ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 2
2
1እንግዲህ እያዘንሁ ወደ እናንተ እንዳልመጣ በልቤ ይህን ወሰንሁ። 2እኔ ካሳዘንኋችሁማ እኔ ካሳዘንሁት በቀር ማን ደስ ያሰኘኛል? 3የእኔ ደስታ የሁላችሁ እንደ ሆነ በሁላችሁ አምኛለሁና በመጣሁ ጊዜ ደስ ሊያሰኙኝ ከሚገባቸው ኀዘን እንዳያገኘኝ ይህን ጻፍሁላችሁ። 4ከብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት የተነሣ በብዙ እንባ ይህን ጽፌላችኋለሁ፤ ነገር ግን እጅግ እንደምወዳችሁ እንድታውቁ ነው እንጂ እንድታዝኑ አይደለም።
5ማንም ያሳዘነኝ ቢሆን፥ እኔን ብቻ ያሳዘነ አይደለም። ከእናንተ አንድ ሳይቀር ሁላችሁንም አሳዘነ እንጂ፤ አሁንም ሥርዐት አላጸናባችሁም። 6እንደዚህ ላለው ሰው ከእናንተ ከብዙዎች ያገኘችው ይህች ተግሣጽ ትበቃዋለች። 7ደግሞም እንዲህ ያለው ሰው ከኀዘን ብዛት የተነሣ እንዳይዋጥ ይቅር ልትሉትና ልታጽናኑት ይገባል። 8ስለዚህም ከእርሱ ጋር ፍቅርን እንድታጸኑ እማልዳችኋለሁ። 9ስለዚህም በሁሉ ትታዘዙኝ እንደ ሆነ፥ ፈቃዳችሁን ዐውቅ ዘንድ ጻፍሁላችሁ። 10ይቅር የምትሉት ቢኖር፥ እኔም ከእናንተ ጋር ይቅር እለዋለሁ፤ እኔም ይቅር ያልሁትን በክርስቶስ ፊት ስለ እናንተ ይቅር ብያለሁ። 11ሰይጣን እንዳያታልለን አሳቡን የምንስተው አይደለምና።
ስለ እግዚአብሔር መንገድ
12ለክርስቶስም ወንጌል ጢሮአዳ በደረስሁ ጊዜ በእግዚአብሔር በሩ ተከፈተልኝ። 13#የሐዋ. 20፥1። ወንድሜን ቲቶን ስላላገኘሁት ለሰውነቴ ዕረፍት አላገኘሁም፤ ነገር ግን ከእርሱ ተለይች ወደ መቄዶንያ ሄድሁ።
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድል ስለ መንሣት
14በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር ድል በመንሣቱ የሚጠብቀን፥ በየሀገሩም ሁሉ የዕውቀቱን መዓዛ በእኛ የሚገልጥ እግዚአብሔር ይመስገን። 15በሚድኑትና በሚጠፉት ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ እኛ ነንና። 16የሞት መዓዛ የሚገባቸው ለሞት፥ የሕይወት መዓዛ የሚገባቸውም ለሕይወት ናቸው፤ ነገር ግን ይህ የሚገባው ማነው? 17የእግዚአብሔርን ቃል በሌላ ቀላቅለው እንደሚሸቅጡ እንደ ብዙዎች አይደለንምና፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላከ በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ እንናገራለን።
Currently Selected:
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 2: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: