YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 4

4
የቃል ኪዳኑ ታቦት መማ​ረክ
1በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ለጦ​ር​ነት በእ​ስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ላይ ተሰ​በ​ሰቡ። እስ​ራ​ኤ​ልም ሊዋ​ጉ​አ​ቸው ወጡ፤ በአ​ቤ​ኔ​ዜር አጠ​ገ​ብም ሰፈሩ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በአ​ፌቅ ሰፈሩ። 2ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን ለመ​ው​ጋት ተሰ​ለፉ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሸሹ፤ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ፊት ድል ሆኑ፤ ጦር​ነት በተ​ደ​ረ​ገ​በ​ትም ስፍራ ከእ​ስ​ራ​ኤል አራት ሺህ ሰዎች ተገ​ደሉ። 3ሕዝ​ቡም ወደ ሰፈር በተ​መ​ለሱ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ “ዛሬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ስለ​ምን ጣለን? በፊ​ታ​ችን እን​ድ​ት​ሄድ፥ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ንም እጅ እን​ድ​ታ​ድ​ነን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ከሴሎ እና​ምጣ” አሉ። 4ሕዝ​ቡም ወደ ሴሎ ላኩ፤ በኪ​ሩ​ቤ​ልም ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ከዚያ አመጡ፤ ሁለ​ቱም የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ። 5የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈር በገ​ባች ጊዜ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ታላቅ እል​ልታ አደ​ረጉ፤ ምድ​ሪ​ቱም አስ​ተ​ጋ​ባች። 6ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ል​ል​ታ​ውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ “በዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሰፈር ያለው ይህ ታላቅ የእ​ል​ልታ ድምፅ ምን​ድን ነው?” አሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ወደ ሰፈሩ እንደ ደረ​ሰች አስ​ተ​ዋሉ። 7ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ፈር​ተው፥ “አማ​ል​ክት ወደ እነ​ርሱ ወደ ሰፈር መጥ​ተ​ዋል” አሉ። ደግ​ሞም እን​ዲህ አሉ፥ “ወዮ​ልን! አቤቱ፥ ዛሬ አድ​ነን፤ ከዚህ አስ​ቀ​ድሞ እን​ዲህ ያለ ነገር አል​ሆ​ነ​ምና። 8ወዮ​ልን! ከእ​ነ​ዚህ ኀያ​ላን አማ​ል​ክት እጅ ማን ያድ​ነ​ናል? እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በም​ድረ በዳ በልዩ ልዩ መቅ​ሠ​ፍት የመቱ ናቸው። 9እና​ንተ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሆይ! በርቱ፤ ጐብዙ፤ እና​ንተ ባሪ​ያ​ዎች እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ኋ​ቸው ዕብ​ራ​ው​ያን ባሪ​ያ​ዎች እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ጓ​ችሁ በርቱ፤ ተዋጉ።” 10ከዚ​ህም በኋላ ተዋ​ጉ​አ​ቸው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ወደቁ፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው ሸሹ፤ እጅ​ግም ታላቅ ግድያ ሆነ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሠላሳ ሺህ እግ​ረ​ኞች ወደቁ። 11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ተማ​ረ​ከች፤ ሁለ​ቱም የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ሞቱ።
የዔሊ ሞት
12በዚ​ያም ቀን አንድ የብ​ን​ያም ሰው ከሰ​ልፍ እየ​በ​ረረ ወደ ሴሎ መጣ፤ ልብ​ሱም ተቀ​ድዶ ነበር፤ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ ነበር። 13በመ​ጣም ጊዜ ዔሊ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ልቡ ተና​ውጦ ነበ​ርና በመ​ን​ገድ ዳር በወ​ን​በሩ ላይ ተቀ​ምጦ ይጠ​ባ​በቅ ነበር፤ ሰው​ዬ​ውም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገብቶ ባወራ ጊዜ ከተ​ማ​ዪቱ ሁሉ ተጭ​ዋ​ጭ​ዋ​ኸች። 14ዔሊም የጩ​ኸ​ቱን ድምፅ በሰማ ጊዜ፥ “ይህ ጩኸት ምን​ድን ነው?” አለ። ሰው​ዬ​ውም ፈጥኖ መጣና ለዔሊ ነገ​ረው። 15ዔሊም የዘ​ጠና ስም​ንት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዘጠና” ይላል። ዓመት ሽማ​ግሌ ነበረ፤ ዐይ​ኖ​ቹም ፈዝ​ዘው አያ​ይም ነበር።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዔሊም በአ​ጠ​ገቡ የቆ​ሙ​ትን ሰዎች እን​ዲህ አላ​ቸው ይህ ድምፅ ምን​ድን ነው” የሚል ይጨ​ም​ራል። 16ሰው​ዬ​ው​ንም፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?”#“አንተ ከወ​ዴት ነህ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። አለው። እር​ሱም፥ “ጦር​ነቱ ከአ​ለ​በት ስፍራ የመ​ጣሁ እኔ ነኝ፥ ዛሬም ከሰ​ልፍ ሸሸሁ” አለ። እር​ሱም፥ “ልጄ ሆይ! ነገ​ሩስ እን​ዴት ሆነ?” አለው። 17ያም ሰው መልሶ፥ “እስ​ራ​ኤል ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፤ ደግ​ሞም በሕ​ዝቡ ዘንድ ታላቅ ግድያ ሆኖ​አል፥ ሁለ​ቱም ልጆ​ችህ አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ሞተ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ተማ​ር​ካ​ለች” አለው። 18የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት ባሰ​ባት ጊዜ በበሩ አጠ​ገብ ካለው ከወ​ን​በሩ ወደቀ፤ እርሱ ሸም​ግሎ፥ ደን​ግ​ዞም ነበ​ርና ጀር​ባው#ዕብ. “አን​ገቱ” ይላል። ተሰ​ብሮ ሞተ። እር​ሱም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አርባ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሃያ” ይላል። ዓመት ፈራጅ ነበረ።
የፊ​ን​ሐስ ሚስት አሟ​ሟት
19ምራ​ቱም የፊ​ን​ሐስ ሚስት አር​ግዛ ልት​ወ​ልድ ተቃ​ርባ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት እንደ ተማ​ረ​ከች፥ አማ​ቷና ባል​ዋም እንደ ሞቱ በሰ​ማች ጊዜ አለ​ቀ​ሰች፤ ከዚ​ያም በኋላ ወለ​ደች። ሕማ​ም​ዋም ተመ​ለ​ሰ​ባት። 20ወደ ሞትም በቀ​ረ​በች ጊዜ በዙ​ሪ​ያዋ ያሉት ሴቶች “ወንድ ልጅ ወል​ደ​ሻ​ልና አት​ፍሪ” አሉ​አት። እር​ስዋ ግን አል​መ​ለ​ሰ​ች​ላ​ቸ​ውም፤ ልብ​ዋም አያ​ስ​ታ​ው​ስም ነበር። 21እር​ስ​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ስለ ተማ​ረ​ከች፥ ስለ አማ​ቷና ስለ ባል​ዋም፦ የሕ​ፃ​ኑን ስም ዊቦ​ር​ኮ​ኢ​ቦት#ዕብ. “ኢካ​ቦድ” ይላል። ብላ ጠራ​ችው። 22እነ​ር​ሱም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ተማ​ር​ካ​ለ​ችና ክብር ከእ​ስ​ራ​ኤል ለቀቀ” አሉ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in