ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 7
7
ሰውነትን ስለ ማንጻት
1ወንድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለሆን ራሳችንን እናንጻ፤ ሥጋችንን አናርክስ፤ ነፍሳችንንም አናሳድፍ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት የምንቀደስበትን እንሥራ። 2አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ ታገሡን፥#ግሪኩ “ልባችሁን አስፉልን” ይላል። የበደልነው የለም፤ የገፋነውም የለም፤#“የገፋነውም የለም” የሚለው በግሪኩ የለም። ያጠፋነውም የለም፤ የቀማነውም የለም። 3ይህንም የምለው በእናንተ ለመፍረድ አይደለም፤#ግእዙ “ለአድልዎ” ይላል። ለሞትም፥ ለሕይወትም ቢሆን እናንተ በልባችን እንዳላችሁ ፈጽሜ ተናግሬአለሁና። 4በእናንተ ዘንድ እንዲሁ ብዙ መወደድ አለኝ፤ ስለ እናንተም የምመካበት ብዙ ነው፤ መጽናናትንም አገኘሁ፤ ከመከራዬም#ግሪኩ “በመከራችን ሁሉ ደስታዬ በዛልኝ” ይላል። ሁሉ ይልቅ ደስታዬ በዛልኝ።
5 #
2ቆሮ. 2፥13። ወደ መቄዶንያም በደረስን ጊዜ ለሰውነታችን ጥቂት ስንኳን ዕረፍት አላገኘንም፤ በሁሉም መከራ አጸኑብን እንጂ፤ በውጭም መጋደል ነበር፤ በውስጥም ፍርሀት ነበር። 6ነገር ግን ያዘኑትን የሚያጽናና እርሱ እግዚአብሔር በቲቶ መምጣት አጽናናን። 7በመምጣቱ ብቻ አይደለም፤ በአጽናናችሁት ማጽናናትም ነው እንጂ፤ ለእኛ እንደምታስቡና እንደምትቀኑ ፍቅራችሁን ነግሮናል፤ ይህንም ሰምቼ ደስታዬ በእናንተ በዛ።
ስለሚገባ ኀዘን
8መጀመሪያ በጻፍሁት መልእክት ባሳዝናችሁም እንኳ አያጸጽተኝም፤ ብጸጸትም፥ እነሆ ያች መልእክት ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንዳሳዘነቻችሁ አያለሁ። 9አሁን ግን እኔ ስለ እርሷ በብዙ ደስ ይለኛል፤ ደስታዬም ስለ አዘናችሁ አይደለም፤ ንስሓ ልትገቡ ስለ አዘናችሁ እንጂ፤ ከእናንተ አንዱ ስንኳ እንዳይጠፋ፥ ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ አዝናችኋልና። 10ስለ እግዚአብሔር ተብሎ የሚደረግ ኀዘን የዘለዓለም ሕይወትን የሚያሰጥ#ግሪኩ “ጸጸት የሌለበት ንስሓ ነው” ይላል። ንስሓ ነው። ስለ ዓለም የሚደረግ ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል። 11እነሆ፥ ያ ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ ያደረጋችሁት ኀዘን ምንም የማታውቁ እስከ መሆን ደርሳችሁ፥ ራሳችሁን በበጎ ሥራና በንጽሕና እስክታጸኑ ድረስ፥ ትጋትንና ክርክርን፥ ቍጣንና ፍርሀትን፥ ናፍቆትንና ቅንዐትን፥ በቀልንም አደረገላችሁ፤ 12ይህን የጻፍሁላችሁ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ እንደ ተጋችሁ ይታወቅ ዘንድ ነው እንጂ ስለ በደለና ስለ ተበደለ ሰው አይደለም። 13ስለዚህም ተጽናንተናል፤ በመጽናናታችንም ስለ ቲቶ ደስታ አብልጦ ደስ አለን፤ በሁላችሁ ዘንድ ሰውነቱን አሳርፋችኋታልና። 14ስለ እናንተ ለእርሱ በተመካሁበት ሁሉ አላሳፈራችሁኝምና፤ ነገር ግን ሁሉን ለእናንተ በእውነት እንደ ተናገርን፥ እንደዚሁ ደግሞ በቲቶ ፊት ትምክህታችን እውነት ሆነ። 15#ግሪኩ “ፍቅሩ በእናንተ ላይ እጅግ በዝትዋል” ይላል።ስለዚህም እጅግ ያመሰግናችኋል፤ እንደ ታዘዛችሁለት፥ በመፍራትና በመደንገጥም እንደ ተቀበላችሁት ያስባችኋል። 16እኔም በሁሉ ነገር እተማመናችኋለሁና ደስ ይለኛል።
Currently Selected:
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 7: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: