YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 8

8
የመ​ቄ​ዶ​ንያ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን አስ​ተ​ዋ​ፅኦ
1ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ለመ​ቄ​ዶ​ንያ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት የተ​ሰ​ጠ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ። 2በብዙ መከራ ከመ​ፈ​ተ​ና​ቸው የተ​ነሣ ደስ​ታ​ቸው በዝ​ቶ​አ​ልና፤ በድ​ህ​ነ​ታ​ቸው ጥል​ቅ​ነ​ትም የለ​ጋ​ስ​ነ​ታ​ቸው ባለ​ጠ​ግ​ነት በዝ​ታ​ለ​ችና። 3እነ​ርሱ ሲቻ​ላ​ቸው፥ ሳይ​ቻ​ላ​ቸ​ውም እን​ስጥ በማ​ለት ቈራ​ጦች ለመ​ሆ​ና​ቸው ምስ​ክ​ራ​ቸው እኔ ነኝና። 4#ሮሜ 15፥26። ለቅ​ዱ​ሳን ስለ​ሚ​ሆ​ነው አገ​ል​ግ​ሎት እን​ዲ​ተ​ባ​በሩ ይህን ቸር​ነት መላ​ል​ሰው ማለ​ዱን። 5እነ​ርሱ አስ​ቀ​ድ​መው በፈ​ቃ​ዳ​ቸው፥#“በፈ​ቃ​ዳ​ቸው” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ ለእ​ኛም አሳ​ል​ፈው ሰጥ​ተ​ዋ​ልና እኛ እንደ አሰ​ብ​ነው አይ​ደ​ለም፤ 6#ግእዙ “ወአ​ስ​ተ​ፍ​ሥ​ሐኒ ቲቶ” ይላል።ይህ​ንም የቸ​ር​ነት ሥራ እንደ ጀመረ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ ዘንድ ቲቶን ማለ​ድ​ነው። 7በሁሉ ነገር በእ​ም​ነ​ትና በቃል፥ በዕ​ው​ቀ​ትም፥ በት​ጋ​ትም በእ​ና​ንተ ዘንድ በሆ​ነው ሁሉ እኛን በመ​ው​ደ​ዳ​ችሁ ፍጹ​ማን እንደ ሆና​ችሁ፥ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ይህ​ቺን ስጦታ አብዙ።
8በግድ የም​ላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ለዚህ ሥራ የሚ​ተ​ጉ​ለት አሉና የፍ​ቅ​ራ​ች​ሁን እው​ነ​ተ​ኛ​ነት አሁን መር​ምሬ ተረ​ዳሁ። 9የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ቸር​ነ​ቱን ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ርሱ ድህ​ነት እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለ​ጸጋ ሲሆን፥ ስለ እና​ንተ ራሱን ድሃ አደ​ረገ። 10በዚ​ህም የሚ​ጠ​ቅ​ማ​ች​ሁን እመ​ክ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይህን ከማ​ድ​ረ​ጋ​ችሁ በፊት ፈቅ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ ከአ​ምና ጀም​ሮም ይህን ጀም​ራ​ች​ኋል። 11አሁ​ንም አድ​ርጉ፤ ፈጽ​ሙም፤ መፍ​ቀድ ከመ​ሻት ነውና፤ ማድ​ረ​ግም ከማ​ግ​ኘት ነውና። 12ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም። 13በዚህ ወራት ተካ​ክ​ላ​ችሁ እን​ድ​ት​ኖሩ ነው እንጂ ሌላው እን​ዲ​ያ​ርፍ እና​ን​ተን የም​ና​ስ​ጨ​ንቅ አይ​ደ​ለም። 14ኑሮ​አ​ችሁ በሁሉ የተ​ካ​ከለ ይሆን ዘንድ፥ የእ​ና​ንተ ትርፍ የእ​ነ​ር​ሱን ጕድ​ለት ይመ​ላ​ልና፥ የእ​ነ​ር​ሱም ትርፍ የእ​ና​ን​ተን ጕድ​ለት ይመ​ላ​ልና። 15#ዘፀ. 16፥18። መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “ብዙ ያለው አላ​ተ​ረ​ፈም፤ ጥቂት ያለ​ውም አላ​ጐ​ደ​ለም።”
ስለ ቲቶና ጓደ​ኞቹ
16 # ግእዙ “ዘወ​ሀ​በነ ለነ ንጽ​ሐቅ... በከመ ይቤ ቲቶ” ይላል። በቲቶ ልብ ስለ እና​ንተ ያን መት​ጋት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው። 17ልመ​ና​ች​ን​ንም#ግእዙ “ሥላ​ጤ​ክሙ” ይላል። ተቀ​ብሎ፥ ጨክኖ ወደ እና​ንተ ይመጣ ዘንድ ቸኵ​ሏል። 18ስለ ወን​ጌል ትም​ህ​ርት አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ ያመ​ሰ​ገ​ኑ​ትን ወን​ድ​ማ​ች​ን​ንም ከእ​ርሱ ጋር ልከ​ናል። 19ይህም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብ​ርና የእ​ኛን በጎ ፈቃድ ለማ​ሳ​የት በም​ና​ገ​ለ​ግ​ል​ባት በዚች ጸጋ ከእኛ ጋር አንድ ይሆን ዘንድ በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ተሾመ። 20ስለ​ም​ና​ገ​ለ​ግ​ለው ስለ​ዚህ ለጋስ ስጦታ ማንም እን​ዳ​ይ​ነ​ቅ​ፈን እን​ጠ​ነ​ቀ​ቃ​ለን። 21#ምሳ. 3፥4። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ብቻ ያይ​ደለ፥ ነገር ግን በሰው ፊትም መል​ካ​ሙን ነገር እና​ስ​ባ​ለ​ንና። 22በብዙ የፈ​ተ​ን​ነ​ው​ንና በሁ​ሉም ነገር ትጉህ ሆኖ ያገ​ኘ​ነ​ውን አሁ​ንም በእ​ና​ንተ እጅግ ስለ​ሚ​ታ​መን ከፊት ይልቅ እጅግ ትጉ የሚ​ሆ​ነ​ውን ወን​ድ​ማ​ች​ንን ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ል​ካ​ለን። 23ቲቶም ቢሆን፥ ስለ እና​ንተ አብ​ሮኝ የሚ​ሠራ ጓደ​ኛዬ ነው፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ቢሆኑ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር#ግሪኩ “የክ​ር​ስ​ቶስ ክብር” ይላል። የአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሐዋ​ር​ያት ናቸው። 24አሁ​ንም መዋ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ንና እኛም በእ​ና​ንተ የም​ን​መ​ካ​በ​ትን ሥራ በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ፊት በግ​ልጥ አሳ​ዩ​አ​ቸው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in