YouVersion Logo
Search Icon

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 30

30
በግ​ብፅ መታ​መን ከንቱ ስለ መሆኑ
1ለዐ​መ​ፀ​ኞች ልጆች ወዮ​ላ​ቸው! ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከእኔ ዘንድ ያል​ሆ​ነን ምክር ይመ​ክ​ራሉ፤ ኀጢ​አ​ት​ንም በኀ​ጢ​አት ላይ ይጨ​ምሩ ዘንድ ከመ​ን​ፈሴ ዘንድ ያል​ሆ​ነ​ውን ቃል ኪዳን ያደ​ር​ጋሉ። 2እኔን ሳይ​ጠ​ይቁ በፈ​ር​ዖን ኀይል ይረዱ ዘንድ በግ​ብ​ፅም ይጠ​በቁ ዘንድ ወደ ግብፅ ይሄ​ዳሉ። 3ስለ​ዚህ የፈ​ር​ዖን ኀይል እፍ​ረት፥ በግ​ብፅ መታ​መ​ንም ስድብ ይሆ​ን​ባ​ች​ኋል። 4አለ​ቆች ምንም በጣ​ኔ​ዎስ ቢሆኑ፥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ምንም ወደ ሓኔስ ቢደ​ርሱ፥ 5ሁላ​ቸው ይጠ​ቅ​ሙ​አ​ቸው ዘንድ ስለ​ማ​ይ​ችሉ፥ እፍ​ረ​ትና ስድብ እንጂ ረድ​ኤ​ትና ረብ ስለ​ማ​ይ​ሆኑ ሕዝብ ያፍ​ራሉ።
በም​ድረ በዳ ስላሉ እን​ስ​ሶች የታየ ራእይ
6ተባ​ትና እን​ስት አን​በሳ፥ እፉ​ኝ​ትም፥ ነዘር እባ​ብም፥ በሚ​ወ​ጡ​ባት በመ​ከ​ራና በጭ​ን​ቀት ምድር በኩል ብል​ጽ​ግ​ና​ቸ​ውን በአ​ህ​ዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛ​ግ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በግ​መ​ሎች ሻኛ ላይ እየ​ጫኑ ወደ​ማ​ይ​ጠ​ቅ​ሙ​አ​ቸው ሕዝብ ይሄ​ዳሉ። 7የግ​ብፅ ርዳታ ከን​ቱና ባዶ ነው፤ ስለ​ዚህ፥ “ምክ​ራ​ችሁ ከንቱ ነው” ብለህ ንገ​ራ​ቸው። 8አሁን ተቀ​መጥ፤ ለሚ​መ​ጣ​ውም ዘመን ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ሆን በሰ​ሌዳ ላይ በመ​ጽ​ሐ​ፍም ውስጥ ጻፍ​ላ​ቸው።
ዐመ​ፀኛ ሕዝብ
9ዐመ​ፀኛ ወገን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ለመ​ስ​ማት እምቢ ያሉ የሐ​ሰት ልጆች ናቸ​ውና፤ 10ነቢ​ያ​ትን፥ “አት​ን​ገ​ሩን፤ ባለ ራእ​ዮ​ች​ንም አታ​ው​ሩን፤ ነገር ግን ሌላ​ውን ስሕ​ተት አስ​ረ​ዱን፤ ንገ​ሩ​ንም” ይላሉ፤ 11“ከዚህ መን​ገድ መል​ሱን፤ ከዚ​ህም ፈቀቅ አድ​ር​ጉን በሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቅዱስ ትም​ህ​ርት ከእኛ ዘንድ አስ​ወ​ግዱ” ይሏ​ቸ​ዋል። 12ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ እን​ዲህ ይላል፥ “ይህ​ችን ቃል አቃ​ል​ላ​ች​ኋ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትና በጠ​ማ​ማ​ነት ተስፋ አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ አጕ​ረ​ም​ር​ማ​ች​ኋ​ል​ምና፥ በዚ​ህም ቃል ታም​ና​ች​ኋ​ልና፤ 13ስለ​ዚህ ይህ በደል አዘ​ብ​ዝቦ ለመ​ፍ​ረስ እንደ ቀረበ፥ አፈ​ራ​ረ​ሱም ፈጥኖ ድን​ገት እን​ደ​ሚ​መጣ እንደ ከተማ ቅጥር ይሆ​ን​ባ​ች​ኋል። 14አወ​ዳ​ደ​ቁም እንደ ሸክላ ሠሪ ገንቦ የደ​ቀቀ ይሆ​ናል፤ ሳይ​ራ​ራም ያደ​ቅ​ቀ​ዋል፤ ከስ​ባ​ሪ​ውም እሳት ከማ​ን​ደጃ የሚ​ወ​ስ​ዱ​በት፥ ወይም ውኃ ከጕ​ድ​ጓድ የሚ​ቀ​ዱ​በት ገል አይ​ገ​ኝም።”
15የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “ብት​ጸ​ጸ​ትና ብታ​ለ​ቅስ ትድ​ና​ለህ፤ የት እን​ዳ​ለ​ህም ታው​ቃ​ለህ፤ በከ​ንቱ ታም​ነ​ሃ​ልና፤ ኀይ​ላ​ች​ሁም ከንቱ ይሆ​ናል፤ እና​ንተ ግን መስ​ማ​ትን እንቢ አላ​ችሁ፤ 16ነገር ግን፥ በፈ​ረስ ላይ ተቀ​ም​ጠን እን​ሸ​ሻ​ለን እንጂ እን​ዲህ አይ​ሆ​ንም አላ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ፤ ደግ​ሞም በፈ​ጣን ፈረስ ላይ እን​ቀ​መ​ጣ​ለን አላ​ችሁ፤ ስለ​ዚ​ህም የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ችሁ ፈጣ​ኖች ይሆ​ናሉ። 17ከአ​ንድ ሰው ዛቻ የተ​ነሣ ሺህ ሰዎች ይሸ​ሻሉ፤ እና​ን​ተም በተ​ራራ ራስ ላይ እን​ዳለ ምሰሶ፥ በኮ​ረ​ብ​ታም ላይ እን​ዳለ ምል​ክት ሆና​ችሁ እስ​ክ​ት​ቀሩ ድረስ፥ ከአ​ም​ስት ሰዎች ዛቻ የተ​ነሣ ብዙ​ዎች ይሸ​ሻሉ።”
18አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራጅ ነውና ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይራ​ራ​ላ​ችሁ ዘንድ ይታ​ገ​ሣል፤ ይም​ራ​ች​ሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እር​ሱን በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው። 19ቅዱስ ሕዝብ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ በጽ​ዮን ይኖ​ራል፤ ልቅ​ሶን አል​ቅሺ፤ ይቅር በለ​ኝም በዪ፤ ልቅ​ሶ​ሽን ባየ ጊዜ ይቅር ይል​ሻል፤ ሰም​ቶ​ሻ​ልና። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የጭ​ን​ቀ​ትን እን​ጀ​ራና የመ​ከ​ራን ውኃ ይሰ​ጥ​ሃል። የሚ​ያ​ሳ​ስ​ቱ​ህም እን​ግ​ዲህ ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ቡም፤ ዐይ​ኖ​ችህ ግን የሚ​ያ​ሳ​ስ​ቱ​ህን ያያሉ፤ 21ወደ ቀኝም ቢሆን ወደ ግራም ቢሆን በኋ​ላህ በዚህ መን​ገድ እን​ሂድ የሚ​ሉና የሚ​ሳ​ሳቱ ሰዎ​ችን ድምፅ ጆሮ​ዎ​ችህ ይሰ​ማሉ። 22በብ​ርም ወደ ተለ​በጡ፥ በወ​ር​ቅም ወደ አጌጡ ወደ ጣዖ​ታቱ እን​ሂድ የሚሉ ናቸው፤ ያን​ጊዜ እንደ ትቢያ የደ​ቀቁ ይሆ​ናሉ፤ እንደ ውኃም ይደ​ፈ​ር​ሳሉ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ጥራ​ጊ​ዎ​ችን ይጥ​ሉ​ባ​ቸ​ዋል። 23በም​ድ​ርም ለተ​ዘ​ራው ዘርህ ዝናም ይዘ​ን​ማል፤ ከም​ድ​ርም ፍሬ የሚ​ወጣ እን​ጀራ ወፍ​ራ​ምና ብዙ ይሆ​ናል። በዚ​ያም ቀን ከብ​ቶ​ችህ በሰ​ፊና በለ​መ​ለመ መስክ ይሰ​ማ​ራሉ፤ 24መሬ​ት​ንም የሚ​ያ​ርሱ በሬ​ዎ​ችና አህ​ዮች በመ​ን​ሽና በወ​ን​ፊት የነ​ጻ​ውን ከገ​ብስ ጋር የተ​ቀ​ላ​ቀ​ለ​ውን ገፈራ ይበ​ላሉ። 25በታ​ላ​ቅም እል​ቂት ቀን ግን​ቦች በወ​ደቁ ጊዜ፥ በረ​ዥሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለ​ውም ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ ወን​ዞ​ችና የውኃ ፈሳ​ሾች ይሆ​ናሉ። 26እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕ​ዝ​ቡን ስብ​ራት በጠ​ገነ ዕለት፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍቱ የቈ​ሰ​ለ​ው​ንም በፈ​ወሰ ዕለት፥ የጨ​ረቃ ብር​ሃን እንደ ፀሐይ ብር​ሃን፥ የፀ​ሐ​ይም ብር​ሃን እንደ ሰባት ቀን ብር​ሃን ሰባት እጥፍ ይሆ​ናል።
27እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመ​ጣል፤ ቍጣ​ውም ከከ​ን​ፈ​ሮቹ ቃል ክብር ጋር ይነ​ድ​ዳል፤ ቃሉም ቍጣን የተ​መላ ነው፤ የቍ​ጣ​ውም መቅ​ሠ​ፍት እን​ደ​ም​ት​በላ እሳት ናት፤ 28እስ​ት​ን​ፋ​ሱም አሕ​ዛ​ብን ስለ ከንቱ ስሕ​ተ​ታ​ቸው ሊከ​ፋ​ፍ​ላ​ቸው በሸ​ለቆ እን​ደ​ሚ​ያ​ጥ​ለ​ቀ​ልቅ፥ እስከ አን​ገ​ትም እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስና እን​ደ​ሚ​ከ​ፋ​ፍል ውኃ ይጐ​ር​ፋል፤ ስሕ​ተ​ታ​ቸ​ውም ይከ​ተ​ላ​ቸ​ዋል፤ ይወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋ​ልም። 29በዐ​ልን እን​ደ​ሚ​ያ​ከ​ብሩ፥ ሁል​ጊዜ ደስ ሊላ​ችሁ፥ ወደ ተቀ​ደ​ሰው ቦታ​የም ልት​ሄዱ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ቸው በእ​ን​ቢ​ልታ ወደ እስ​ራ​ኤል ቅዱስ ልት​ሄዱ ይገ​ባ​ች​ኋል። 30እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የድ​ም​ፁን ክብር ያሰ​ማል፤ የክ​ን​ዱ​ንም መፈ​ራት፥ በጽኑ ቍጣና በም​ት​በላ እሳት፥ በወ​ጀ​ብም፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም፥ በበ​ረ​ዶም ድን​ጋይ ይገ​ል​ጣል። 31አሦ​ርም በመ​ቅ​ሠ​ፍቱ#ዕብ. “በብ​ትር” ይላል። ከመ​ታው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድምፅ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣል። 32እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላዩ የሚ​ያ​ወ​ር​ድ​በት የታ​ዘ​ዘ​በቱ የበ​ትር ድብ​ደባ ሁሉ በከ​በ​ሮና በመ​ሰ​ንቆ ይሆ​ናል፤ በጦ​ር​ነ​ትም ክን​ዱን አን​ሥቶ ይዋ​ጋ​ቸ​ዋል። 33ከቀ​ድ​ሞም ጀምሮ የማ​ቃ​ጠያ ስፍራ ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ለች፤ ለን​ጉ​ሥም ተበ​ጅ​ታ​ለች፤ ጥል​ቅና ሰፊም አድ​ር​ጎ​አ​ታል፤ እሳ​ትና ብዙ ማገዶ ተከ​ም​ሮ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in