YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 23

23
ዳዊት የቂ​አ​ላን ከተማ ከጥ​ፋት እንደ አዳነ
1ለዳ​ዊ​ትም፥ “እነሆ፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ቂአ​ላን ይወ​ጋሉ፤ አው​ድ​ማ​ው​ንም ይዘ​ር​ፋሉ” ብለው ነገ​ሩት። 2ዳዊ​ትም፥ “ልሂ​ድን? እነ​ዚ​ህ​ንስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ልም​ታን?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሂድ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ምታ፤ ቂአ​ላ​ንም አድን” አለው። 3የዳ​ዊ​ትም ሰዎች፥ “እነሆ፥ በዚህ በይ​ሁዳ መቀ​መጥ እን​ፈ​ራ​ለን፤ ይል​ቁ​ንስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ለመ​ዝ​ረፍ ወደ ቂአላ ብን​ሄድ እን​ዴት እን​ሆ​ና​ለን?” አሉት። 4ዳዊ​ትም ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መልሶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለ​ሁና ተነ​ሥ​ተህ ወደ ቂአላ ውረድ” አለው። 5ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ወደ ቂአላ ሄዱ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ተዋጉ፤ እነ​ር​ሱም ከፊቱ ሸሹ፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ማረኩ፤ በታ​ላ​ቅም አገ​ዳ​ደል ገደ​ሉ​አ​ቸው። ዳዊ​ትም በቂ​አላ የሚ​ኖ​ሩ​ትን አዳነ።
6እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የአ​ቤ​ሜ​ሌክ ልጅ አብ​ያ​ታር ወደ ዳዊት ወደ ቂአላ በኰ​በ​ለለ ጊዜ ኤፉ​ዱን ይዞ ወርዶ ነበር። 7ለሳ​ኦ​ልም ዳዊት ወደ ቂአላ እንደ መጣ ተነ​ገ​ረው፤ ሳኦ​ልም፥ “መዝ​ጊ​ያና መወ​ር​ወ​ሪያ ወዳ​ለ​ባት ከተማ ገብቶ ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጄ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ታል” አለ። 8ሳኦ​ልም ወደ ቂአላ ወር​ደው ይዋጉ ዘንድ፥ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹ​ንም ይከ​ብቡ ዘንድ ሕዝ​ቡን ሁሉ አዘዘ። 9ዳዊ​ትም ሳኦል በእ​ርሱ ለክ​ፋት ዝም እን​ደ​ማ​ይል ዐወቀ፤ ዳዊ​ትም ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኤፉድ ወደ​ዚህ አምጣ” አለው። 10ዳዊ​ትም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! በእኔ ምክ​ን​ያት ከተ​ማ​ዪ​ቱን ያጠፋ ዘንድ ሳኦል ወደ ቂአላ ሊመጣ እን​ደ​ሚ​ፈ​ልግ እኔ ባሪ​ያህ ፈጽሜ ሰም​ቻ​ለሁ። 11የቂ​አላ ሰዎ​ችስ ይከ​በ​ባ​ሉን? ባሪ​ያ​ህስ እንደ ሰማ ሳኦል በውኑ ይወ​ር​ዳ​ልን? የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! ለባ​ር​ያህ ንገ​ረው” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይወ​ር​ዳል” አለ። 12ዳዊ​ትም፥ “የቂ​አላ ሰዎች እኔ​ንና ሰዎ​ቼን በሳ​ኦል እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ና​ልን?” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​አ​ች​ኋል” ብሎ ተና​ገረ። 13ዳዊ​ትና ስድ​ስት መቶ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አራት መቶ” ይላል። የሚ​ሆኑ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ከቂ​አላ ወጡ፤ ወደ​ሚ​ሄ​ድ​በ​ትም ይከ​ተ​ሉት ነበር። ሳኦ​ልም ዳዊት ከቂ​አላ እንደ ሸሸ ሰማ፤ ስለ​ዚ​ህም ከመ​ው​ጣት ቀረ። 14ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ በጠ​ባቡ በማ​ሴ​ሬም ይኖር ነበር፥ በአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ውስ​ጥም በዚፍ ተራራ ምድረ በዳ ተቀ​መጠ፤ ሳኦ​ልም ሁል​ጊዜ ይፈ​ል​ገው ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእጁ አሳ​ልፎ አል​ሰ​ጠ​ውም። 15ዳዊ​ትም ሳኦል ሊፈ​ል​ገው እንደ ወጣ አየ፤ ዳዊ​ትም በቄኒ ዚፍ ምድረ በዳ በአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ውስጥ ይኖር ነበር። 16የሳ​ኦ​ልም ልጅ ዮና​ታን ተነ​ሥቶ ወደ ዳዊት ወደ ቄኒ ሄደ። እጁ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጸና። 17ለእ​ር​ሱም “የአ​ባቴ የሳ​ኦል እጅ አታ​ገ​ኝ​ህ​ምና አት​ፍራ፤ አን​ተም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆ​ና​ለህ፤ እኔም ከአ​ንተ በታች እሆ​ና​ለሁ፤ ይህን ደግሞ አባቴ ሳኦል ያው​ቃል” አለው። 18ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ፤ ዳዊ​ትም በቄኒ ውስጥ ተቀ​መጠ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ቤቱ ሄደ።
19የዚፍ ሰዎ​ችም ከአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ወደ ሳኦል ወደ ኮረ​ብ​ታው ወጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየ​ሴ​ሞን ቀኝ በጠ​ባቡ በኩል በኤ​ኬላ ኮረ​ብታ ላይ በቄኒ ውስጥ በማ​ሴ​ሬት በእኛ ዘንድ ተሸ​ሽጎ የለ​ምን? 20አሁ​ንም፦ ንጉሥ ሆይ! ለመ​ው​ረድ ፈቃ​ድህ ከሆነ ወደ እኛ ውረድ፤ በን​ጉሡ እጅ ጥሎ​ታ​ልና።” 21ሳኦ​ልም አለ፥ “እና​ንተ ስለ እኔ አዝ​ና​ች​ኋ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ባ​ረ​ካ​ችሁ ሁኑ፤ 22አሁ​ንም ደግሞ ሂዱና አዘ​ጋጁ፤ የተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ት​ንም፥ ያለ​በ​ት​ንም ቦታ ሁሉ እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ላ​ችሁ ፈጥ​ና​ችሁ ዕወቁ። 23እን​ግ​ዲህ ዕወቁ፤ ከአ​ያ​ችሁ በኋላ ከእ​ና​ንተ ጋር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ያ​ችም ምድር ካለ በይ​ሁዳ አእ​ላፍ ሁሉ እፈ​ት​ሻ​ታ​ለሁ።”#ዕብ. “እርሱ የሚ​ደ​በ​ቅ​በ​ት​ንና የሚ​ሸ​ሸ​ግ​በ​ትን ስፍራ እዩና ዕወቁ፤ በእር​ግ​ጥም ወደ እኔ ተመ​ለሱ፥ እኔም ከእ​ና​ንተ ጋር እሄ​ዳ​ለሁ፤ በም​ድ​ርም ውስጥ ቢሸ​ሸግ በይ​ሁዳ አእ​ላ​ፋት ሁሉ መካ​ከል እፈ​ል​ገ​ዋ​ለሁ” ይላል።
24የዚፍ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ከሳ​ኦል በፊት ሄዱ፤ ዳዊ​ትና ሰዎቹ ግን በየ​ሴ​ሞን ቀኝ በኩል በዓ​ረባ በማ​ዖን ምድረ በዳ ነበሩ። 25ሳኦ​ልና ሰዎ​ቹም ሊፈ​ል​ጉት ሄዱ፤ ለዳ​ዊ​ትም ነገ​ሩት፤ እር​ሱም በማ​ዖን ምድረ በዳ ወዳ​ለው ዓለት ወረደ፤ ሳኦ​ልም ያን በሰማ ጊዜ ዳዊ​ትን በማ​ዖን ምድረ በዳ ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ደው። 26ሳኦ​ልና ሰዎ​ቹም በተ​ራ​ራው በአ​ንድ ወገን ሄዱ፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም በተ​ራ​ራው በሌ​ላው ወገን ሄዱ። ዳዊ​ትም ከሳ​ኦል ፊት ያመ​ልጥ ዘንድ ተሰ​ውሮ ነበር። ሳኦ​ልና ሰዎቹ ዳዊ​ት​ንና ሰዎ​ቹን ለመ​ያዝ ከብ​በ​ዋ​ቸው ነበ​ርና። 27ወደ ሳኦ​ልም መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገ​ሩን ወር​ረ​ው​ታ​ልና ፈጥ​ነህ ና” አለው። 28ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ማሳ​ደ​ድን ትቶ ተመ​ለሰ። ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ሊዋጋ ሄደ። ስለ​ዚህ የዚያ ስፍራ ስም የመ​ለ​ያ​የት ዓለት ተባለ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in