YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 11

11
ሳኦል አሞ​ና​ው​ያ​ንን ድል እንደ አደ​ረገ
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከአ​ንድ ወር በኋላ አሞ​ና​ዊው ናዖስ መጣ፤ በኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓ​ድም ሰፈረ፤ የኢ​ያ​ቢ​ስም ሰዎች ሁሉ፥ “አሞ​ና​ዊ​ውን ናዖ​ስን ቃል ኪዳን አድ​ር​ግ​ልን፤ እኛም እን​ገ​ዛ​ል​ሃ​ለን” አሉት። 2አሞ​ና​ዊው ናዖ​ስም፦“ ቀኝ ዐይ​ና​ች​ሁን ብታ​ወጡ ከእ​ና​ንተ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ላይ ስድ​ብን አደ​ር​ጋ​ለሁ” አላ​ቸው። 3የኢ​ያ​ቢ​ስም ሰዎች፥ “ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን እን​ድ​ን​ልክ ሰባት ቀን ቈይ​ልን፤ ከዚ​ያም በኋላ የሚ​ያ​ድ​ነን ባይ​ኖር ወደ አንተ እን​መ​ጣ​ለን” አሉት። 4መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹም ሳኦል ወዳ​ለ​በት ወደ ገባ​ዖን መጥ​ተው ይህን ነገር በሕ​ዝቡ ጆሮ ተና​ገሩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን ከፍ አድ​ር​ገው አለ​ቀሱ። 5እነ​ሆም፥ ሳኦል ከእ​ር​ሻው አር​ፍዶ መጣ፤ ሳኦ​ልም፥ “ሕዝቡ የሚ​ያ​ለ​ቅስ ምን ሆኖ ነው?” አለ። የኢ​ያ​ቢ​ስ​ንም ሰዎች ነገር ነገ​ሩት።
6ይህ​ንም ነገር በሰማ ጊዜ በሳ​ኦል ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ መጣ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ተቈጣ። 7ጥም​ዱ​ንም በሬ​ዎች ወስዶ በየ​ብ​ል​ታ​ቸው ቈራ​ረ​ጣ​ቸው፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ዳርቻ ሁሉ በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኞቹ እጅ ላከና፥ “ሳኦ​ል​ንና ሳሙ​ኤ​ልን ተከ​ትሎ የማ​ይ​ወጣ ሁሉ፥ በበ​ሬ​ዎቹ እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​በ​ታል” አለ። ድን​ጋ​ጤም በሕ​ዝቡ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደቀ፤ እንደ አንድ ሰውም ሆነው ጮኹ። 8በባማ ባለው በቤ​ዜ​ቅም ቈጠ​ራ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሦስት መቶ ሺህ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ስድ​ስት መቶ ሺህ” ይላል። የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሠላሳ ሺህ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰባ ሺህ” ይላል። ነበሩ። 9የመ​ጡ​ት​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች፥ “የኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓ​ድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተ​ኰሰ ጊዜ ድኅ​ነት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል በሉ​አ​ቸው” አሉ​አ​ቸው። መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ቢስ ሰዎች ነገሩ፤ ደስም አላ​ቸው። 10የኢ​ያ​ቢ​ስም ሰዎች፦ ለአ​ሞ​ና​ዊው ናዖስ “ነገ እን​ወ​ጣ​ላ​ች​ኋ​ለን፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ች​ሁ​ንም አድ​ር​ጉ​ብን” አሉት። 11በነ​ጋ​ውም ሳኦል ሕዝ​ቡን በሦ​ስት ወገን አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ወገ​ግም ባለ ጊዜ ወደ ሰፈሩ መካ​ከል ገቡ፤ ቀት​ርም እስ​ኪ​ሆን ድረስ አሞ​ና​ው​ያ​ንን መቱ፤ የቀ​ሩ​ትም ተበ​ተኑ፤ ከው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ሁለት በአ​ንድ ላይ ሆነው አል​ተ​ገ​ኙም።
የሳ​ኦል ንጉ​ሥ​ነት እንደ ተረ​ጋ​ገጠ
12ሕዝ​ቡም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ሳኦል አይ​ን​ገ​ሥ​ብን ያሉ እነ​ማን ናቸው? እነ​ዚ​ያን ሰዎች አው​ጡ​አ​ቸ​ውና እን​ግ​ደ​ላ​ቸው” አሉት። 13ሳኦ​ልም፦“በዚ​ያች ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ድኅ​ነ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ዛሬ አንድ ሰው አይ​ሞ​ትም” አለ።
14ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን፥ “ኑ፤ ወደ ጌል​ገላ እን​ሂድ፤ በዚ​ያም መን​ግ​ሥ​ቱን እና​ጽና” አላ​ቸው። 15ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ጌል​ገላ ሄዱ፤ ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን ቀብቶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጌ​ል​ጌላ አነ​ገ​ሠው፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የእ​ህል ቍር​ባ​ንና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ በዚ​ያም ሳኦ​ልና#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሳሙ​ኤል” ይላል። የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደ​ረጉ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in