ኦሪት ዘዳግም 17
17
1“በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና ነውር ወይም ክፉ ነገር ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ።
2“አምላክህ እግዚአብሔር ከሰጠህ ሀገሮች በአንዲትዋ ውስጥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን ቃል ኪዳኑን በማፍረስ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ክፋት የሠራ ቢገኝ፥ 3ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ላላዘዘህ ለፀሐይና ለጨረቃ ወይም ለሰማይ ከዋክብት የሰገደ ቢገኝ፥ 4ቢያወሩልህም#“ቢያወሩልህም” የሚለው በግእዙ የለም። ብትሰማም፥ ያን ፈጽመህ መርምር፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥ 5ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ታወጣቸዋለህ፥#ዕብ. “ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ” ይላል። እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትመትዋቸዋላችሁ። 6በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ሞት የሚገባቸው ይገደሉ፤ በአንድ ምስክር ግን አይገደሉ። 7እርሱን ለመግደል በመጀመሪያ የምስክሮች እጅ በኋላም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ትሁንበት፤ እንዲሁ ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።
በካህናትና ዳኞች የሚሰጡ የፍርድ ውሳኔዎች
8“በደምና በደም መካከል፥ በፍርድና በፍርድ መካከል፥ በመቍሰልና በመቍሰል መካከል፥ በክርክርና በክርክር መካከል በሀገርህ ውስጥ ሰዎች ስለሚከራከሩበት ክርክር የሚሳንህ የፍርድ ነገር ቢኖር፥ አንተ ተነሥተህ ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ትወጣለህ፤ 9ወደ ሌዋውያን ካህናት በዚያም ዘመን ወደ አሉ ፈራጆች መጥተህ ትጠይቃለህ፤ እነርሱም የፍርዱን ነገር ይነግሩሃል። 10ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ እንደ ነገሩህ ቃል ታደርጋለህ፤ ያስተማሩህንም ሕጉን ታደርግ ዘንድ ጠብቅ። 11እንዳስተማሩህም ሕግ፥#“እንዳስተማሩህም ሕግ” የሚለው በግእዙ የለም። እንደ ነገሩህም ፍርድ አድርግ፤ ከነገሩህ ፍርድ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል። 12ማናቸውም ሰው ቢኰራ፥ በአምላክህ እግዚአብሔር ስም ለማገልገል የሚቆመውን ካህኑን ወይም በዚያ ወራት ያለውን ፈራጁን ባይሰማ ያ ሰው ይሙት፤ ከእስራኤልም ዘንድ ክፉውን አስወግዱ፤ 13ሕዝቡም ሁሉ ሰምቶ ይፈራል፤ ከዚያም ወዲያ ደግሞ አይበድልም።
ስለ ንጉሥ የተሰጠ መመሪያ
14“አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በተቀመጥህባትም ጊዜ፦ በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ በላዬ አለቃ#ዕብ. “ንጉሥ አነግሣለሁ ...” ይላል። እሾማለሁ ብትል፥ 15ከወንድሞችህ መካከል አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን ለአንተ አለቃ ትሾማለህ፤#ዕብ. “ለአንተ ታነግሣለህ ...” ይላል። ወንድምህ ያልሆነውን ሌላ ሰው በአንተ ላይ መሾም አትችልም። 16ለእርሱ ፈረሶችን እንዳያበዛ፥ ሕዝቡንም ወደ ግብፅ እንዳይመልስ፤ እግዚአብሔር፦ በዚያች መንገድ መመለስን አትድገም ብሎአልና። 17ልቡም እንዳይስት ሚስቶችን ለእርሱ አያብዛ፤ ወርቅና ብርም ለእርሱ እጅግ አያብዛ።
18“በግዛቱም#ዕብ. “በመንግሥቱ ዙፋን ...” ይላል። በተቀመጠ ጊዜ ከሌዋውያን ካህናት ወስዶ ይህን ሁለተኛ ሕግ ለራሱ በመጽሐፍ ይጻፍ። 19መጽሐፉ ከእርሱ ጋር ይኑር፤ ዕድሜውንም ሁሉ ያንብበው። አምላኩን እግዚአብሔርን መፍራት ይማር ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ፥ ይህችንም ሥርዐት ጠብቆ ያደርግ ዘንድ፥ 20ልቡ በወንድሞቹ ላይ እንዳይኰራ፥ የአምላኩ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንዳይተው፥ ቀኝና ግራም እንዳይል፥ እርሱም ልጆቹም በእስራኤል ልጆች መካከል ረዥም ዘመን ይገዙ ዘንድ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 17: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: