መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 1
1
ሕልቃናና ቤተ ሰቡ በሴሎ
1በተራራማው በኤፍሬም ሀገር ከአርማቴም መሴፋ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ስሙም፥ የናሲብ#በግሪክ ሰባ. ሊ. “ለቦታ” ነው። ልጅ የቴቆ ልጅ፥ የኤልዩ ልጅ ፥ የኢያርምያል ልጅ፥ ኤፍራታዊው ሕልቃና ነበረ። 2ሁለትም ሚስቶች ነበሩት፤ የአንዲቱ ስም ሐና፥ የሁለተኛዪቱም ስም ፍናና ነበረ፤ ለፍናናም ልጆች ነበሩአት፤ ለሐና ግን ልጆች አልነበሩአትም። 3ያም ሰው በሴሎ ይሰግድ ዘንድ፥ ለሠራዊት ጌታም ለእግዚአብሔር ይሠዋ ዘንድ ከከተማው ከአርማቴም በየዓመቱ ይወጣ ነበር። የእግዚአብሔርም ካህናት ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በዚያ ነበሩ። 4ሕልቃናም የሚሠዋበት ቀን በደረሰ ጊዜ ለሚስቱ ለፍናናና ለልጆችዋ#ግሪክ. ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ለወንዶችና ሴቶች ልጆችዋ” ይላል። ሁሉ ዕድል ፋንታቸውን ሰጣቸዉ። 5ለሐናም ልጅ ስላልነበራት አንድ#ዕብ. “ሁለት” ይላል። ዕድል ፋንታ ሰጣት፤ ሕልቃናም ከዚያችኛይቱ ይልቅ ሐናን ይወድድ ነበር። እግዚአብሔር ግን ማኅፀንዋን ዘግቶ ነበር። 6እንደ መከራዋና እንደ ኀዘንዋም እግዚአብሔር ልጅ አልሰጣትም ነበር። ስለዚህም ታዝን ነበር። እግዚአብሔር ማኅፀንዋን ዘግትዋልና፥ ልጆችንም አልሰጣትምና። 7በየዓመቱም ወደ እግዚአብሔር ቤት በሚወጣበት ጊዜ እንዲህ ያደርግ ነበር፤ እርስዋም ትበሳጭና ታለቅስ ነበር። እህልም አትበላም ነበር። 8ባልዋ ሕልቃናም፥ “ሐና ሆይ!” አላት እርስዋም፥ “ጌታዬ እነሆኝ” አለችው። እርሱም፥ “ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትበዪም? ለምንስ ልብሽ ያዝንብሻል? እኔስ ከዐሥር ልጆች አልሻልሽምን?” አላት።
ካህኑ ዔሊና ሐና
9በሴሎም ከበሉ በኋላ ሐና ተነሣች። በሴሎም በእግዚአብሔር ፊት ቆመች። ካህኑም ዔሊ በእግዚአብሔር መቅደስ መቃን አጠገብ በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር። 10እርስዋም በልብዋ አዝና አለቀሰች፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየች። 11እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች።
12ጸሎቷንም በእግዚአብሔር ፊት ባበዛች ጊዜ፥ ካህኑ ዔሊ አፍዋን ይመለከት ነበር። 13ሐናም በልብዋ ትናገር ነበር፤ ድምፅዋም ሳይሰማ ከንፈርዋን ታንቀሳቅስ ነበር፤ ዔሊም እንደ ሰከረች ቈጠራት። 14የዔሊም አገልጋይ፦#ዕብ. “ዔሊ ተናገራት” ይላል። “ስካርሽ እስከ መቼ ነው? የወይን ጠጅሽን ከአንቺ አርቂው፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ውጪ” አላት። 15ሐናም መልሳ እንዲህ አለችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አይደለም፤ እኔስ ወራት የባሳት ሴት ነኝ፤ ጠጅና ሌላ የሚያሰክር ነገር አልጠጣሁም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ነፍሴን አፈሰስሁ፤ 16ኀዘኔና ጭንቀቴ ስለ በዛ እስከ አሁን ድረስ እደክማለሁና ባርያህን እንደ ኀጢአተኞች ሴቶች ልጆች አትቍጠራት።” 17ዔሊም፥ “በሰላም ሂጂ፤ የእስራኤልም አምላክ ከአንቺ ጋር ይሁን#“ከአንቺ ጋር ይሁን” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። የለመንሽውንም ልመና ሁሉ ይስጥሽ” ብሎ መለሰላት። 18እርስዋም፥ “ባርያህ በፊትህ ሞገስን አገኘች” አለችው። ሴቲቱም መንገድዋን ሄደች፤ ወደ ቤትዋም ገባች፤ ከባሏም ጋር በላች፤ ጠጣችም ፤ ፊቷም ከዚያ በኋላ አዘንተኛ መስሎ አልታየም።
የሳሙኤል መወለድና ለእግዚአብሔር መሰጠቱ
19ማልደውም ተነሥተው ለእግዚአብሔር ሰግደው ሄዱ፤ ወደ ቤታቸውም ወደ አርማቴም ደረሱ፤ ሕልቃናም ሚስቱን ሐናን ዐወቃት፤ እግዚአብሔርም አሰባት፤ ፀነሰችም። 20የመውለጃዋም ወራት በደረሰ ጊዜ ሐና ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርስዋም፥ “ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ለምኜዋለሁ” ስትል ስሙን “ሳሙኤል” ብላ ጠራችው።
21ሰውዬውም ሕልቃና ከቤተ ሰቡ ሁሉ ጋር የዓመቱን መሥዋዕትና ስእለቱን፥ የምድሩንም ዐሥራት ሁሉ ለእግዚአብሔር ያቀርብ ዘንድ ወጣ። 22ሐና ግን ከእርሱ ጋር አልወጣችም። ለባልዋም፥ “ሕፃኑን ጡት እስከ አስጥለው፥ ከእኔም ጋር እስኪወጣና በእግዚአብሔር ፊት እስኪታይ ድረስ አልወጣም፤ በዚያም ለዘለዓለም ይኖራል” ብላዋለችና። 23ባልዋም ሕልቃና፥ “በዐይንሽ ደስ ያሰኘሽን አድርጊ፤ ጡትም እስኪተው ድረስ ተቀመጪ፤ ብቻ እግዚአብሔር ከአፍሽ የወጣውን ያጽና” አላት። ሴቲቱም ልጅዋን እያጠባች ጡት እስኪተው ድረስ ተቀመጠች። 24#ዕብ. “ጡትም በተወ ጊዜ” የሚል ይጨምራል።እርስዋም ከእርሱ ጋር አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፥ እንጀራ፥ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወጣች። በሴሎም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት ገባች። ልጃቸውም ከእነርሱ ጋር ነበረ። 25በእግዚአብሔርም ፊት አቀረቡት ፤ አባቱም በየዓመቱ ለእግዚአብሔር የሚሠዋውን መሥዋዕት ሠዋ። ሕፃኑንም አቀረበው፤ ወይፈኑንም አረደ፤ እናቱም ሐና ሕፃኑን ወደ ዔሊ አገባችው። 26እርስዋም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ በዚህ በፊትህ ቆማ የነበረች ሴት እኔ ነኝ። 27ስለዚህ ልጅ ተሳልሁ፤ ጸለይሁም፤ እግዚአብሔርም የለመንሁትን ልመናዬን ሰጥቶኛል፤ 28እኔም ደግሞ ዕድሜውን ሙሉ እግዚአብሔርን ያገለግል ዘንድ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 1: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: