YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 19

19
ሳኦል ዳዊ​ትን እንደ አሳ​ደ​ደው
1ሳኦ​ልም ለልጁ ለዮ​ና​ታ​ንና ለብ​ላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ ዳዊ​ትን ይገ​ድሉ ዘንድ ነገ​ራ​ቸው። የሳ​ኦል ልጅ ዮና​ታን ግን ዳዊ​ትን እጅግ ይወ​ድ​ደው ነበር። 2ዮና​ታ​ንም፥ “አባቴ ሳኦል ሊገ​ድ​ልህ ፈል​ጎ​አል፤ አሁን እን​ግ​ዲህ ለነ​ገው ተጠ​ን​ቅ​ቀህ ተሸ​ሸግ፤ በስ​ው​ርም ተቀ​መጥ። 3እኔም እወ​ጣ​ለሁ፤ አን​ተም ባለ​ህ​በት እርሻ በአ​ባቴ አጠ​ገብ እቆ​ማ​ለሁ፤ ስለ አን​ተም ለአ​ባቴ እነ​ግ​ረ​ዋ​ለሁ፤ የሆ​ነ​ው​ንም አይቼ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” ብሎ ለዳ​ዊት ነገ​ረው። 4ዮና​ታ​ንም ለአ​ባቱ ለሳ​ኦል ስለ ዳዊት መል​ካም ተና​ገረ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እርሱ አል​በ​ደ​ለ​ህ​ምና፥ ሥራ​ውም ለአ​ንተ እጅግ መል​ካም ሆኖ​አ​ልና ንጉሡ ባሪ​ያ​ውን ዳዊ​ትን አይ​በ​ድ​ለው፤ 5ነፍ​ሱ​ንም በእጁ ጥሎ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ገደለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ርሱ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አይ​ተው ደስ አላ​ቸው፤ በከ​ንቱ ዳዊ​ትን ትገ​ድ​ለው ዘንድ ስለ​ምን በን​ጹሕ ደም ላይ ትበ​ድ​ላ​ለህ?”
6ሳኦ​ልም የዮ​ና​ታ​ንን ቃል ሰማ፤ ሳኦ​ልም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳዊት አይ​ገ​ደ​ልም” ብሎ ማለ። 7ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን ጠርቶ ይህን ነገር ሁሉ ነገ​ረው፤ ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን ወደ ሳኦል አመ​ጣው፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም በፊቱ ነበረ።
8ደግ​ሞም ጦር​ነት ሆነ፤ ዳዊ​ትም ወጥቶ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ተዋጋ፤ ታላቅ ግዳ​ይም ገደ​ላ​ቸው፤ ከፊ​ቱም ሸሹ። 9ሳኦ​ልም ጦሩን ይዞ በቤቱ ተቀ​ምጦ ሳለ ክፉ መን​ፈስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያዘው። ዳዊ​ትም በእጁ በገና ይመታ ነበር። 10ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ከግ​ንብ ጋር ያጣ​ብ​ቀው ዘንድ ጦሩን ወረ​ወረ፤ ዳዊ​ትም ከሳ​ኦል ፊት ዘወር አለ፤ ጦሩም በግ​ንቡ ውስጥ ተተ​ከለ፤ በዚ​ያም ሌሊት ዳዊት ሸሸቶ አመ​ለጠ። 11ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ጠበ​ቀው፤ በነ​ጋው እን​ዲ​ገ​ድ​ሉት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹን ወደ ዳዊት ቤት ላከ፤ ሚስ​ቱም ሜል​ኮል፥ “በዚ​ህች ሌሊት ነፍ​ስ​ህን ካላ​ዳ​ንህ ነገ ትገ​ደ​ላ​ለህ” ብላ ነገ​ረ​ችው። 12ሜል​ኮ​ልም ዳዊ​ትን በመ​ስ​ኮት አወ​ረ​ደ​ችው፤ ሄደም፤ ሸሽ​ቶም አመ​ለጠ። 13ሜል​ኮ​ልም ተራ​ፊ​ምን#ግእዙ “ግን​ዘት” ይላል። ወስዳ በአ​ልጋ ላይ አኖ​ረ​ችው፤ በራ​ስ​ጌ​ውም ጕን​ጕን የፍ​የል ጠጕር አደ​ረ​ገች፤ በል​ብ​ስም ከደ​ነ​ችው። 14ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ይዘው እን​ዲ​ያ​መ​ጡት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እር​ስ​ዋም ታሞ​አል አለ​ቻ​ቸው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እነ​ር​ሱም ታሞ​አል አሉት” ይላል። 15ሳኦ​ልም፥ “እገ​ድ​ለው ዘንድ ዳዊ​ትን ከነ​አ​ል​ጋው” አም​ጡ​ልኝ ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹን ወደ ዳዊት ላከ። 16መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹም በገቡ ጊዜ እነሆ፥ ተራ​ፊ​ሙን በአ​ል​ጋው ላይ አገኙ፤ በራ​ስ​ጌ​ውም ጕን​ጕን የፍ​የል ጠጕር ነበረ። 17ሳኦ​ልም ሜል​ኮ​ልን አላት፥ “ስለ​ምን እን​ዲህ አታ​ለ​ል​ሽኝ? ጠላ​ቴን አስ​ኰ​በ​ለ​ልሽ፤ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ጥም አደ​ረ​ግ​ሽው?” ሜል​ኮ​ልም ለሳ​ኦል፥ “እርሱ፦ አው​ጥ​ተሽ ስደ​ጂኝ፤ አለ​ዚያ እገ​ድ​ል​ሻ​ለሁ አለኝ” አለ​ችው።
18ዳዊ​ትም ሸሽቶ አመ​ለጠ፤ ወደ አር​ማ​ቴ​ምም ወደ ሳሙ​ኤል መጣ፤ ሳኦ​ልም ያደ​ረ​ገ​በ​ትን ሁሉ ነገ​ረው፤ እር​ሱና ሳሙ​ኤ​ልም ሄዱ፤ በአ​ው​ቴ​ዘ​ራ​ማም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ናው​ት​ዘ​ራማ” ይላል። ተቀ​መጡ። 19ለሳ​ኦ​ልም፥ “ዳዊት እነሆ፥ በአ​ው​ቴ​ዘ​ራማ ተቀ​ም​ጦ​አል” ብለው ነገ​ሩት። 20ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ያመ​ጡት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ የነ​ቢ​ያ​ት​ንም ጉባኤ አገኙ፤ ሳሙ​ኤ​ልም አለ​ቃ​ቸው ሆኖ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ቆሞ ነበረ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በሳ​ኦል መል​እ​ክ​ተ​ኞች ላይ ወረደ፤ እነ​ር​ሱም ትን​ቢት ይና​ገሩ ጀመር። 21ለሳ​ኦ​ልም ይህን በነ​ገ​ሩት ጊዜ ሌሎች መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ትን​ቢት ተና​ገሩ። ሳኦ​ልም እንደ ገና ሦስ​ተኛ ጊዜ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እነ​ር​ሱም ደግሞ ትን​ቢት ተና​ገሩ። 22ሳኦ​ልም እጅግ ተቈጣ፤ እር​ሱም ደግሞ ወደ አር​ማ​ቴም መጣ፤ በመ​ሴ​ፋም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሴፋ” ሲል ዕብ. “ሴኩ” ይላል። አው​ድማ ወዳ​ለው ወደ ታላቁ የውኃ ጕድ​ጓድ ደረሰ። “ሳሙ​ኤ​ልና ዳዊት የት ናቸው?” ብሎ ጠየቀ፤ “እነሆ፥ በአ​ው​ቴ​ዘ​ራማ ናቸው” አሉት። 23ወደ አው​ቴ​ዘ​ራ​ማም ሄደ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ደግሞ ወረደ፤ እር​ሱም ሄደ፤ ወደ አው​ቴ​ዘ​ራ​ማም እስ​ኪ​መጣ ድረስ ትን​ቢት ይና​ገር ነበር። 24ልብ​ሱ​ንም አወ​ለቀ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ትን​ቢት ተና​ገረ፤ ራቁ​ቱ​ንም ወድቆ በዚያ ቀን ሁሉ በዚ​ያም ሌሊት ሁሉ ተጋ​ደመ። ስለ​ዚህ፥ “ሳኦል ደግሞ ከነ​ቢ​ያት መካ​ከል ነውን?” ይባ​ባሉ ነበር።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in