የሐዋርያት ሥራ 9:17-18
የሐዋርያት ሥራ 9:17-18 አማ2000
ያንጊዜም ሐናንያ ሄደ፤ ወደ ቤትም ገባ፤ እጁንም ጫነበትና፥ “ወንድሜ ሳውል፥ በመንገድ ስትመጣ የታየህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታይና መንፈስ ቅዱስ ይመላብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮኛል” አለው። ያንጊዜም ፈጥኖ እንደ ቅርፊት ያለ ነገር ከዐይኖቹ ላይ ተገፎ ወደቀ፤ ዐይኖቹም ተገለጡ፤ ወዲያውም አየ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ።