YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 21

21
ዳዊት ከሳ​ኦል ፊት እንደ ሸሸና ወደ ኖብ እንደ ሄደ
1ዳዊ​ትም ወደ ካህኑ ወደ አቤ​ሜ​ሌክ ወደ ኖብ መጣ፤ አቤ​ሜ​ሌ​ክም እር​ሱን በተ​ገ​ና​ኘው ጊዜ ደነ​ገጠ፥ “ስለ​ምን አንተ ብቻ​ህን ነህ? ከአ​ን​ተስ ጋር ስለ​ምን ማንም የለም?” አለው። 2ዳዊ​ትም ካህ​ኑን አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “የተ​ላ​ክ​ህ​በ​ትን ነገ​ርና የሰ​ጠ​ሁ​ህን ትእ​ዛዝ ማንም አይ​ወቅ ብሎ ንጉሡ አንድ ነገር አዝ​ዞ​ኛል፤ ስለ​ዚ​ህም ‘ብላ​ቴ​ኖቼን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን’ በሚ​ባ​ለው እን​ዲህ ባለው ስፍራ እን​ዲ​ሆኑ አዝ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ። 3አሁ​ንም አም​ስት እን​ጀራ በእ​ጅህ ካለ፥ ወይም በእ​ጅህ ያለ​ውን ስጠኝ” አለው። 4ካህ​ኑም ለዳ​ዊት መልሶ፥ “ሁሉ የሚ​በ​ላው እን​ጀራ የለ​ኝም፤ ነገር ግን የተ​ቀ​ደሰ እን​ጀራ አለ፤ ብላ​ቴ​ኖቹ ከሴ​ቶች ንጹ​ሓን እንደ ሆኑ መብ​ላት ይች​ላሉ” አለው። 5ዳዊ​ትም ለካ​ህኑ መልሶ፥ “ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተን ወደ መን​ገድ ከወ​ጣን ዛሬ ሦስ​ተኛ ቀና​ችን ነው። እኔም ብላ​ቴ​ኖ​ቼም ንጹ​ሓን ነን። ነገር ግን ዛሬ ሰው​ነቴ ንጽ​ሕት ስለ ሆነች ነው እንጂ ይህች መን​ገድ የነ​ጻች አይ​ደ​ለ​ችም” አለው። 6ካህኑ አቤ​ሜ​ሌ​ክም በእ​ርሱ ፋንታ ትኩስ እን​ጀራ ይደ​ረግ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከአ​ለው ኅብ​ስት በቀር ሌላ እን​ጀራ አል​ነ​በ​ረ​ምና የቍ​ር​ባ​ኑን ኅብ​ስት ሰጠው።
7በዚ​ያም ቀን ከሳ​ኦል አገ​ል​ጋ​ዮች አንድ ሰው በኔ​ሴራ አቅ​ራ​ቢያ በዚያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበር፤ ስሙም ሶር​ያ​ዊው ዶይቅ ነበረ፤ የሳ​ኦ​ልም በቅ​ሎ​ዎች ጠባቂ ነበረ። 8ዳዊ​ትም አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “የን​ጉሥ ጉዳይ ስላ​ስ​ቸ​ኰ​ለኝ ሰይ​ፌ​ንና መሣ​ሪ​ያ​ዬን አላ​መ​ጣ​ሁ​ምና በአ​ንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ እን​ዳለ እይ​ልኝ” አለው። 9ካህ​ኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገ​ደ​ል​ኸው የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው የጎ​ል​ያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊያ ተጠ​ቅ​ልላ አለች፤ የም​ት​ወ​ስ​ዳት ከሆነ ውሰ​ዳት፤ ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለ​ምና” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው። እር​ሱም ሰጠው።
10ዳዊ​ትም ተነሣ በዚ​ያም ቀን ከሳ​ኦል ፊት ሸሸ፤ ወደ ጌትም ንጉሥ ወደ አን​ኩስ መጣ። 11የአ​ን​ኩስ ብላ​ቴ​ኖ​ችም፥ “ይህ ዳዊት የሀ​ገሩ ንጉሥ አይ​ደ​ለ​ምን? ሳኦል ሺህ፥ ዳዊ​ትም ዐሥር ሺህ ገደለ ብለው ሴቶች በዘ​ፈን የዘ​መ​ሩ​ለት እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?” አሉት። 12ዳዊ​ትም ይህን ቃል በልቡ አኖረ፤ የጌ​ት​ንም ንጉሥ አን​ኩ​ስን እጅግ ፈራ። 13በፊ​ቱም መል​ኩን ለወጠ፤ በዚ​ያ​ችም ቀን አመ​ለጠ። በከ​ተ​ማ​ውም በር ከበሮ ይዞ በእጁ መታ፤ በበ​ሩም መድ​ረክ ላይ ተን​ፈ​ራ​ፈረ፤ ልጋ​ጉም በጢሙ ላይ ይወ​ርድ ነበር። 14አን​ኩ​ስም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “እነሆ፥ ይህ ሰው እብድ እንደ ሆነ አይ​ታ​ች​ኋል፤ ለምን ወደ እኔ አመ​ጣ​ች​ሁት? 15በፊቴ ያብድ ዘንድ ይህን ያመ​ጣ​ች​ሁት እኔ የእ​ብ​ዶች አለቃ ነኝን? እን​ዲህ ያለ​ውስ ወደ ቤቴ ይገ​ባ​ልን?” አላ​ቸው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in