ወደ ቈላስይስ ሰዎች 4
4
1 #
ኤፌ. 6፥9። ጌቶች ሆይ፥ ለአገልጋዮቻችሁ ትክክለኛውን አድርጉላቸው፤ እውነትንም ፍረዱ፤ በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና።
ስለ ወንጌል መስፋፋት መጸለይ እንደሚገባ
2በምስጋና እየተጋችሁ ለጸሎት ፅሙዳን ሁኑ። 3ስለ እርሱ የታሰርሁለትን የእግዚአብሔርን ምሥጢር እንድንናገር፥ እግዚአብሔር የቃሉን በር ይከፍትልን ዘንድ ለእኛም ደግሞ ጸልዩልን፤ ለምኑልንም፤ 4ልናገርም እንደሚገባኝ እገልጠው ዘንድ ጸልዩልኝ። 5#ኤፌ. 5፥16። ዘመኑን እየዋጃችሁ#“ዘመኑን እየዋጃችሁ” የሚለው በግሪኩ ብቻ። ከሃይማኖት ወደ ተለዩ ሰዎች በማስተዋል ሂዱ። 6ለእያንዳንዱ እንዴት እንደምትመልሱ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው እንደ ተቀመመ በጸጋ ይሁን።
የመምህሩ ዜና በደቀ መዝሙሩ
7 #
የሐዋ. 20፥4፤ 2ጢሞ. 4፥12። የተወደደ ወንድማችንና የታመነ አገልጋይ፥ በጌታ ሥራም ተባባሪያችን የሆነ ቲኪቆስ የእኔን ዜና ይነግራችኋል። 8#ኤፌ. 6፥21-22። ስለዚህ ሥራ ወደ እናንተ የላክሁት ዜናዬን ታውቁ ዘንድ፥ ልባችሁንም ያጽናና ዘንድ ነው። 9#ፊል. 1፥10-12። ወገናችሁ ከሆነው ከምንወደውና ከታመነው ወንድማችን ከአናሲሞስ ጋር፥ እነርሱ ሥራችንንና ያለንበትን ያስረዱአችኋል።
ሰላምታ ለደቀ መዛሙርት
10 #
የሐዋ. 19፥29፤ 27፥2፤ ፊልሞ. 24፤ የሐዋ. 12፥12፤ 25፤ 13፥13፤ 15፥37-39። ከእኔ ጋር የተማረከው አርስጥሮኮስ፥ ወደ እናንተ በሚመጣ ጊዜ ትቀበሉት ዘንድ ስለ እርሱ ያዘዝኋችሁ የበርናባስ የአባቱ ወንድም ልጅ ማርቆስም፥#ግሪኩ “የበርናባስ የወንድሙ ልጅ” ይላል። 11ኢዮስጦስ የተባለ ኢያሱም፥ ከግዙራን ሰዎች ወገን የሚሆኑ እነዚህ ሰላም ይሏችኋል። በእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ረዳቶች እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እነርሱም እኔን አጽናንተውኛል። 12#ቈላ. 1፥7፤ ፊልሞ. 23። ከእናንተ ወገን የሚሆን ኤጳፍራስም ሰላም ይላችኋል፥ እርሱ የክርስቶስ አገልጋይ ነው፤ እግዚአብሔር በሚወደው ነገር ሁሉ ምሉኣንና ፍጹማን እንድትሆኑ፥ ስለ እናንተ ዘወትር ይጸልያል፤ ይማልዳልም። 13እጅግ እንደሚወዳችሁና ስለ እናንተ በሎዶቅያና በኢያራ ከተማ ስላሉትም እንደሚቈረቈር እኔ ምስክሩ ነኝ። 14#2ጢሞ. 4፥10-11፤ ፊልሞ. 24። ወዳጃችን ባለ መድኃኒቱ ሉቃስም ሰላም ብሎአችኋል፤ ዴማስም ሰላም ይላችኋል። 15በሎዶቅያ ላሉት ወንድሞቻችንና ለንምፋን፥ በቤቱም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ። 16ይህችን መልእክት እናንተ አንብባችሁ፥ በቤተ ክርስቲያን ያነብቡአት ዘንድ ወደ ሎዶቅያ ላኩአት፤ ዳግመኛም እናንተ ከሎዶቅያ የጻፍኋትን መልእክት አንብቡአት። 17#ፊል. 2። አክርጳንም “ከእግዚአብሔር የተሾምህባትን መልእክትህን እንድትፈጽማት ተጠንቀቅ” በሉት።
18እኔ ጳውሎስ በእጄ ጽፌ ሰላም አልኋችሁ፤ እስራቴን አስቡ፤ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።
በሮሜ ተጽፋ በቲኪቆስ እጅ ወደ ቈላስይስ ሰዎች የተላከችው መልእክት ተፈጸመች።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። አሜን።
Currently Selected:
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 4: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: