነው፤ በም​ድ​ርም ያለው አካል ክብሩ ልዩ ነው። 41የፀ​ሐይ ክብሩ ሌላ ነው፤ የጨ​ረ​ቃም ክብሩ ሌላ ነው፤ የከ​ዋ​ክ​ብ​ትም ክብ​ራ​ቸው ሌላ ነው፤ ኮከብ ከኮ​ከብ በክ​ብር ይበ​ል​ጣ​ልና።
42የሙ​ታን ትን​ሣ​ኤ​ያ​ቸው እን​ዲሁ ነው፥ በሚ​ፈ​ርስ አካል ይዘ​ራል፤ በማ​ይ​ፈ​ርስ አካል ይነ​ሣል። 43በው​ር​ደት ይዘ​ራል፤ በክ​ብር ይነ​ሣል፤ በድ​ካም ይዘ​ራል፤ በኀ​ይል ይነ​ሣል። 44ሥጋዊ አካል ይዘ​ራል፤ መን​ፈ​ሳዊ አካል ይነ​ሣል፤ ሥጋዊ አካል አለና መን​ፈ​ሳዊ አካ​ልም ደግሞ አለ። 45#ዘፍ. 2፥7። መጽ​ሐፍ እን​ዲሁ ብሎ​አ​ልና የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰው አዳም በነ​ፍስ ሕያው ሆኖ ተፈ​ጠረ፤ ሁለ​ተ​ኛው አዳም ግን ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ መን​ፈስ ነው። 46ነገር ግን አስ​ቀ​ድሞ ሥጋ​ዊው፥ ቀጥ​ሎም መን​ፈ​ሳ​ዊው ነው እንጂ፥ መን​ፈ​ሳ​ዊው መጀ​መ​ሪ​ያው አይ​ደ​ለም። 47መጀ​መ​ሪ​ያው ሰው ከመ​ሬት የተ​ገኘ መሬ​ታዊ ነው፤ ሁለ​ተ​ኛው ሰው ከሰ​ማይ የወ​ረደ ሰማ​ያዊ ነው። 48መሬ​ታ​ው​ያኑ እን​ደ​ዚያ እንደ መሬ​ታ​ዊው ናቸው፤ ሰማ​ያ​ው​ያ​ኑም እን​ደ​ዚያ እንደ ሰማ​ያ​ዊው ናቸው። 49የመ​ሬ​ታ​ዊ​ውን መልክ እንደ ለበ​ስን እን​ዲሁ የሰ​ማ​ያ​ዊ​ውን መልክ ደግሞ እን​ለ​ብ​ሳ​ለን። 50ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ይህን እን​ነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለን፦ ሥጋ​ዊና ደማዊ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አይ​ወ​ር​ስም፥ የሚ​ፈ​ር​ሰው የማ​ይ​ፈ​ር​ሰ​ውን አይ​ወ​ር​ስም። 51እነሆ፥ አንድ ምሥ​ጢ​ርን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፥ ሁላ​ችን የም​ን​ሞት አይ​ደ​ለም። 52#1ተሰ. 4፥15-17። ነገር ግን የኋ​ለ​ኛው መለ​ከት ሲነፋ ሁላ​ችን እንደ ዐይን ጥቅሻ በአ​ንድ ጊዜ እን​ለ​ወ​ጣ​ለን፤ መለ​ከት ይነ​ፋል፤ ሙታ​ንም የማ​ይ​ፈ​ርሱ ሁነው ይነ​ሣሉ፤ እኛም እን​ለ​ወ​ጣ​ለን። 53ይህ የሚ​ፈ​ር​ሰው የማ​ይ​ፈ​ር​ሰ​ውን፥ ይህም የሚ​ሞ​ተው የማ​ይ​ሞ​ተ​ውን ይለ​ብስ ዘንድ አለ​ውና። 54ይህ የሚ​ፈ​ር​ሰው የማ​ይ​ፈ​ር​ሰ​ውን በለ​በሰ ጊዜ፥ የሚ​ሞ​ተ​ውም የማ​ይ​ሞ​ተ​ውን በለ​በሰ ጊዜ፤ “ሞት በመ​ሸ​ነፍ ተዋጠ” ተብሎ የተ​ጻ​ፈው ያን​ጊዜ ይፈ​ጸ​ማል። 55#ሆሴዕ 13፥14። “ሞት ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ መው​ጊ​ያህ ወዴት አለ? መቃ​ብር ሆይ፥ አሸ​ና​ፊ​ነ​ትህ ወዴት አለ?” 56የሞት መው​ጊያ ኀጢ​አት ናት፥ የኀ​ጢ​አ​ትም ኀይ​ልዋ ኦሪት ናት። 57በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ድል መን​ሣ​ትን ለሰ​ጠን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን። 58አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የጸ​ና​ች​ሁና የማ​ት​ና​ወጡ ሁኑ፤ ዘወ​ትር በጎ ምግ​ባ​ርን አብ​ዝ​ታ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አበ​ር​ክቱ፤ ስለ ጌታ​ችን መድ​ከ​ማ​ችሁ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ይ​ደለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in