YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 16

16
ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምእ​መ​ና​ን​ስ​ለ​ሚ​ደ​ረግ አስ​ተ​ዋ​ፅኦ
1 # ሮሜ 15፥25-26። ለቅ​ዱ​ሳን ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው አስ​ተ​ዋ​ፅኦ በገ​ላ​ትያ ላሉት ምእ​መ​ናን እንደ ደነ​ገ​ግ​ሁት እና​ን​ተም እን​ዲሁ አድ​ርጉ። 2እኔ ስመጣ ይህ የገ​ን​ዘብ ማዋ​ጣት ያን​ጊዜ እን​ዳ​ይ​ሆን፥ ከእ​ና​ንተ ሰው ሁሉ በየ​ሳ​ም​ንቱ እሑድ የተ​ቻ​ለ​ውን ያወ​ጣጣ፤ ያገ​ኘ​ው​ንም በቤቱ ይጠ​ብቅ። 3በመ​ጣሁ ጊዜም ስጦ​ታ​ች​ሁን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያደ​ርሱ ዘንድ የመ​ረ​ጣ​ች​ኋ​ቸ​ውን ሰዎች መል​እ​ክ​ቴን ጨምሬ እል​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ። 4ለመ​ሄድ ቢቻ​ለኝ ግን እኔ ራሴ እሄ​ዳ​ለ​ሁና፥ እነ​ር​ሱም አብ​ረ​ውኝ ይሄ​ዳሉ። 5#የሐዋ. 19፥21። መቄ​ዶ​ን​ያም ደርሼ ወደ እና​ንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ በመ​ቄ​ዶ​ንያ በኩል አል​ፋ​ለ​ሁና። 6እና​ን​ተም ወደ​ም​ሄ​ድ​በት ትሸ​ኙኝ ዘንድ ምን​አ​ል​ባት የሆ​ነ​ውን ቀን ያህል በእ​ና​ንተ ዘንድ እቈይ፥ ወይም እከ​ርም ይሆ​ናል። 7አሁን እግረ መን​ገ​ዴን ላያ​ችሁ አል​ሻም፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ቀደ እንደ ሆነ የሆ​ነ​ውን ቀን ያህል በእ​ና​ንተ ዘንድ እን​ደ​ም​ቈይ ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ። 8#ዘሌ. 23፥15-21፤ ዘዳ. 16፥9-11። እስከ በዓለ ኀምሳ በኤ​ፌ​ሶን እቈ​ያ​ለሁ። 9#የሐዋ. 19፥8-10። ሥራ የሞ​ላ​በት ታላቅ በር ተከ​ፍ​ቶ​ል​ኛ​ልና፤ ነገር ግን ብዙ​ዎች ተቃ​ዋ​ሚ​ዎች አሉ።
10 # 1ቆሮ. 4፥17። ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም በመጣ ጊዜ በእ​ና​ንተ ዘንድ ያለ ፍር​ሀት እን​ዲ​ኖር ተጠ​ን​ቀቁ፤ እንደ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ይሠ​ራ​ልና። 11የሚ​ን​ቀ​ውም አይ​ኑር፤ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ጋር እጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለ​ሁና፥ ወደ እኔ እን​ዲ​መጣ በሰ​ላም ሸኙት።
12ስለ ወን​ድ​ማ​ችን ስለ አጵ​ሎ​ስም ከወ​ን​ድ​ሞች ጋር ወደ እና​ንተ እን​ዲ​መጣ መላ​ልሼ ማል​ጄው ነበር፤ አሁን ሊመጣ አል​ወ​ደ​ደም፤ በተ​ቻ​ለው ጊዜ ግን ይመ​ጣል። 13ትጉ፤ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትም ቁሙ፤ ታገሡ#ግሪኩ “ጐል​ምሱ” ይላል። ጽኑ፤ 14ሁሉን በፍ​ቅር አድ​ርጉ። 15#1ቆሮ. 1፥16። ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስና የፈ​ር​ዶ​ና​ጥስ፥ የአ​ካ​ይ​ቆ​ስም#“የፈ​ር​ዶ​ና​ጥ​ስና የአ​ካ​ይ​ቆ​ስም ቤተ​ሰ​ቦች” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ቤተ​ሰ​ቦች፥ የአ​ካ​ይያ መጀ​መ​ሪ​ያ​ዎች እንደ ሆኑ፥ ቅዱ​ሳ​ን​ንም ለማ​ገ​ል​ገል ራሳ​ቸ​ውን እንደ ሰጡ ታውቁ ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ። 16እና​ን​ተም እንደ እነ​ዚህ ላሉ​ትና ከእኛ ጋር በሥራ ተባ​ብሮ ለሚ​ደ​ክም ሁሉ ትታ​ዘ​ዙ​ላ​ቸው ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ። 17እስ​ጢ​ፋ​ኖስ፥ ፈር​ዶ​ና​ጥ​ስና አካ​ይ​ቆስ በመ​ም​ጣ​ታ​ቸ​ውም ደስ ይለ​ኛል፤ እና​ንተ ያጐ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን እነ​ርሱ ፈጽ​መ​ዋ​ልና። 18እነ​ርሱ መን​ፈ​ሴ​ንና መን​ፈ​ሳ​ች​ሁን ደስ አሰ​ኝ​ተ​ዋል፤ እን​ዲህ ያሉ​ት​ንም ዕወ​ቋ​ቸው።
19 # የሐዋ. 18፥2። በእ​ስያ ያሉ ምእ​መ​ናን ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል፤ አቂ​ላና ጵር​ስ​ቅላ በቤ​ታ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያሉ ምእ​መ​ና​ንም ሁሉ በጌ​ታ​ችን እጅግ ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል። 20ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ሁሉ ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል፤ በተ​ቀ​ደ​ሰች ሰላ​ምታ እርስ በር​ሳ​ችሁ ሰላም ተባ​ባሉ።
21እኔ ጳው​ሎስ ይህን ሰላ​ምታ በእጄ ጻፍሁ። 22ጌታ​ች​ንን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን የማ​ይ​ወ​ደው የተ​ለየ ይሁን፤ ጌታ​ችን ይመ​ጣል። 23የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋራ ይሁን። 24የእ​ኔም ፍቅር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን። አሜን።
በኤ​ፌ​ሶን ተጽፎ በጢ​ሞ​ቴ​ዎ​ስና በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ፥ በፈ​ር​ዶ​ና​ጥ​ስና በአ​ካ​ይ​ቆስ እጅ ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች የተ​ላ​ከው መጀ​መ​ሪ​ያዉ መል​እ​ክት ተፈ​ጸመ።
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in