YouVersion Logo
Search Icon

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 18

18
ጳው​ሎስ በቆ​ሮ​ን​ቶስ ከአ​ቂ​ላና ከጵ​ር​ስ​ቅላ ጋር እንደ ተገ​ናኘ
1ከዚህ በኋላ ጳው​ሎስ ከአ​ቴና ወጥቶ ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሄደ። 2አቂላ የሚ​ባል አንድ አይ​ሁ​ዳ​ዊም አገኘ፤ የት​ው​ልድ ሀገ​ሩም ጳን​ጦስ ነው፤ እር​ሱም ከጥ​ቂት ወራት በፊት ከኢ​ጣ​ልያ ተሰዶ መጣ፤ ሚስቱ ጵር​ስ​ቅ​ላም አብ​ራው ነበ​ረች፤ ቀላ​ው​ዴ​ዎስ አይ​ሁድ ከሮም እን​ዲ​ሰ​ደዱ አዝዞ ነበ​ርና ወደ እነ​ርሱ መጣ። 3ሥራ​ቸው አንድ ስለ ነበረ ድን​ኳን ሰፊ​ዎ​ችም ስለ ነበሩ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብሮ ኖረ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይሠሩ ነበር። 4ጳው​ሎ​ስም በየ​ሰ​ን​በቱ በም​ኵ​ራብ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር፤ አይ​ሁ​ድ​ንና አረ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ያሳ​ም​ና​ቸው ነበር።
5ሲላ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም ከመ​ቄ​ዶ​ንያ በወ​ረዱ ጊዜ ጳው​ሎስ፥ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ለአ​ይ​ሁድ እየ​መ​ሰ​ከረ ቃሉን በማ​ስ​ተ​ማር ይተጋ ነበር። 6እነ​ር​ሱም በተ​ቃ​ወ​ሙ​ትና በሰ​ደ​ቡት ጊዜ ልብ​ሱን አራ​ግፎ፥ “እን​ግ​ዲህ እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ደማ​ችሁ በራ​ሳ​ችሁ ላይ ነው፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ ወደ አሕ​ዛብ እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው። 7ከዚ​ያም አልፎ ስሙ ኢዮ​ስ​ጦስ ወደ​ሚ​ባል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ወደ​ሚ​ፈራ ሰው ቤት ገባ፤ ቤቱም በም​ኵ​ራብ አጠ​ገብ ነበር። 8የም​ኵ​ራብ አለቃ ቀር​ስ​ጶ​ስም ከነ​ቤተ ሰቡ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አመነ፤ ከቆ​ሮ​ን​ቶስ ሰዎ​ችም ብዙ​ዎች ሰም​ተው አም​ነው ተጠ​መቁ። 9ጌታ​ች​ንም ጳው​ሎ​ስን በሌ​ሊት ራእይ እን​ዲህ አለው፥ “አት​ፍራ፥ ነገር ግን ተና​ገር፥ ዝምም አት​በል፤ 10እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ማንም ሊጐ​ዳህ የሚ​ነ​ሣ​ብህ የለም፤ በዚች ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉ​ኝና።” 11ጳው​ሎ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እየ​አ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸው ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር በቆ​ሮ​ን​ቶስ ተቀ​መጠ።
12ጋል​ዮ​ስም የአ​ካ​ይያ አገረ ገዢ በሆነ ጊዜ አይ​ሁድ ተባ​ብ​ረው በጳ​ው​ሎስ ላይ ተነሡ፤ ወደ ሸን​ጎም አመ​ጡት። 13እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ይህ ሰው ኦሪ​ትን በመ​ቃ​ወም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ልኩ ዘንድ ሰዎ​ችን ያባ​ብ​ላል።” 14ጳው​ሎ​ስም ይመ​ል​ስ​ላ​ቸው ዘንድ አፉን ሊከ​ፍት ወድዶ ሳለ አገረ ገዢው ጋል​ዮስ መልሶ አይ​ሁ​ድን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ አይ​ሁድ ሆይ፥ የበ​ደ​ላ​ችሁ በደል ቢኖር፥ ወይም ሌላ በደል ቢኖ​ር​በት አቤ​ቱ​ታ​ች​ሁን በሰ​ማ​ሁና ባከ​ራ​ከ​ር​ኋ​ችሁ#“ባከ​ራ​ከ​ር​ኋ​ችሁ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ነበር። 15ስለ ትም​ህ​ር​ትና ስለ ስሞች፥ ስለ ሕጋ​ች​ሁም የም​ት​ከ​ራ​ከሩ ከሆነ ግን ለራ​ሳ​ችሁ ዕወቁ፤ እኔ እን​ዲህ ያለ ነገር ልሰማ አል​ፈ​ቅ​ድም።” 16ከሸ​ን​ጎ​ውም አባ​ረ​ራ​ቸው። 17አረ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ የም​ኵ​ራ​ቡን አለቃ ሶስ​ቴ​ን​ስን ይዘው በሸ​ንጎ ፊት ደበ​ደ​ቡት፤ የእ​ር​ሱም ነገር ጋል​ዮ​ስን ምንም አላ​ሳ​ዘ​ነ​ውም።
18 # ዘኍ​. 6፥18። ጳው​ሎ​ስም እንደ ገና በወ​ን​ድ​ሞቹ ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀ​መጠ፤ በሰ​ላ​ምም ሸኙ​ትና ወደ ሶርያ በባ​ሕር ተጓዘ፤ ጵር​ስ​ቅ​ላና አቂ​ላም አብ​ረ​ውት ነበሩ፤ ስእ​ለ​ትም ነበ​ረ​በ​ትና በክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ራሱን ተላጨ። 19ወደ ኤፌ​ሶ​ንም ደረሱ፤ በዚ​ያም ተዋ​ቸ​ውና እርሱ ብቻ​ውን ወደ ምኵ​ራብ ገብቶ አይ​ሁ​ድን ተከ​ራ​ከ​ራ​ቸው። 20እነ​ር​ሱም ብዙ ጊዜ እን​ዲ​ሰ​ነ​ብት ማለ​ዱት፤ ነገር ግን አል​ወ​ደ​ደም። 21ከዚ​ህም በኋላ በሚ​ሸ​ኙት ጊዜ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢፈ​ቅድ እን​ደ​ገና እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ አሁን ግን የሚ​መ​ጣ​ውን በዓል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላደ​ርግ እወ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው፤ ከኤ​ፌ​ሶ​ንም በመ​ር​ከብ ሄደ።
22ወደ ቂሳ​ር​ያም ደረሰ፤ ከዚ​ያም ወጥቶ ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ሰላ​ምታ ከሰጠ በኋላ ወደ አን​ጾ​ኪያ ሄደ። 23ጥቂት ቀንም ተቀ​መጠ፤ ከዚ​ያም ወጥቶ በገ​ላ​ት​ያና በፍ​ር​ግያ በኩል በተራ እየ​ዞረ ሄደ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ንም አጸ​ና​ቸው።
24በእ​ስ​ክ​ን​ድ​ር​ያም የሚ​ኖር፥ ንግ​ግር የሚ​ች​ልና መጽ​ሐ​ፍን የሚ​ያ​ውቅ አጵ​ሎስ የሚ​ባል አንድ አይ​ሁ​ዳዊ ሰው ወደ ኤፌ​ሶን መጣ። 25እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ የተ​ማረ ነበር፤ ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሊያ​ስ​ተ​ም​ርና ሊመ​ሰ​ክር ከልቡ የሚ​ተጋ ነበር፤ ነገር ግን የዮ​ሐ​ን​ስን ጥም​ቀት ብቻ ተጠ​ምቆ ነበር። 26እር​ሱም በም​ኵ​ራብ በግ​ልጥ ይና​ገር ጀመር፤ ጵር​ስ​ቅ​ላና አቂ​ላም በሰ​ሙት ጊዜ ወደ ማደ​ሪ​ያ​ቸው ወስ​ደው ፍጹም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ አስ​ረ​ዱት። 27ወደ አካ​ይ​ያም ሊሄድ በወ​ደደ ጊዜ ወን​ድ​ሞች አጽ​ና​ኑት፤ እን​ዲ​ቀ​በ​ሉ​ትም ወደ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ጻፉ​ለት፤ ወደ እነ​ር​ሱም በደ​ረሰ ጊዜ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ላመ​ኑት ብዙ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ትልቅ ርዳ​ታም ረዳ​ቸው። 28ተሰ​ብ​ስ​በው ሳሉም በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት አይ​ሁ​ድን በግ​ልጥ እጅግ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር፤ ስለ ኢየ​ሱ​ስም እርሱ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ከመ​ጻ​ሕ​ፍት ማስ​ረጃ ያመ​ጣ​ላ​ቸው ነበር።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Video for የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 18