YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 12

12
ጌታን ስለ መከ​ተል
1እን​ግ​ዲህ እነ​ዚ​ህን የሚ​ያ​ህሉ ምስ​ክ​ሮች እንደ ደመና በዙ​ሪ​ያ​ችን ካሉ​ልን እኛ ደግሞ ሸክ​ምን ሁሉ፥ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ጭን​ቀት ከእኛ አስ​ወ​ግ​ደን፥ በፊ​ታ​ችን ያለ​ውን ሩጫ በት​ዕ​ግ​ሥት እን​ሩጥ። 2የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።
3በነ​ፍ​ሳ​ችሁ ዝላ​ችሁ እን​ዳ​ት​ደ​ክሙ፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች በደ​ረ​ሰ​በት እን​ዲህ ባለ መቃ​ወም የጸ​ና​ውን እስኪ ዐስ​ቡት። 4ገና አል​ጸ​ና​ች​ሁ​ምና ደማ​ች​ሁን ለማ​ፍ​ሰስ እስ​ክ​ት​ደ​ርሱ ኀጢ​አ​ትን ተጋ​ደ​ሉ​ኣት፥ አሸ​ን​ፉ​ኣ​ትም፤ ተስ​ፋ​ች​ሁን የም​ታ​ገ​ኙ​ባ​ትን ትም​ህ​ር​ትም ውደ​ዷት። 5እንደ ልጆ​ችም ከእ​ና​ንተ ጋር፥ “ልጄ ሆይ፥ የጌ​ታን ቅጣት አታ​ቅ​ልል በሚ​ገ​ሥ​ጽ​ህም ጊዜ አት​ድ​ከም። 6#ኢዮብ 5፥17፤ ምሳ. 3፥11-12። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ደ​ውን ይገ​ሥ​ጻ​ልና፥ የሚ​ወ​ደ​ደ​ው​ንም ልጅ ሁሉ ይገ​ር​ፈ​ዋል” ብሎ የሚ​ነ​ጋ​ገ​ረ​ውን ምክር ረስ​ታ​ች​ኋል። 7ቅጣ​ታ​ች​ሁን ታገሡ፤ ልጆቹ እንደ መሆ​ና​ችሁ ይወ​ዳ​ች​ኋ​ልና፤ አባቱ የማ​ይ​ቈ​ጣው ልጅ ማን ነው? 8ነገር ግን ሁሉ የቅ​ጣት ተካ​ፋይ ሆኖ​አ​ልና፥ ያለ ቅጣት ብት​ኖሩ ዲቃ​ሎች እንጂ ልጆች አይ​ደ​ላ​ች​ሁም። 9በሥጋ የወ​ለ​ዱን አባ​ቶ​ቻ​ችን የሚ​ቀ​ጡን፥ እኛም የም​ን​ፈ​ራ​ቸው ከሆነ፥ እን​ግ​ዲያ ይል​ቁን ለመ​ን​ፈስ አባ​ታ​ችን ልን​ታ​ዘ​ዝና ልን​ገዛ በሕ​ይ​ወ​ትም ልን​ኖር እን​ዴት ይገ​ባን ይሆን? 10እነ​ርሱ መል​ካም ሆኖ እንደ ታያ​ቸው ለጥ​ቂት ቀን ይቀ​ጡ​ናል፤ እርሱ ግን ከቅ​ድ​ስ​ናው እን​ድ​ን​ካ​ፈል ለጥ​ቅ​ማ​ችን ይቀ​ጣ​ናል። 11ቅጣት ሁሉ በጊ​ዜው ያሳ​ዝ​ናል እንጂ ደስ አያ​ሰ​ኝም፤ በኋላ ግን ለተ​ቀጡ ሰላ​ምን ያፈ​ራል፤ ጽድ​ቅ​ንም ያሰ​ጣ​ቸ​ዋል።
12 # ኢሳ. 35፥3። ስለ​ዚ​ህም የላ​ሉ​ትን እጆች፥ የሰ​ለ​ሉ​ት​ንም ጕል​በ​ቶች አቅኑ። 13#ምሳ. 4፥26። አን​ካ​ሳ​ነ​ታ​ችሁ እን​ዲ​ድ​ንና እን​ዳ​ት​ሰ​ነ​ካ​ከሉ ለእ​ግ​ሮ​ቻ​ችሁ የቀና መን​ገ​ድን አድ​ርጉ። 14ከሁሉ ጋር ወደ ሰላም ሩጡ፤ ቅድ​ስ​ና​ች​ሁ​ንም አት​ተዉ፤ ያለ እርሱ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​የው የለም። 15#ዘዳ. 29፥18። አስ​ተ​ውሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጸጋ የሚ​ያ​ቃ​ልል አይ​ኑር፤ ሕማ​ምን የም​ታ​መጣ፥ ብዙ​ዎ​ች​ንም የም​ታ​ስ​ታ​ቸ​ውና የም​ታ​ረ​ክ​ሳ​ቸው መራራ ሥር የም​ት​ገ​ኝ​በ​ትም አይ​ኑር። 16#ዘፍ. 25፥29-34። ለጥ​ቂት መብል ብኵ​ር​ና​ውን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ሴሰ​ኛና ርኩስ የሚ​ሆን አይ​ኑር። 17#ዘፍ. 27፥30-40። ከዚያ በኋላ እንኳ በረ​ከ​ትን ሊወ​ርስ በወ​ደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና፤ በእ​ን​ባም ተግቶ ምንም ቢፈ​ል​ጋት ለን​ስሓ ስፍራ አላ​ገ​ኘ​ምና።
18ሊዳ​ሰስ ወደ​ሚ​ችል ወደ​ሚ​ቃ​ጠ​ልም እሳት ወደ ጭጋ​ግም፥ ወደ ጨለ​ማም ወደ ዐውሎ ነፋ​ስም፥ 19#ዘፀ. 19፥16-22፤ 20፥18-21፤ ዘዳ. 4፥11-12፤ 5፥22-27። ወደ መለ​ከት ድም​ፅም፥ ወደ ቃሎ​ችም ነገር አል​ደ​ረ​ሳ​ች​ሁ​ምና፥ ያንም ነገር የሰ​ሙት ሌላ ቃል እን​ዳ​ይ​ጨ​መ​ር​ባ​ቸው ለመኑ። 20#ዘፀ. 19፥12-13። የተ​ነ​ጋ​ገ​ራ​ቸ​ውን ሊሰ​ሙት አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ርና፥ “እን​ስ​ሳም ያን ተራራ ቢቀ​ር​በው በድ​ን​ጋይ ይወ​ግ​ሩት” ነበር። 21#ዘዳ. 9፥19። የታ​ያ​ቸ​ውም እን​ዲህ ግሩም ነበር፤ ሙሴም እን​ኳን፥ “እኔ ፈር​ቻ​ለሁ፥ ደን​ግ​ጫ​ለ​ሁም” አለ። 22እና​ንተ ግን፥ የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ ወደ​ም​ት​ሆን ወደ ጽዮን ተራራ፥ በሰ​ማ​ያት ወደ አለ​ችው ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ደስ ብሎ​አ​ቸው ወደ​ሚ​ኖሩ አእ​ላፍ መላ​እ​ክ​ትም ደር​ሳ​ች​ኋል። 23ስማ​ቸው በሰ​ማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅ​በረ በኵ​ርም፥ ሁሉን ወደ​ሚ​ገ​ዛም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ወደ ፍጹ​ማን ጻድ​ቃ​ንም ነፍ​ሳት፥ 24#ዘፍ. 4፥10። የአ​ዲስ ኪዳ​ንም መካ​ከ​ለኛ ወደ​ሚ​ሆን ወደ ኢየ​ሱስ፥ ከአ​ቤ​ልም ደም ይልቅ የሚ​ሻ​ለ​ውን ወደ​ሚ​ና​ገር ወደ ተረ​ጨው ደሙ ደር​ሳ​ች​ኋል።
25 # ዘፀ. 20፥22። ለሚ​ና​ገ​ረው እንቢ እን​ዳ​ትሉ ተጠ​ን​ቀቁ፤ እነ​ርሱ በደ​ብረ ሲና የተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸ​ውን እንቢ ስለ አሉት ካል​ዳኑ፥ ከሰ​ማይ ከመ​ጣው ፊታ​ች​ንን ብን​መ​ልስ እኛማ እን​ዴታ? 26#ሐጌ. 2፥6። ያን​ጊዜ ቃል ምድ​ርን አና​ወ​ጣት፤ “አሁ​ንም እኔ ምድ​ርን እንደ ገና አንድ ጊዜ አና​ው​ጣ​ታ​ለሁ” ብሎ ተና​ገረ፤ ምድ​ርን ብቻም አይ​ደ​ለም፤ ሰማ​ይ​ንም ጭምር እንጂ። 27አንድ ጊዜ ደግሞ ያለ​ውም ፍጡ​ራን ናቸ​ውና፥ የማ​ይ​ና​ወ​ጠው ይኖር ዘንድ፥ የሚ​ና​ወ​ጠ​ውን እን​ደ​ሚ​ያ​ሳ​ል​ፈው ያሳ​ያል። 28ስለ​ዚህ የማ​ይ​ና​ወጥ መን​ግ​ሥ​ትን ስለ​ም​ን​ቀ​በል በማ​ክ​በ​ርና በፍ​ር​ሀት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ እያ​ሰ​ኘን የም​ና​መ​ል​ክ​በ​ትን ጸጋ እን​ያዝ። 29#ዘዳ. 4፥24። አም​ላ​ካ​ችን በእ​ው​ነት የሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት ነውና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in