YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘዳ​ግም 30

30
ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​መ​ለስ የሚ​ገኝ በረ​ከት
1“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እኔ በፊ​ትህ ያኖ​ር​ሁት ይህ ነገር ሁሉ፥ በረ​ከ​ቱና መር​ገሙ በወ​ረ​ደ​ብህ ጊዜ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​በ​ት​ንህ በዚያ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል ሆነህ በል​ብህ ዐስ​በው፤ 2ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተመ​ለስ፤ እኔም ዛሬ እን​ደ​ማ​ዝ​ዝህ ሁሉ አን​ተና ልጆ​ችህ በፍ​ጹም ልብና በፍ​ጹም ነፍስ ቃሉን ስማ፤ 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀጢ​አ​ት​ህን ይቅር ይል​ሃል#ዕብ. “ምር​ኮ​ህን ይመ​ል​ሳል” ይላል። ይራ​ራ​ል​ህ​ማል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን ከበ​ተ​ነ​በት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል መልሶ ይሰ​በ​ስ​ብ​ሃል። 4መበ​ተ​ን​ህም እስከ ሰማይ ዳርቻ ቢሆን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ ይሰ​በ​ስ​ብ​ሃል፤ ከዚ​ያም ያመ​ጣ​ሃል። 5አባ​ቶ​ች​ህም ወደ ወረ​ሱ​አት ምድር አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ ትወ​ር​ሳ​ት​ማ​ለህ፤ መል​ካ​ምም ነገር ያደ​ር​ግ​ል​ሃል፤ ከአ​ባ​ቶ​ች​ህም ይልቅ ያበ​ዛ​ሃል። 6በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ድ​ት​ኖር፥#በግ​እዙ “ከመ ትሕ​የው አንተ ወዘ​ር​እከ” ይላል። አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ እን​ድ​ት​ወ​ድድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ​ህን፥ የዘ​ር​ህ​ንም ልብ ያጠ​ራ​ዋል።#ዕብ. “ይገ​ር​ዛል” ይላል። 7አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን መር​ገም ሁሉ በጠ​ላ​ቶ​ች​ህና በሚ​ጠ​ሉህ በሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ህም ላይ ያመ​ጣ​ታል። 8አን​ተም ተመ​ል​ሰህ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ትሰ​ማ​ለህ፤ ዛሬም እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን ትእ​ዛ​ዙን ሁሉ ታደ​ር​ጋ​ለህ። 9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ባ​ቶ​ችህ ደስ እን​ዳ​ለው በመ​ል​ካሙ ነገር ሁሉ እንደ ገና በአ​ንተ ደስ ይለ​ዋ​ልና አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ፥ በሆ​ድ​ህም ፍሬ፥ በእ​ር​ሻ​ህም ፍሬ፥ በከ​ብ​ት​ህም ብዛት እጅግ ይባ​ር​ክ​ሃል። 10በዚህ የሕግ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን ትእ​ዛ​ዙን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱን ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ብት​ሰማ፥ በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብት​መ​ለስ ይባ​ር​ክ​ሃል።
ሕይ​ወ​ትና ሞት
11“እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዝህ ይህች ትእ​ዛዝ ከባድ አይ​ደ​ለ​ችም፤ ከአ​ን​ተም የራ​ቀች አይ​ደ​ለ​ችም። 12ሰም​ተን እና​ደ​ር​ጋት ዘንድ ስለ እኛ ወደ ሰማይ ወጥቶ እር​ስ​ዋን የሚ​ያ​መ​ጣ​ልን ማን​ነው? እን​ዳ​ትል በሰ​ማይ አይ​ደ​ለ​ችም። 13ሰም​ተን እና​ደ​ር​ጋት ዘንድ ስለ እኛ ባሕ​ሩን ተሻ​ግሮ እር​ስ​ዋን የሚ​ያ​መ​ጣ​ልን ማን ነው? እን​ዳ​ትል ከባ​ሕሩ ማዶ አይ​ደ​ለ​ችም። 14ታደ​ር​ገው ዘንድ ቃሉ በአ​ፍ​ህና በል​ብህ፥ በእ​ጅ​ህም ውስጥ ለአ​ንተ እጅግ ቅርብ ነው።
15“እነሆ፥ ዛሬ በፊ​ትህ ሕይ​ወ​ት​ንና ሞትን፥ መል​ካ​ም​ነ​ት​ንና ክፉ​ነ​ትን አኑ​ሬ​አ​ለሁ። 16ዛሬ እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛ​ዛት ብት​ሰማ፥ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ብት​ወ​ድድ፥ በመ​ን​ገ​ዶ​ቹም ሁሉ ብት​ሄድ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ፍር​ዱ​ንም ብት​ጠ​ብቅ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለህ፤ በቍ​ጥ​ርም ትበ​ዛ​ለህ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልት​ወ​ር​ሳት በም​ት​ሄ​ድ​ባት በም​ድ​ሪቱ ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል። 17ልብህ ግን ቢስት፥ አን​ተም ባት​ሰማ፥ ብት​ታ​ለ​ልም፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ብት​ሰ​ግድ፥ ብታ​መ​ል​ካ​ቸ​ውም፥ 18ፈጽ​መህ እን​ደ​ም​ት​ጠፋ እኔ ዛሬ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ረህ ትወ​ር​ሳት ዘንድ በም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ዘመ​ንህ አይ​ረ​ዝ​ምም። 19በፊ​ትህ ሕይ​ወ​ት​ንና ሞትን፥ በረ​ከ​ት​ንና መር​ገ​ምን እን​ዳ​ስ​ቀ​መ​ጥሁ እኔ ዛሬ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በአ​ንተ ላይ አስ​መ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ አን​ተና ዘርህ በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ ሕይ​ወ​ትን ምረጥ፤ 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ችህ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እን​ዲ​ሰ​ጣ​ቸው በማ​ለ​ላ​ቸው በም​ድ​ሪቱ ትቀ​መጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይ​ወ​ትህ፥ የዘ​መ​ን​ህም ርዝ​መት ነውና አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ውደ​ደው፤ ቃሉን ስማው፤ አጥ​ና​ውም።”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in