ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 9
9
ስለ ቅዱሳን አገልግሎት
1ለቅዱሳን ስለሚደረገው አገልግሎት የምጽፍላችሁ ብዙ አለኝ#ግሪኩ “ልጽፍላችሁ አያስፈልግም” ይላል። 2እናንተ እንደምትተጉ አውቃለሁና፤ ስለዚህም “የአካይያ ሰዎች እኮ ከአምና ጀምሮ አዘጋጅተዋል” ብዬ በመቄዶንያ ሰዎች ዘንድ አመሰገንኋችሁ፤ እነሆም የእናንተ መፎካከር ብዙዎችን ሰዎች አትግቶአቸዋል። 3በዚህም ያመሰገንናችሁ ምስጋና በእነርሱ ዘንድ ሐሰት እንዳይሆንብን፥ እንደ ነገርናቸውም ተዘጋጅታችሁ እንዲያገኙአችሁ ወንድሞችን ወደ እናንተ ላክናቸው።#ግሪኩ “ላክኋቸው” ይላል። 4ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመጡና ሳታዘጋጁ ቢያገኙአችሁ እናንተ ታፍራላችሁ ባልልም እኛ ስለ እናንተ ከነገርናቸው የተነሣ እናፍራለን። 5ስለዚህም አስቀድመው ወደ እናንተ መጥተው በቅድሚያ የተናገራችኋትን በረከታችሁን እንዲያዘጋጁ ወንድሞችን ማለድሁ፤ እንደዚህም የተዘጋጀ ይሁን፤ በረከትን እንደምታገኙበት እንጂ በንጥቂያ እንደ ተወሰደባችሁ አይሁን።
6አሳንሶ የሚዘራ ለእርሱ እንዲሁ መከሩ ያንስበታል፤ በብዙ የሚዘራ ግን በብዙ ያመርታል። 7ሁሉ ልቡ እንደ ወደደ ያድርግ፤ በደስታ ይስጡ እንጂ በግድ አይሆንም፤ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና። 8እግዚአብሔር መልካሙን ነገር ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል፤ ፍጹም በረከቱንም ለዘወትር ያበዛላችሁ ዘንድ፥ ለሁሉም ታተርፉታላችሁ፤ በጎ ሥራ መሥራትንም ታበዛላችሁ። 9#መዝ. 111፥9። “በተነ፤ ለድሃም ሰጠ፤ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል” ብሎ መጽሐፍ እንደ ተናገረ። 10#ኢሳ. 55፥10። እርሱ ዘርን ለዘሪ ይሰጣል፤ እህልንም ለምግብ ይሰጣችኋል፤ ዘራችሁንም ያበዛላችኋል፤ የጽድቃችሁንም መከር ያበጃል። 11ለብዙ ሰዎች ስለ ሰጣችሁም የእግዚአብሔርን ምስጋና በምታደርግላችሁ ልግስና ሁሉ ባለጸጎች ትሆናላችሁ። 12ይህቺ የዚህ ሥራ አገልግሎት ግዳጅ የምትፈጽመው ለዚህ ለቅዱሳን ችግር መሟላት ብቻ አይደለም፤ በቅዱሳን ዘንድም#ግሪኩ “በብዙዎች ዘንድ” ይላል። ደግሞ የእግዚአብሔርን ምስጋና ታበዛለች። 13ክርስቶስ ላስተማራት ትምህርት ታዝዛችኋልና፥ ሁላችሁም ደስ ብሎአችሁና ተባብራችሁ አወጣጥታችኋልና በዚች በሃይማኖታችሁ ፈተና#ግሪኩ “በአገልግሎታችሁ ፈተና” ይላል። ምክንያት እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፤ 14እነርሱም ስለ እናንተ ይጸልያሉ፤ ስለ አደረባችሁ ታላቅ የእግዚአብሔር ጸጋም ሊያዩአችሁ ይመኛሉ። 15ስለማትመረመርና ባላሰቡአት ጊዜ ስለምትመጣው#“ባላሰቡአት ጊዜም ስለምትመጣው” የሚለው በግሪኩ የለም። ጸጋው እግዚአብሔር ይመስገን።
Currently Selected:
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2 9: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: