YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ተሰ​ሎ​ንቄ ሰዎች 2 3

3
ስለ ጸሎት የቀረበ ጥያቄ
1-2በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! የጌታ ቃል እንዲሮጥ፥ በእናንተም ዘንድ ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር፥ እምነትም ለሁሉ ስለማይሆን ከዐመፀኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ስለ እኛ ጸልዩ። 3ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው። 4የምናዛችሁንም አሁን እንድታደርጉ ወደ ፊትም ደግሞ እንድታደርጉ ስለ እናንተ በጌታ ታምነናል። 5ጌታም ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ወደ ክርስቶስም ትዕግሥት ልባችንን ያቅናው።
ስለ ሥራ ፈትነት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ
6ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን። 7እኛን ልትመስሉ እንዴት እንደሚገባችሁ ራሳችሁ ታውቃላችሁና፤ በእናንተ ዘንድ ያለ ሥርዐት አልሄድንምና፤ 8ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም። 9ይህም እኛን ልትመስሉ ራሳችንን እንደ ምሳሌ እንሰጣችሁ ዘንድ ነበር እንጂ፥ ያለ ሥልጣን ስለ ሆንን አይደለም። 10ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን “ሊሠራ የማይወድ አይብላ፤” ብለን አዘናችሁ ነበርና። 11ሥራ ከቶ ሳይሠሩ በሰው ነገር እየገቡ ያለ ሥርዐት ከእናንተ ዘንድ ስለሚሄዱ ስለ አንዳንዶች ሰምተናልና። 12እንደነዚህ ያሉትንም በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን ይበሉ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን፤ እንመክራቸውማለን። 13እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ! መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ።
14በዚህ መልእክት ለተላከ ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ተመልከቱት፤ ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር አትተባበሩ። 15ነገር ግን እንደ ወንድም ገሥጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቍጠሩት።
የመጨረሻ ሰላምታ
16የሰላምም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
17በገዛ እጄ የተጻፈ የእኔ የጳውሎስ ሰላምታ ይህ ነው፤ የመልእክቴ ሁሉ ማስረጃ ይህ ነው፤ እንዲህ እጽፋለሁ። 18የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in