YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘዳ​ግም 32

32
1 # “እን​ዲ​ህም አለ” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። እን​ዲ​ህም አለ፦
“ሰማይ ሆይ፥ አድ​ምጥ፥ ልን​ገ​ርህ፤
ምድ​ርም የአ​ፌን ቃሎች ትስማ።
2ትም​ህ​ር​ቴ​ንም እንደ ዝናም ተስፋ ታድ​ር​ገው፤
ነገሬ እንደ ጠል ይው​ረድ፤
በእ​ር​ሻም ላይ እንደ ዝናም፥
በሣ​ርም ላይ እንደ ጤዛ።
3የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም እጠ​ራ​ለ​ሁና፤
ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ታላ​ቅ​ነ​ትን ስጡ።
4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሥ​ራው እው​ነ​ተኛ ነው፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራው ፍጹም ነው” ይላል።
መን​ገ​ዱም ሁሉ የቀና ነው፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው፤ ክፋ​ትም የለ​በ​ትም፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቅና ቸር ነው።
5እነ​ርሱ በደሉ፤ ልጆ​ቹም አይ​ደ​ሉም፤
ነው​ርም አለ​ባ​ቸው፤ ጠማ​ማና ገል​በ​ጥ​ባጣ ትው​ልድ ናቸው።
6ደን​ቆሮ፥ ብል​ሃ​ተ​ኛም ያል​ሆ​ንህ ሕዝብ ሆይ፥
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ትመ​ል​ሳ​ለ​ህን?
የፈ​ጠ​ረህ አባ​ትህ አይ​ደ​ለ​ምን?
የፈ​ጠ​ረ​ህና ያጸ​ናህ እርሱ ነው።
7የዱ​ሮ​ውን ዘመን አስብ፤
የልጅ ልጅ​ንም ዓመ​ታት አስ​ተ​ውል፤
አባ​ት​ህን ጠይቅ፥ ይነ​ግ​ር​ህ​ማል፤
ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ህን ጠይቅ፤ ይተ​ር​ኩ​ል​ህ​ማል።
8ልዑል አሕ​ዛ​ብን በከ​ፈ​ላ​ቸው ጊዜ፥
የአ​ዳ​ም​ንም ልጆች በለ​ያ​ቸው ጊዜ፥
እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ቍጥር፥
አሕ​ዛ​ብን በየ​ድ​ን​በ​ራ​ቸው አቆ​ማ​ቸው።#ዕብ. “እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ቍጥር የአ​ሕ​ዛ​ብን ድን​በር አቆመ” ይላል።
9ሕዝቡ ያዕ​ቆ​ብም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕድል ፋንታ ሆነ፤
እስ​ራ​ኤ​ልም#ዕብ. “ያዕ​ቆብ” ይላል። የር​ስቱ ገመድ ነው።
10በም​ድረ በዳ አጠ​ገ​ባ​ቸው፤
በጥ​ማ​ትና በድ​ካም ቦታ፥ በው​ድማ ከበ​ባ​ቸው፤
መገ​ባ​ቸው፤ መራ​ቸ​ውም፤
እንደ ዐይን ብሌ​ንም ጠበ​ቃ​ቸው።
11ንስር ጫጩ​ቶ​ቹን በክ​ን​ፎቹ በታች እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ስብ፥
በጎ​ኑም እን​ደ​ሚ​ያ​ቅፍ፥
በክ​ን​ፎቹ አዘ​ላ​ቸው፤
በደ​ረ​ቱም ተሸ​ከ​ማ​ቸው።
12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ​ውን መራ​ቸው፤
ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሌላ አም​ላክ አል​ነ​በ​ረም።
13በም​ድር ኀይል ላይ አወ​ጣ​ቸው፤
የእ​ር​ሻ​ው​ንም ፍሬ መገ​ባ​ቸው፤
ከዓ​ለ​ትም ድን​ጋይ በሚ​ገኝ ማር፥
ከጭ​ን​ጫ​ውም ድን​ጋይ በሚ​ገኝ ዘይት አሳ​ደ​ጋ​ቸው፤
14በላሙ ቅቤ፥ በበ​ጉም ወተት፥
ከፍ​የል ጠቦ​ትና ከላም፥ ከጊ​ደ​ሮ​ችና ከበ​ጎች ስብ ጋር፥
ከፍ​ትግ ስንዴ ጋር መገ​ባ​ቸው፤
የዘ​ለ​ላ​ው​ንም ደም የወ​ይን ጠጅ አድ​ር​ገው ጠጡ።
15ያዕ​ቆብ በላ፤ ጠገ​በም፤ የተ​ወ​ደ​ደ​ውን ጥጋብ አቀ​ና​ጣው፤
ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤
የፈ​ጠ​ረ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ሔ​ርን ተወ፤
ከሕ​ይ​ወቱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራቀ።
16በዚህ በልዩ ጣዖት አነ​ሣ​ሡኝ፤
በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውም አስ​መ​ረ​ሩኝ።
17ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ​ደለ ለአ​ጋ​ን​ንት፥
ለማ​ያ​ው​ቋ​ቸ​ውም አማ​ል​ክት፥
ድን​ገት ለተ​ገኙ ለማ​ይ​ሠ​ሩና ለማ​ይ​ጠ​ቅሙ አማ​ል​ክት፥
አባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ለማ​ያ​ው​ቋ​ቸው አማ​ል​ክት ሠዉ።
18የወ​ለ​ደ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተውህ፤
ያሳ​ደ​ገ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ረሳ​ኸው።
19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አይቶ ቀና፤
በወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችም ፈጽሞ ተቈጣ።
20እር​ሱም አለ፦ ፊቴን ከእ​ነ​ርሱ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤
በመ​ጨ​ረ​ሻው ዘመን ምን እንደ ሆነ አያ​ለሁ፤
ጠማማ ትው​ልድ፥
እም​ነት የሌ​ላ​ቸው ልጆች ናቸ​ውና።
21አም​ላክ ባል​ሆ​ነው አስ​ቀ​ኑኝ፤
በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አስ​ቈ​ጡኝ፤
እኔም ሕዝብ ባል​ሆ​ነው አስ​ቀ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤
በማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝ​ብም አስ​ቈ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።
22እሳት ከቍ​ጣዬ ትነ​ድ​ዳ​ለ​ችና፥
እስከ ሲኦል ድረስ ታቃ​ጥ​ላ​ለች፤
ምድ​ር​ንም ከፍ​ሬዋ፤ ጋር ትበ​ላ​ለች፤
የተ​ራ​ሮ​ችን መሠ​ረት ታነ​ድ​ዳ​ለች።
23ለመ​ከራ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤
ፍላ​ጻ​ዎ​ች​ንም እጨ​ር​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።
24በራብ ያል​ቃሉ፤
ለሰ​ማይ ወፎ​ችም መብል ይሆ​ናሉ፤
ኀይ​ላ​ቸ​ውም ይደ​ክ​ማል፥#ዕብ. “በን​ዳድ ያል​ቃሉ ፤ በረ​ኀ​ብና በመ​ራራ ጥፋት ያል​ቃሉ” ይላል።
ከም​ድር ይጠፉ ዘንድ የም​ድር አራ​ዊ​ትን ጥርስ፥
ከመ​ርዝ ጋር እል​ክ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።
25ጐል​ማ​ሳ​ውን ከድ​ን​ግል፥ ሕፃ​ኑ​ንም ከሽ​ማ​ግሌ ጋር፥
በሜዳ ሰይፍ፥ በቤ​ትም ውስጥ ድን​ጋጤ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።
26እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ፤
ከሰ​ዎ​ችም መካ​ከል መታ​ሰ​ቢ​ያ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ።
27ነገር ግን ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ይ​ታ​በዩ፦
እጃ​ችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ሁሉ አላ​ደ​ረ​ገም እን​ዳ​ይሉ፥
በቍጣ ጠላት ሆኑኝ።
28ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፤
ምግ​ባ​ርና ሃይ​ማ​ኖት የላ​ቸ​ውም።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ማስ​ተ​ዋል የላ​ቸ​ውም” ይላል።
29ይህ​ንም ያው​ቁት ዘንድ አላ​ሰ​ቡ​ትም፤
በሚ​መ​ጣ​ውም ዘመን አያ​ው​ቁ​ትም።
30አንዱ ሽሁን እን​ዴት ያሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል?
ሁለ​ቱስ ዐሥ​ሩን ሽህ እን​ዴት ያባ​ር​ሩ​አ​ቸ​ዋል?
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍዳ​ውን አም​ጥ​ቶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና።
አም​ላ​ካ​ች​ንም አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።
31አም​ላ​ካ​ችን እንደ አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምና፤
ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሰነ​ፎች ናቸው።
32ወይ​ና​ቸው ከሰ​ዶም ወይን፥
ሐረ​ጋ​ቸ​ውም ከገ​ሞራ ነው፤
ፍሬ​አ​ቸ​ውም ሐሞት ነው፤
ዘለ​ላ​ቸ​ውም መራራ ነው።
33የወ​ይን ጠጃ​ቸው የእ​ባብ መርዝ፥
የሚ​ገ​ድ​ልም የእ​ፉ​ኝት መርዝ ነው።
34በእኔ ዘንድ ያለው ትእ​ዛዝ ይህ አይ​ደ​ለ​ምን?
በመ​ዝ​ገ​ቤስ የታ​ተመ አይ​ደ​ለ​ምን?
35በፍ​ርድ ቀን እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤
እግ​ራ​ቸው በሚ​ሰ​ና​ከ​ል​በት ጊዜ፥
የጥ​ፋ​ታ​ቸው ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና፥
የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ላ​ች​ሁም ፈጥኖ ይደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ልና።
36እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ይፈ​ር​ዳል፤
ስለ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ይራ​ራል፤
በያ​ሉ​በት መሳ​ለ​ቂያ ሆነው እንደ ኖሩ፥
ኀይ​ላ​ቸ​ውም እንደ ደከመ፥
በጠ​ላ​ትም እጅ እንደ ወደቁ አይ​ቶ​አ​ልና።
37እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፦ ትታ​መ​ኑ​ባ​ቸው የነ​በ​ሩት አማ​ል​ክት የት አሉ?
38የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን ስብ የም​ት​በ​ሉ​ላ​ቸው፥
የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ች​ው​ንም ወይን የም​ት​ጠ​ጡ​ላ​ቸው፥
እነ​ርሱ ይነሡ፤ ይር​ዱ​አ​ች​ሁም፤
የሚ​ያ​ድ​ኑ​አ​ች​ሁም ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።
39እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥
ከእ​ኔም በቀር አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ።
እኔ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ አድ​ን​ማ​ለሁ፤
እኔ እገ​ር​ፋ​ለሁ፤ ይቅ​ርም እላ​ለሁ፤
ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።
40እጄን ወደ ሰማይ እዘ​ረ​ጋ​ለ​ሁና፥
በቀኜ እም​ላ​ለሁ፦ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም እኔ ሕያው ነኝ እላ​ለሁ።
41ሰይ​ፌን እንደ መብ​ረቅ እስ​ላ​ታ​ለሁ፤
እጄም ፍር​ድን ትይ​ዛ​ለች፤
ለሚ​ጠ​ሉ​ኝም ፍዳ​ቸ​ውን እከ​ፍ​ላ​ለሁ፤
ጠላ​ቶ​ች​ንም እበ​ቀ​ላ​ለሁ።
42ከተ​ወ​ጉት፥ ከተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ደም፥
ፍላ​ጻ​ዎ​ቼን በደም አሰ​ክ​ራ​ለሁ፤
ከጠ​ላት አለ​ቆ​ችም ራስ
ሰይፌ ሥጋን ትበ​ላ​ለች።
43ሰማ​ያት ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መላ​እ​ክት ሁሉ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል።#“ሰማ​ያት ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ደስ ይላ​ቸ​ዋል ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መላ​እ​ክት ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል” የሚ​ለው በዕብ. የለም።
አሕ​ዛ​ብም ከሕ​ዝቡ ጋር ደስ ይላ​ቸ​ዋል።
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ሁሉ እርሱ ጽኑዕ ነው ይላሉ፤
የል​ጆ​ቹን ደም ይበ​ቀ​ላ​ልና፥
ጠላ​ቶ​ቹ​ንም ይበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ልና፥
ለሚ​ጠ​ላ​ቸ​ውም ፍዳ​ቸ​ውን ይከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ልና፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕ​ዝ​ቡን ምድር ያነ​ጻል።”
44ሙሴም በዚ​ያች ቀን ይህ​ችን መዝ​ሙር ጻፋት፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አስ​ተ​ማ​ራት፤#“ሙሴም በዚ​ያች ቀን ይህ​ችን መዝ​ሙር ጻፋት ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አስ​ተ​ማ​ራት” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ሙሴም ገባ እር​ሱና የነዌ ልጅ ኢያ​ሱም የዚ​ህ​ችን ሕግ ቃሎች ሁሉ በሕ​ዝቡ ጆሮ ተና​ገሩ።
የሙሴ መጨ​ረሻ ምክር
45ሙሴም ይህን ቃል ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ተና​ግሮ ፈጸመ። 46እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ ልጆ​ቻ​ች​ሁን እን​ድ​ታ​ዝ​ዙ​በት ዛሬ የም​መ​ሰ​ክ​ር​ላ​ች​ሁን ቃል ሁሉ በል​ባ​ችሁ አኑ​ሩት። 47ይህ ነገር ሕይ​ወ​ታ​ችሁ ነው እንጂ ለእ​ና​ንተ ከንቱ አይ​ደ​ለ​ምና፤ በዚ​ህም ነገር ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ በም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ዘመ​ና​ችሁ ይረ​ዝ​ማል።”
የሙሴ ሞት መነ​ገሩ
48በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 49“በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምድር በዓ​ባ​ሪም ተራራ ውስጥ ወዳ​ለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ርስት አድ​ርጌ የም​ሰ​ጣ​ቸ​ውን የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር እያት፤ 50ወን​ድ​ምህ አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ፥ ወደ ወገ​ኖ​ቹም እንደ ተጨ​መረ፥ በወ​ጣ​ህ​በት ተራራ ሙት፤ ወደ ወገ​ኖ​ች​ህም ተጨ​መር፤ 51በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል በጺን ምድረ በዳ በቃ​ዴስ ባለው በክ​ር​ክር ውኃ ለቃሌ አል​ታ​ዘ​ዛ​ች​ሁ​ምና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች መካ​ከል አል​ቀ​ደ​ሳ​ች​ሁ​ኝ​ምና፥ 52ምድ​ሪ​ቱን ፊት ለፊት ታያ​ለህ እንጂ ወደ​ዚ​ያች#ዕብ. “እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ​ም​ሰ​ጣት ምድር” የሚል ይጨ​ም​ራል። ምድር አት​ገ​ባም።”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in