YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ካልእ 11

11
ዳዊት ኦር​ዮን እንደ አስ​ገ​ደ​ለው
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዓ​መቱ መጨ​ረሻ ነገ​ሥ​ታት ወደ ሰልፍ በሚ​ወ​ጡ​በት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮ​አ​ብን ከእ​ር​ሱም ጋር አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ ሰደደ። የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አጠፉ፤ አራ​ቦ​ት​ንም ከበቡ፤ ዳዊት ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቀርቶ ነበር።
2እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከም​ን​ጣፉ ተነሣ፤ በን​ጉ​ሥም ቤት በሰ​ገ​ነት ላይ ተመ​ላ​ለሰ፤ በሰ​ገ​ነ​ቱም ሳለ አን​ዲት ሴት ስት​ታ​ጠብ አየ፤ ሴቲ​ቱም እጅግ የተ​ዋ​በች መልከ መል​ካም ነበ​ረች። 3ዳዊ​ትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፤ አንድ ሰውም፥ “የኤ​ል​ያብ ልጅ የኬ​ጤ​ያ​ዊው የኦ​ርዮ ሚስት ቤር​ሳ​ቤህ አይ​ደ​ለ​ች​ምን?” አለው። 4ዳዊ​ትም መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልኮ አስ​መ​ጣት፤ ወደ እር​ሱም ገባች፤ ከር​ኵ​ሰ​ቷም ነጽታ ነበ​ርና ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤቷም ተመ​ለ​ሰች። 5ሴቲ​ቱም አረ​ገ​ዘች፤ ወደ ዳዊ​ትም “አር​ግ​ዤ​አ​ለሁ” ብላ ላከ​ች​በት።
6ዳዊ​ትም ወደ ኢዮ​አብ፦ ኬጤ​ያ​ዊ​ውን ኦር​ዮን ወዲህ ላከው ብሎ ላከ። ኢዮ​አ​ብም ኦር​ዮን ወደ ዳዊት ላከው። 7ኦር​ዮም ደርሶ ወደ እርሱ በገባ ጊዜ ዳዊት የኢ​ዮ​አ​ብ​ንና የሕ​ዝ​ቡን ደኅ​ን​ነት፥ ሰል​ፉም እን​ዴት እንደ ሆነ ጠየ​ቀው። 8ዳዊ​ትም ኦር​ዮን፥ “ወደ ቤትህ ሂድ፤ እግ​ር​ህ​ንም ታጠብ” አለው። ኦር​ዮም ከን​ጉሡ ቤት ሲወጣ አንድ የን​ጉሥ መል​እ​ክ​ተኛ ተከ​ተ​ለው።#ዕብ. “ከን​ጉሥ ስጦታ ተከ​ተ​ለው” ይላል። 9ኦርዮ ግን ከጌ​ታው አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ ጋር በን​ጉሥ ቤት ደጅ ተኛ፤ ወደ ቤቱም አል​ወ​ረ​ደም። 10“ኦርዮ ወደ ቤቱ አል​ሄ​ደም” ብለው ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ዳዊ​ትም ኦር​ዮን፥ “አንተ ከመ​ን​ገድ የመ​ጣህ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቤትህ አል​ወ​ረ​ድ​ህም?” አለው። 11ኦር​ዮም ለዳ​ዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦ​ትና እስ​ራ​ኤል፥ ይሁ​ዳም በድ​ን​ኳን ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ጌታዬ ኢዮ​አ​ብና የጌ​ታ​ዬም አገ​ል​ጋ​ዮች በሰፊ ሜዳ ሰፍ​ረ​ዋል፤ እኔ ልበ​ላና ልጠጣ ወይስ ከሚ​ስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄ​ዳ​ለ​ሁን? በሕ​ይ​ወ​ት​ህና በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ይህን ነገር አላ​ደ​ር​ገ​ውም” አለው። 12ዳዊ​ትም ኦር​ዮን፥ “ዛሬ ደግሞ በዚህ ተቀ​መጥ፤ ነገም አሰ​ና​ብ​ት​ሃ​ለሁ” አለው። ኦር​ዮም በዚያ ቀንና በነ​ጋው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጠ። 13ዳዊ​ትም ጠራው፤ በፊ​ቱም በላና ጠጣ፤ አሰ​ከ​ረ​ውም፤ ነገር ግን በመሸ ጊዜ ወጥቶ ከጌ​ታው አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር በም​ን​ጣፉ ላይ ተኛ፤ ወደ ቤቱም አል​ወ​ረ​ደም።
14በነ​ጋም ጊዜ ዳዊት ለኢ​ዮ​አብ ደብ​ዳቤ ጻፈ፤ በኦ​ር​ዮም እጅ ላከው። 15በደ​ብ​ዳ​ቤ​ውም፥ “ኦር​ዮን ጽኑ ሰልፍ ባለ​በት በፊ​ተ​ኛው ስፍራ አቁ​ሙት፤ ተወ​ግ​ቶም ይሞት ዘንድ ከኋላ ሽሹ” ብሎ ጻፈ። 16ኢዮ​አ​ብም ከተ​ማ​ዪ​ቱን በከ​በበ ጊዜ ጀግ​ኖች እን​ዳ​ሉ​በት በሚ​ያ​ው​ቀው ስፍራ ኦር​ዮን አቆ​መው። 17የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሰዎች ወጥ​ተው ከኢ​ዮ​አብ ጋር ተዋጉ፤ ከዳ​ዊ​ትም አገ​ል​ጋ​ዮች ከሕ​ዝቡ አን​ዳ​ንዱ ወደቁ፤ ኬጤ​ያ​ዊው ኦር​ዮም ደግሞ ሞተ። 18ኢዮ​አ​ብም የጦ​ር​ነ​ቱን ዜና ሁሉ ለዳ​ዊት ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ላከ፤ 19ለመ​ል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “የጦ​ር​ነ​ቱን ነገር ሁሉ ለን​ጉሡ ነግ​ረህ በፈ​ጸ​ምህ ጊዜ፤ 20ንጉሡ ቢቈጣ፥ እን​ዲ​ህም ቢል፦ ልትዋጉ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ለምን ቀረ​ባ​ችሁ? ከቅ​ጥሩ በላይ ፍላጻ እን​ዲ​ወ​ረ​ወር አታ​ው​ቁ​ምን? 21የኔር ልጅ የይ​ሩ​በ​ዓ​ልን ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን ማን ገደ​ለው? አን​ዲት ሴት ከቅ​ጥር ላይ የወ​ፍጮ መጅ ጥላ​በት የሞተ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቅጥሩ እን​ደ​ዚህ ቀረ​ባ​ችሁ? አን​ተም፦ ባሪ​ያህ ኬጤ​ያ​ዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ በለው።”
22የኢ​ዮ​አ​ብም መል​እ​ክ​ተኛ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ንጉሡ ሄደ። ደር​ሶም ኢዮ​አብ የነ​ገ​ረ​ውን የጦ​ር​ነ​ቱን ዜና ሁሉ ለዳ​ዊት ነገ​ረው። ዳዊ​ትም በኢ​ዮ​አብ ላይ ተቈጣ። ያንም መል​እ​ክ​ተኛ፥ “ትዋጉ ዘንድ ወደ ከተ​ማዋ ቅጥር ለምን ቀረ​ባ​ችሁ? በቅ​ጥ​ሩም እን​ደ​ም​ት​ቈ​ስሉ አታ​ው​ቁ​ምን? የይ​ሩ​በ​ዓል ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን ማን ገደ​ለው? አን​ዲት ሴት ከቅ​ጥር ላይ የወ​ፍጮ መጅ ጥላ​በት በቴ​ቤስ የሞተ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቅጥሩ ቀረ​ባ​ችሁ?” አለው። 23መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም ዳዊ​ትን፥ “ሰዎቹ በረ​ቱ​ብን፤ ወደ ሜዳም ወጡ​ብን፤ እኛም እስከ በሩ መግ​ቢያ ድረስ አሳ​ደ​ድ​ና​ቸው። 24ፍላ​ጻም የሚ​ወ​ረ​ውሩ በቅ​ጥሩ ላይ ሆነው በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ላይ ወረ​ወሩ፤ ከን​ጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖች አን​ዳ​ንድ ሞቱ፤ አገ​ል​ጋ​ይህ ኬጤ​ያ​ዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ” አለው። 25ዳዊ​ትም መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውን፥ “ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፥ አንድ ጊዜም ያን ይበ​ላ​ልና ይህ ነገር በዐ​ይ​ንህ አይ​ክፋ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ወ​ጉ​ትን አበ​ርታ፤ አፍ​ር​ሳ​ትም ብለህ ለኢ​ዮ​አብ ንገ​ረው፤ አን​ተም አጽ​ናው” አለው።
26የኦ​ር​ዮም ሚስት ባልዋ ኦርዮ እንደ ሞተ በሰ​ማች ጊዜ ለባ​ልዋ አለ​ቀ​ሰች። 27የል​ቅ​ሶ​ዋም ወራት ሲፈ​ጸም ዳዊት ልኮ ወደ ቤቱ አስ​መ​ጣት፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደ​ች​ለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደ​ረ​ገው ነገር ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሆነ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in