YouVersion Logo
Search Icon

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 33

33
ከጠ​ላት ስለ መዳን የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
1ለሚ​ያ​ዋ​ር​ዱ​አ​ችሁ ወዮ​ላ​ቸው! እና​ን​ተን ግን የሚ​ያ​ዋ​ር​ዳ​ችሁ የለም፤ የሚ​ወ​ነ​ጅ​ላ​ችሁ እና​ን​ተን የሚ​ወ​ነ​ጅል አይ​ደ​ለም፤ ወን​ጀ​ለ​ኞች ይጠ​መ​ዳሉ፤ ይያ​ዛ​ሉም፤ ብል እን​ደ​በ​ላው ልብ​ስም ያል​ቃሉ።#ምዕ. 33 ቍ. 1 የዕብ. ልዩ ነው። 2አቤቱ፥ ማረን፤ አን​ተን ተማ​ም​ነ​ና​ልና፤ የዐ​ላ​ው​ያን ዘራ​ቸው ለጥ​ፋት ነው፤#ዕብ. “ጥዋት ጥዋት ክንድ ሁነን፥” ይላል። በመ​ከ​ራም ጊዜ መድ​ኀ​ኒ​ታ​ችን አንተ ነህ። 3ከቃ​ልህ ግርማ የተ​ነሣ አሕ​ዛብ ፈር​ተው ሸሹ፤ አሕ​ዛ​ብም ተበ​ተኑ።
4አን​በጣ እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ሰብ ትን​ሹም ትል​ቁም ምር​ኮ​አ​ችሁ እን​ዲሁ ይሰ​በ​ሰ​ብ​ላ​ች​ኋል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እን​ዲሁ ያፌ​ዙ​ባ​ች​ኋል” ይላል። 5በአ​ር​ያም የሚ​ኖር ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይኖ​ራል፤ ጽዮ​ንም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ተሞ​ላች። 6በድ​ኅ​ነ​ታ​ችን መዝ​ገብ በሕግ ይሰ​በ​ስ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፤ ጥበ​ብና ምክር፥ ጽድ​ቅም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህም የጽ​ድቅ መዝ​ገ​ቦች ናቸው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. ከግ​እዙ ይለ​ያል።
7እነሆ እና​ንተ ቀድሞ ትፈ​ሩ​አ​ቸው የነ​በሩ በግ​ር​ማ​ችሁ ይፈ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ከእ​ና​ን​ተም የተ​ነሣ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ። መል​እ​ክ​ተ​ኞች መራራ ልቅ​ሶን እያ​ለ​ቀሱ ይላ​ካሉ፤ ሰላ​ም​ንም ይለ​ም​ናሉ። 8መን​ገ​ዶች ባድማ ሆኑ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብም መፈ​ራት ቀረ፤ ቃል ኪዳ​ና​ቸ​ውም ፈረሰ፤ እንደ ሰውም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸ​ውም። 9ምድር አለ​ቀ​ሰች፤ ሊባ​ኖስ አፈረ፤ ሳሮ​ንም እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ገሊ​ላና ቀር​ሜ​ሎስ ታወቁ።
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “አሁን እነ​ሣ​ለሁ፤ አሁን እከ​ብ​ራ​ለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላ​ለሁ። 11ዛሬ ታያ​ላ​ችሁ፤ ዛሬ ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ፤ የመ​ን​ፈ​ሳ​ች​ሁም ኀይል ከንቱ ይሆ​ናል፤ እሳ​ትም ትበ​ላ​ች​ኋ​ለች።#ዕብ. “ገለ​ባን ትጸ​ን​ሳ​ላ​ችሁ ፤ እብ​ቅ​ንም ትወ​ል​ዳ​ላ​ችሁ ፤ እስ​ት​ን​ፋ​ሳ​ችሁ የም​ት​በ​ላ​ችሁ እሳት ናት” ይላል። 12አሕ​ዛ​ብም በእ​ርሻ ውስጥ ተቈ​ርጦ እንደ ተጣ​ለና በእ​ሳት እንደ ተቃ​ጠለ እሾህ የተ​ቃ​ጠሉ ይሆ​ናሉ።”
13በሩቅ ያሉ የሠ​ራ​ሁ​ትን ይሰ​ማሉ፤ በቅ​ር​ብም ያሉ ኀይ​ሌን ያው​ቃሉ። 14በጽ​ዮን ያሉ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ፈሩ፤ መን​ቀ​ጥ​ቀጥ ዝን​ጉ​ዎ​ችን ያዘ፤ እሳት እን​ደ​ሚ​ነ​ድድ የሚ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ማን ነው? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሀገ​ር​ንስ የሚ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ማን ነው? 15በጽ​ድቅ የሚ​ሄድ፥ ቅን ነገ​ር​ንም የሚ​ና​ገር፥ በደ​ል​ንና ኀጢ​አ​ትን የሚ​ጠላ፥ መማ​ለ​ጃን ከመ​ጨ​በጥ እጁን የሚ​ያ​ራ​ግፍ፥ ደም ማፍ​ሰ​ስን ከመ​ስ​ማት ጆሮ​ቹን የሚ​ደ​ፍን፥ ክፋ​ት​ንም ከማ​የት ዐይ​ኖ​ቹን የሚ​ጨ​ፍን ነው። 16እርሱ ከፍ ባለ በጽ​ኑዕ ዓለት ዋሻ ይኖ​ራል፤ እን​ጀ​ራም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ውኃ​ውም የታ​መ​ነች ትሆ​ና​ለች።
ስለ​ሚ​መ​ጣው የክ​ብር ዘመን
17ንጉ​ሥን በክ​ብሩ ታዩ​ታ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በሩቅ ያለች ምድ​ርን ያዩ​አ​ታል። 18ልባ​ች​ሁም፥ “ጸሓ​ፊ​ዎች ወዴት አሉ? መማ​ክ​ር​ትስ ወዴት አሉ? የት​ን​ሹና የት​ልቁ ዐማ​ፅ​ያን ብዛ​ትስ ወዴት አለ?” ብሎ ፍር​ሀ​ትን ያስ​ባል። 19የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን አሕ​ዛብ አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ንት ዐማ​ፅ​ያን ሕዝብ፥ ጥልቅ ነገ​ርን ትሰ​ማ​ላ​ችሁ። የሚ​ሰ​ማም ማስ​ተ​ዋል እን​ደ​ሌ​ለው ይሆ​ናል።
20እነሆ፥ የመ​ድ​ኀ​ኒ​ታ​ች​ንን ከተማ ጽዮ​ንን ተመ​ል​ከት፤ ዐይ​ኖ​ች​ህም ድን​ኳ​ኖ​ችዋ የማ​ይ​ና​ወጡ፥ ካስ​ማ​ዎ​ችዋ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የማ​ይ​ነ​ቀሉ፥ አው​ታ​ሮ​ች​ዋም ሁሉ የማ​ይ​በ​ጠሱ፥ የበ​ለ​ጸ​ገች ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ያያሉ። 21የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ለእ​ና​ንተ ታላቅ ነው፤ ሀገ​ራ​ች​ሁም የሰፉ ወን​ዞ​ችና ታላቅ የመ​ስኖ ስፍራ ይሆ​ናል፤ በዚ​ህች መን​ገድ አት​ሄ​ድም፤ መር​ከ​ቦ​ችም አይ​ሄ​ዱም። 22አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነውና ቸል አይ​ለ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራ​ጃ​ችን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አለ​ቃ​ችን” ይላል። ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉ​ሣ​ችን ነው፤ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነ​ናል።
23ገመ​ዶ​ችሽ ተበ​ጥ​ሰ​ዋል፤ ጥን​ካሬ የላ​ቸ​ው​ምና፤ ደቀ​ልሽ ዘመመ፤ ሸራ​ው​ንም መዘ​ር​ጋት አል​ቻ​ለም፤ እስ​ከ​ሚ​ያ​ዝም ድረስ አላ​ማ​ውን አል​ተ​ሸ​ከ​መም። በዚ​ያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ተከ​ፈለ፤ ብዙ አን​ካ​ሶች እንኳ ምር​ኮ​ውን ማረኩ። 24በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም የሚ​ቀ​መጥ ሕዝብ፦ ደክ​ሜ​አ​ለሁ አይ​ልም፥ በደ​ላ​ቸው ይቅር ይባ​ል​ላ​ቸ​ዋ​ልና።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in