ወደ ገላትያ ሰዎች 6
6
ወንድምን ስለ ማጽናናት
1ወንድሞቻችን ሆይ፥ ከእናንተ ወገን የተሳሳተ ሰው ቢኖር በመንፈስ ቅዱስ የጸናችሁ እናንት እንዳትሳሳቱ ለራሳችሁ እየተጠበቃችሁ፥ እንደዚህ ያለውን ሰው ቅንነት ባለው ልቡና አጽኑት። 2ከእናንተ እያንዳንዱ የባልንጀራውን ሸክም ይሸከም፤ በዚህም የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ። 3አንዱም ምንም ሳይሆን ምንም የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና።#ግእዙ “አልቦ ዘያስሕት ርእሶ” ይላል። 4ለሌላ ያይደለ ለራሱ መመኪያ እንዲሆነው ሁሉም ሥራዉን ይመርምር። 5ሁሉም ሸክሙን ይሸከማልና።
6ይህንም ነገር ንኡሰ ክርስቲያን ይስማው፤ መልካሙንም ነገር ሁሉ ከሚያስተምረው ይማር። 7አያስቱአችሁ፤ በእግዚአብሔርም የሚዘብት አይኑር፤ ሰውም የሚዘራውን ያጭዳል። 8በሥጋው የሚዘራ ሞትን ያጭዳል፤ በመንፈሱም የሚዘራ የዘለዓለም ሕይወትን ያጭዳል። 9በጎ ሥራ መሥራትን ቸል አንበል፥#ግሪኩ “ባንዝልም” የሚል አለው። በጊዜው እናገኘዋለንና። 10እንግዲህ ጊዜ ሳለን ለሁሉ መልካም ሥራ እናድርግ፤ ይልቁንም ለሃይማኖት ሰዎች።
ምክርና ቡራኬ
11በእጄ እንደ ጻፍሁላችሁ እዩ።#ግሪኩ “እንዴት ባሉ ታላላቅ ፊደላት እንደጻፍሁላችሁ ...” ይላል። 12ለሰው ፊት ሊያደሉ የሚወዱ እነዚያ እንድትገዘሩ ያስገድዱአችኋል፤ ነገር ግን የክርስቶስን መስቀል እንዳትከተሉ ነው።#ግሪኩ “ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ነው” ይላል። 13የተገዘሩትም ቢሆኑ በሰውነታችሁ እንደምትመኩ ልትገዘሩ ይወዳሉ እንጂ ኦሪትን አልጠበቁም። 14እኔ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንጂ በሌላ አልመካም፤ በእኔ ዘንድ ዓለሙ የሞተ ነው፥ እኔም በዓለሙ ዘንድ የሞትሁ ነኝ።#ግሪኩ “ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት፥ እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክሕት ከእኔ ይራቅ” ይላል። 15በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ አዲስ ፍጥረት መሆን ነው እንጂ መገዘር አይጠቅምም፤ አለመገዘርም ግዳጅ አይፈጽምም። 16ይህን ሕግ ለሚፈጽሙ ሰዎች ሰላምና ይቅርታ ይሁን፤ የእግዚአብሔር ወገኖች በሆኑ በእስራኤል ላይም ይሁን።
17እንግዲህ ወዲህስ የሚያደክመኝ አይኑር፤ እኔ የኢየሱስ ክርስቶስን መከራ#ግሪኩ “የኢየሱስ ክርስቶስን ማሕተም” ይላል። በሥጋዬ እሸከማለሁ። 18ወንድሞች ሆይ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።
በሮሜ ተጽፋ በቲቶ እጅ ወደ ገላትያ ሰዎች የተላከች መልእክት ተፈጸመች።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ አሜን።
Currently Selected:
ወደ ገላትያ ሰዎች 6: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: