ትንቢተ ኢሳይያስ 23
23
በጢሮስ ላይ የተነገረ ትንቢት
1ስለ ጢሮስ የተነገረ ትንቢት። የኬልቀዶን #ዕብ. “የተርሴስ” ይላል። መርከቦች ሆይ፥ አልቅሱ፤ ጠፍተዋልና፤ እንግዲህም ከኬጤዎን ሀገር አይመጡምና ማርከውም ይወስዱአቸዋልና።#ዕብ. “ቤት የለም ፤ መግባትም የለም” ይላል። 2በደሴት የሚኖሩ በባሕር የሚሻገሩ የፊኒቄ ስደተኞች#ዕብ. “ነጋዴዎች” ይላል። ምን ይመስላሉ? 3የገቡ ስደተኞች አሕዛብ በመከር ጊዜ እንደሚለወጥ ዘር ናቸው። 4ሲዶና ሆይ፥ ባሕር፥ የባሕር ምሽግ፥ “አላማጥሁም፥ አልወለድሁም፤ ጐበዛዝትንም አላሳደግሁም፥ ደናግልንም አላሳደግሁም” ብሎ ተናግሮአልና እፈሪ። 5ወሬዋ ወደ ግብፅ በደረሰ ጊዜ ስለ ጢሮስ ምጥ ይይዛቸዋል። 6ወደ ኬልቄዶን ተሻገሩ፤ እናንተ በደሴት የምትኖሩ፥ አልቅሱ። 7ተማርካችሁ ሂዱ እንጂ ይህች ዕረፍት የእናንተ አይደለችም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. ልዩ ነው። 8በጢሮስ ላይ ይህን የመከረ ማን ነው? እርስዋ ከሁሉ የምትሻልና የምትበልጥ አይደለችምን? ነጋዴዎችዋ የከበሩ የምድር አለቆች ናቸው። 9የክቡራንን ትዕቢት ይሽር ዘንድ፥ የምድርንም ክቡራን ሁሉ ያዋርድ ዘንድ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኖታል። 10ምድርህን እረስ፤ እንግዲህ መርከቦች ከኬልቀዶን አይመጡምና። 11ነገሥታቱን ያበሳጨቻቸው የባሕር ሰዎች እጃቸው ትደክማለች፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም የከነዓንን ኀይል ያጠፉ ዘንድ አዘዘ። 12እርሱም፥ “አንቺ የተበደልሽ የሲዶና ድንግል ልጅ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ደስ አይበልሽ፤ ተነሥተሽ ወደ ኪቲም ተሻገሪ፤ በዚያም ደግሞ አታርፊም” አለ። 13እነሆ፥ የከለዳውያንን ሀገር አሦራውያን አጥፍተዋታልና፤ ግንብዋም ወድቆአል፤ 14እናንተ የኬልቀዶን መርከቦች ሆይ፥ ምሽጋችሁ ፈርሶአልና ዋይ በሉ።
15በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ጢሮስ እንደ አንድ ንጉሥ ዘመን ወይም እንደ አንድ ሰው ዘመን ሰባ ዓመት ያህል የተረሳች ትሆናለች፤ ከሰባ ዓመት በኋላ ግን ለጢሮስ በጋለሞታ ዘፈን እንደሚሆን እንዲሁ ይሆናል። 16አንቺ የተረሳሽ ጋለሞታ ሆይ፥ መሰንቆ ያዢ፤ በከተማ ላይም ዙሪ፤ መታሰቢያም ይሆንልሽ ዘንድ ዜማን አሳምሪ፤ ዘፈንሽንም አብዢ። 17ከሰባ ዓመትም በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን በይቅርታ ይጐበኛታል፤ ወደ ጥንቷም ትመለሳለች፤ ደግሞም ለዓለም መንግሥታት ሁሉ መናገሻና መናገጃ ትሆናለች። 18ንግድዋና ዋጋዋ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ንግድዋም በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖሩ ለመብላትና ለመጠጣት፥ ለመጥገብም፥ በእግዚአብሔርም ፊት ለመታሰቢያ ይሆናል እንጂ ለእነርሱ አይሰበሰብም።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 23: አማ2000
Highlight
Share
Copy
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fen.png&w=128&q=75)
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

: